Addis Maleda - አዲስ ማለዳ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


ዜና ከምንጩ

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


የትግራይ ክልል የፖለቲካ ውዝግብ ከሁለቱ ተፋላሚዎች ባለፈ የክልሉን ሊህቃን ለሁለት የከፈለ ሆኗል፡፡

የህዝቡን እሮሮ ለመስማት አለመፍቀድ ፣የስልጣን ሽኩቻ ውስጥ መግባትና መሰል ሂደቶችን ማስተናገድ የክልሉ ነባራዊ ሃቅ ከሆነም ሰነባብቷል፤ የሚሉት አቶ ክብሮም በርኸ በክልሉ ያለው ቀውስና እያጋጠመ ያለውን ፖለቲካ ውድቀት በሚመለከት ከትዝብታቸው አጋርተዋል፡፡

ሙሉ ቃለ-ምልልሱን ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ
https://youtu.be/pe-OjWSO2jk?si=1-aD15_hy2rYnrXr


"የመንግስት ተቋማት ፊት ለፊት የሚገኙ የመርካቶ ነጋዴዎች ላይ ብቻ ነው ቁጥጥር ያደረጉት” ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ማክሰኞ ህዳር 10 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የመንግስት ተቋማት ቁጥጥራቸውን ፊት ለፊት የሚገኙ የመርካቶ ነጋዴዎች ላይ ብቻ ማድረጋቸውን እንደ ትልቅ ክፍተት አግኝተነዋል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።

ከንቲባዋ ይህን ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አራተኛ ዓመት የስራ ዘመን፣ አንደኛ መደበኛ ጉባኤ የበጀት ዓመቱን የሶስት ወራት የስራ አፈፃፀም በቀረበበት ወቅት ነው።

በጉባኤው በዋነኝነት ጥያቄ ካስነሱ ጉዳዮች መካከልም፣ በመርካቶ ገበያ ከሰሞኑ በደረሰኝ ከመገበያየት ጋር የተነሱ አለመግባባቶች ነበር።

ከንቲባዋ መርካቶን ዳግም ለማልማት ከመነሳታችን በፊት የተለያዩ ጥናቶች አከናውነናል ያሉ ሲሆን ለዚህም ምክንያቱ መርካቶ የሀገሪቱ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ ከመሆኑ ጀርባ የህገ ወጥ ንግድ መሸሸጊያ ሆኖ በማግኘታችን ነው ብለዋል።

ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት የመንግስት ተቋማት ቁጥጥራቸውን ፊት ለፊት የሚገኙ የመርካቶ ነጋዴዎች ላይ ብቻ ማድረጋቸው እንደሆነ ነው የጠቆሙት።

" ሲነጋ ግብረ ሐይሎች እንዳያገኘን በሚል፣ በሌሊት ትልልቅ ተሸከርካሪዎች ተሰልፈው እቃ ጭነው ለመሄድ ጥረት ይደረጋል። ይህ ሀገርን ይጎዳል። ግብር መክፈል መርህ እስከሆነ፣ ችግሮቻችንን እያሳዩን እና የሚሰርቀውን ለእኛ አሳልፈው እየሰጡ እነርሱም ግድታቸውን መወጣት ነው ያለባቸው።" ሲሉ አስጠንቅቀዋል


ሲቪል ሰርቪስ በአንድ ብሔር ቁጥጥር ስር ነው መባሉን እና በፌዴራል የመንግስት መስሪያ ቤቶች ኢትዮጵያን የሚመስል የሰራተኞች ድልድል እንዲኖር በረቂቅ አዋጅ መቅረቡ ትክክል አይደለም ሲሉ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በፓርላማ ሰፊ ክርክር አድርገዋል፡፡

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ከዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ጋር በፓርላማ ያደረጉትን ፍጥጫ ከስር ባለው መስፈንጠሪያ ተጠቅመው በአዲስ ማለዳ ይከታተሉ

https://youtu.be/RzdONqXRWUE?si=QnxYL1re4_0Ah4Ik






በትግራይ ክልል አለ የተባለው አለመረጋጋት ሰዎች ወደ ክልሉ እንዳይመጡ ሆን ተብሎ የሚደረግ ሴራ ነው ተባለ

ማክሰኞ ህዳር 10 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) በትግራይ ክልል በተለያዩ ቦታዎች ተኩስ ተከፍቶ እንደነበር እና አለመረጋጋት መኖሩን በተለያዩ የማህበራዊ ድህረገጾች እና የዜና ምንጮች ሲነገር መቆየቱ ይታወቃል፡፡

በተለይም በትግራይ ክልል የማዕከላዊ ዞን አስተዳዳሪ ሰለሞን መዓሾ ባሳለፍነው እሁድ ማለትም ህዳር 08 ቀን 2017 ከአክሱም ወደ መቀሌ እየተጓዙ ባሉበት ወቅት ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ተኩስ እንደተከፈተባቸው መግለጻቸው ይታወቃል፡፡

መኪናቸው ላይ ተኩስ እንደተከፍተባቸው የገለጹት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ከአክሱም ወደ መቐለ ሲመለሱ ማይቅነጣል ፈላፍል በተባለ ቦታ ሲደርሱ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በተሽከርካሪ ውስጥ እሳቸውን ጨምሮ ሶስት ሰዎች እንደነበሩ እና በማንም ላይ የደረሰ ጉዳት ባይኖርም ተኩሱን የከፈቱባቸው አካላት እነማን እንደሆኑ ኮሚቴ ተቋቁሞ እንዲጣራላቸው ለክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር ጥያቄ ማቅረባቸውን አሳውቀዋል፡፡

አስተዳዳሪው ከትግራይ ክልል አመራር መከፋፈል በኋላ በአቶ ጌታቸው ረዳ ከሚመራው 16 ከፍተኛ አመራሮች መካከል አንዱ ሆነው የቀጠሉ ናቸው፡፡

በአንጻሩ የመግደል ሙከራ ተቃጥቶባቸዋል የተባለው አካባቢን የሚያስተዳድሩት አቶ ገብረ ተክለሃይማኖት በበኩላቸው “በማይ ቅነጣል ወረዳ ጉዳዩ አልተፈፀመም፤ መረጃው ከእውነት የራቀ ነው” ብለዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በክልሉ ያለው እንቅስቃሴ ምን ይመስላል ስትል አዲስ ማለዳ በአካባቢው ከሚኖሩ ምንጮች መረጃውን ለማጣራት የሞክራች ሲሆን እነዚህ ምንጮች በማዕከላዊ ዞን አስተዳዳሪዉ አቶ ሰለሞን መዓሾ መኪና ላይ ተኩስ መከፈቱን መስማታቸውን ጠቅሰዉ ከዚህ ውጪ በተለያዩ ማህበራዊ ድህረገጾች እንደሚናፈሰው በክልሉ ሁከትም ሆነ የተለየ ተኩስ አለመኖሩን ገልጸዋል፡፡

በትግራይ ክልል በድምቀት የሚከበረውን አመታዊ የፂዮን ማርያም ሀይማኖታዊ ክብረ በዓልን ተከትሎ እና ከሰሞኑ በነበሩ ዝግጅቶች ምክንያት ከተለመደው በዛ ባለመንገድ የፖሊስ ሀይሎች በአካባቢው ላይ ከመታየታቸው ውጪ ምንም አይነት አዲስ ነገር እንደሌለ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በተጨማሪም በዓሉን ተከትሎ በርካታ ሰዎች ከተለያዩ ክልሎች እና አካባቢዎች የሚመጡ ስለሆነ እና አንደኛው የቱሪስት መስህብ በመሆኑም ባልተረጋገጠ መረጃ ሆንተብሎ ሰዎችን ለማስቀረት የሚደረግ ሀሰተኛ መረጃ ስለመሆኑም የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል፡፡












“ዘመናቸውን የጨረሱ የምርጫ ቦርድ አመራሮች ከሃላፊነታቸው ሊነሱ ይገባል” ገዳ ቢሊሱማ ፓርቲ

ማክሰኞ ህዳር 10 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ዘመናቸውን የጨረሱ የምርጫ ቦርድ አባላት ከሃላፊነት ሊነሱ ይገባል ሲል ከሰሞኑ ፍቃዱ የተሰረዘው ገዳ ቢሊሱማ ፓርቲ ከሷል፡፡

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የፓርቲዎችን ፍቃድ በመሰረዝ የሰላማዊ ትግል በርን እየዘጋ ነው ያለው ፓርቲው፣ ይህ ደግሞ ሆን ብሎ የሚከናወን ነው ሲል አብራርቷል፡፡

ከሰሞኑ ከታገዱ የ11 የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆነው ገዳ ቢሊሱማ ፓርቲ ለአዲስ ማለዳ እንደገለጸው ምርጫ ቦርድ ህግን ባልጠበቀ መንገድ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ፍቃድ በማገድና በመሰረዝ የፖለቲካ እንቅስቃሴን እየዘጋ ነው ያለ ሲሆን ፤ ይህም በተለይ በበህሄር የተደራጁ ፓርቲዎችን ሆን ብሎ ለማጥፋት ያለመ ነው ብሏል፡፡

የቦርዱ አመራሮች 11 የፖለቲካ ፓርቲዎችን ፍቃድ በማገድ እና በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጉባኤ ላይ እንዳይገኙ በመከልከል የጋራ ምክር ቤቱን እንዲፈርስ ወይም ለሶስት ቦታ እንዲሰነጠቅ አድርገዋል በማለትም ፓርቲው ወቅሷል፡፡

ይህ ሂደት ከፓርቲ ስራ ባለፈ በአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ተካተው ውይይት ሲያደርጉ የነበሩ ፓርቲዎችን ጭምር የጎዳ ነው በማለትም ዘመናቸውን የጨረሱ የምርጫ ቦርድ አመራሮች ከሃላፊነት መነሳት አለባቸው ሲልም ሃሳቡን ሰንዝሯል፡፡

አዲስ ማለዳ የፓርቲውን ክስ በሚመለከት ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መልስ ለማገኘት በተደጋጋሚ ያደረገችው ጥረት ያልተሳካ ሲሆን በቀጣይ ቦርዱ ምላሽ በሚሰጥበት ወቅት የዘገባ ሽፋን የምንሰጥ ይሆናል፡፡






በሶማሊላንድ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ሙሴ ቢሂ በሰፊ ልዩነት ተሸነፉ

ማክሰኞ ህዳር 10 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በሶማሊላንድ በፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ሙሴ ቢሂ በሰፊ ልዩነት ሲሸነፉ አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ " ኢሮ " አሸነፈዋል።

የዋደኒ ፓርቲ እጩ ሆነው የቀረቡት አብዲራህማን ኢሮ ባለፈው ሳምንት የተካሄደውን የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ እንዳሸነፉ የምርጫ ኮሚሽኑ ዛሬ አሳውቋል።

በምርጫው ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ እንዲሁም ፋይሰል አሊ ዋርቤ ተሳታፊ የነበሩ ቢሆንም ድል ሳይቀናቸው ቀርቷል።

የኢሮ ፓርቲ ምርጫውን 63.92 በመቶ ድምፅ በማግኘት ነው ያሸነፈው። የተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ ፤ ኩልሚዬ ፓርቲ 34.81% ነው ያገኘው።

ሶማሌላንድ ከሶማሊያ ተገንጥላ እራሷን እንደ ነጻ ሀገር የምትቆጥር ስትሆን ላለፉት በርካታ አመታት ከሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የላትም።






በፍትህ ሚኒስቴር ጥያቄ የምክር ቤቱ አባል ያለመከሰስ መብታቸው ተነሳ

ማክሰኞ ህዳር 10 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የአዲስ አበባ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤው የአንድ አባሉን ያለመከሰስ መብት አንሥቷል።

በፍትሕ ሚኒስቴር በቀረበ ጥያቄ መሠረት የምክር ቤቱ አባል ሰዒድ ዓሊ ከማል ያለመከሰስ መብትን ያነሳ መሆኑን በምክር ቤቱ የሰላም፣ የፍትሕ እና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ አስታውቋል።

ቋሚ ኮሚቴው በሚኒስቴሩ የቀረበውን የሙስና ክስ በመመርመር የደረሰበትን ውጤት ለምክር ቤቱ ዝርዝር ሪፖርት አቅርቧል።

ምክር ቤቱ የቀረበው ሪፖርትን በመመልከት አባሉ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል በሕግ እንዲጠየቁ ለማድረግ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ በሙሉ ድምፅ መወሰኑን ከአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።




ሀብታቸውን በውጭ ባንኮች የሚያስቀምጡ ባለሐብቶች የሚቀጡት ቅጣት በቂ አይደለም ተባለ

ሰኞ ህዳር 09 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ሀብታቸውን ውጭ ባንኮች ውስጥ የሚያስቀምጡ ባለሀብቶች ሃገርን ከሚያሳጡት የውጭ ምንዛሬ አንጻር የሚቀጡት ቅጣት በቂ አይደለም ተብሏል

ከፍራንኮ ቫሉታ መከልከል ጋር ተያይዞ ቀድሞውንም የነዚህ ባለሃብቶች የውጭ ምንዛሬ ምንጭ ህጋዊ አልነበረም ሲሉ ከአዲስ ማለዳ ጋር ቆይታ ያደረጉ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ገልጸዋል፡፡

ባለሃብቶቹ የውጭ ምንዛሬ ምንጮቻቸውም ከጥቁር ገበያ እና በውጭ ባንኮች ያከማቹት ሀብታቸው ሊሆን ስለሚችል በሃገር ውስጥ ባንክ ማስቀመጥን አይፈልጉም ሲሉ አክለዋል፡፡

በተለይም ከፍራንኮ ቫሉታ መተግበር ቀደም ብሎም የውጭ ባንኮች ውስጥ ሀገር በቀል ባለሐብቶች ሀብታቸውን እንደሚያስቀምጡ ተገልቷል።

ነገር ግን እነዚህ ባለሀብቶች ሃገር ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሬ እንድታጣ ከማድረጋቸው ጋር ተያይዞ የሚተላለፍባቸው ቅጣት በቂ የሚባል አይደለም ያሉት የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎቹ ይህም ሊስተካከል ይገባል ብለዋል፡፡

20 last posts shown.