ኤልሮኢ ፡ (⚜ዝማሬ⚜)
የተወደደ ስምሽ ማርያም የተወደደ ስምሽ ማርያም
እንደአንቺ ንፁህ በዓለም የለም
አሳስቢልን እንዲምረን መድኃኔዓለም
በንፅህናሽ በመመረጥሽ
ድንግል በእውነት እፁብ ድንቅ ነሽ
አሳስቢልን እንዲምረን መድኃኔዓለም
ፍጥረታት አንቺን ይማፀኑሻል
ከሲኦል ዓለም አውጪን ይሉሻል
አሳስቢልን እንዲምረን መድኃኔዓለም
አስራትሽን ኢትዮጵያን
ጠብቂልን ድንግል ህዝቧን
አሳስቢልን እንዲምረን መድኃኔዓለም
@aleroe@Alerobot