Lifestyle
አንዱ ኪሎ ከ1,800 የአሜሪካን ዶላር በላይ የሚሸጠውን የሻይ ቅጠል ጣእም ለማወቅ ፡ ኒታ አምባኒን መሆን ያስፈልጋል ።
Silver tips Imperial የሚባለው ይህ አንደኛ ደረጃ የሻይ ቅጠል በህንድ ከምትገኘው Darjeeling ግዛት ከሚገኙ ኮረብታማ ስፍራዎች ላይ ይበቅላል ። እናም ምርቱ ሲደርስ ፡ ይህን የሻይ ቅጠል በመልቀም ሙያ በሰለጠኑ ባለሙያዎች ፡ የምሽቷ ጨረቃ ሙሉ በሆነችበት እለት ብቻ በጥንቃቄ ተለቅሞ ። በንፅህና ተጠብቆና ታሽጎ ፡ በህንድና ከህንድ ውጭ ላሉ ባለሃብቶች በአድራሻቸው ይላካል ። በጥቂት መጠንም ፡ ለመደብሮች ይከፋፈላል ።
..............
የኒታ አምባኒ ብሩህ ቀን የሚጀምረው ይህን ውድ ሻይ በመጠጣት ነው ። አስገራሚ ቀለም እና ማራኪ አሮማ ያለው ይህ የሻይ ቅጠል ፡ ጣእሙን የቀመሱ ሰወች እንደሚሉት የማንጎና የfrangipani አይነት የሚመስል ውስብስብ እና ቀምሶ ለማጣጣም እንጂ ለመግለፅ የሚያስቸግር የሚማርክ ጣእም አለው ።
................
ዛሬ በዚህ ፅሁፍ አብረን የምንቆየው ከህንዳዊቷን ቢሊየነር ከወ/ሮ ኒታ አምባኒ ጋር ነው ። እናም እሷ ፡ ጨረቃ ሙሉ በሆነበት ምሽት ብቻ የሚለቀመውን ውዱን እና ውስብስብ ጣእም ያለውን ሻይ ጠጥታ እስክትጨርስ እኛ መልበሻ ክፍሏ፡እንገባና ቅንጦት የሚባለውን ነገር ፡ ከነነብሱ እያየን እንቆያለን ።
.............................
በዚህ የወ/ሮ ኒታ አምባኒ መልበሻ ክፍል ውስጥ ከሚገኙት በሺህ የሚቆጠሩ አልባሳት መሀከል ፡ በጊነስ መፅሀፍ የተመዘገበው ፡ የአለም ውዱ ሳሪ ( የህንድ ባህላዊ ቀሚስ ) ይገኝበታል ፡ ይህ ባህላዊ ቀሚስ ፡ እጅግ ጥራት ባለው ሀር የተሰራ ሲሆን ፡ ዲዛይን ለማድረግ ፡ በሴት አልባሳት ዲዛይነርነት የታወቁ ፡ 25 ሴት ዲዛይነሮች ተሳትፈውበታል ፡ ከዚህ ቀሚስ ጀርባ ያለውን የክሪሽና ምስል የተሳለውም በህንድ እጅግ ታዋቂ በሆነ ዲዛይነር ነው ።
የዚህ ልብስ ጥለቶች የተሰሩት ፡ እጅግ ስስ እና ጠንካራ በሆኑ ፡ ከንፁህ ወርቅ እና ከንጹህ ብር በተሰሩ ቀጫጭን ክሮች የተሸመነ ሲሆን ፡ እንደፈርጥ ሆነው የሚያብረቀርቁት ደግሞ ፡ ሩቢ ፡ ኤመራልድ እና የአልማዝ ነጠብጣቦች ናቸው ። ይህን በአለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ የሰፈረውን ውድ ልብስ በዋናነት አነሳን እንጂ ፡ የወይዘሮዋ አልባሳት ፡ በተለይ የህንድ ባህላዊ አልባሳቶቹ ፡ ባብዛኛው በወርቅ ክሮች የተጌጡ ናቸው ።
...........
በነገራችን ላይ የኒታ አምባኒ አልባሳትን ያህል ባይሆንም በህንድ ውስጥ ከወርቅ ክር ልብሶችን መሸመን ፡ ሺህ ዘመናትን ያስቆጠረ የልብስ መስሪያ አንድ አካል ነው
............................
..............
በሂማልያ ብቻ ከሚገኝ የሚያምር ቆዳ ያለው አዞ የሚሰሩት ቦርሳዎች ።
.......
ሄርሜስ ፡ ዋና መደብሩ በፈረንሳይ ሀገር የሚገኝ ፡ የቅንጦት መደብር ነው ። በ1830ዎቹ የተቋቋመው ይህ ካምፓኒ ትኩረቱን በአብዛኛው ከቆዳ በሚሰሩ የሴት ቦርሳዎችና ተያያዥ የሆኑ ቁሶችን በማምረት የሚታወቅ ሲሆን ፡ ታርጌት አድርጎ የሚሰራው ከፍተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ነው ። እናም በዚህ ካምፓኒ ከሚሰሩት የቅንጦት ቦርሳዎች መሀከል በሂማልያ ከሚገኝ የአዞ ቆዳ የሚሰራው ቦርሳ ነው ።
እነዚህን ሄርሜስ ካምፓኒ ደረቱን ነፍቶ እስከ 150 ሺህ የአሜሪካን ዶላር የሚሸጣቸውን ቦርሳዎች የሚገዙት እጅግ ጥቂት የሆኑ ሰወች ሲሆኑ ፡ ከነዚህ መሀከል ወ/ኒታ አንዷ ናት ። ስለሆነም በመልበሻ ክፍሏ ውስጥ ለቁጥር የሚያዳግቱ በሂማልያ የአዞ ቆዳ ፡ በአንድ ባለሙያ ብቻ ማሽን ሳይነካቸው ፡ በእጅ ብቻ የተሰሩ ቦርሳዎችን ማየት ወይም የአለማችን ቁጥር አንድ የጫማ ዲዛይነር የሆነው የጂሚ ቾ ምርቶች የሆኑ hand made ጫማዎችን ማየት የሚገርም አይደለም ።
.................
ሌላው አስገራሚ ነገር የኒታ አምባኒ ሊፒስቲክ ነው ። ኒታ ፡ የሊፒስቲክ አድናቂ ናት ፡ የሊፒስቲክ ስብስቦቿ በመቶሺዎች ዶላር የሚገመቱ ሲሆን ፡ አንድም ሊፒስቲክ የላስቲክ ወይም የብረት መያዣ የለውም ፡ ሁሉም ሊፒስቲኮች የተሰሩት ወይ ከወርቅ ነው ፡ ካልሆነም እጅግ ጥራት ካለው ንፁህ ብር የተሰሩ ናቸው ።
..............
የማይኮፈስ ስብእና ባለቤት
በህንድ ውስጥ ፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ፡ በአለም ካሉት ቢሊየነሮች መሀከል ዋንኛ የሆነው ፡ የሙኬሽ አምባኒ ባለቤት የሆነችው ኒታ አምባኒ ፡ ህይወት ለሷ እንዲህ ናት ፡ የምትኖርበት ቤት በድፍን አለማችን ተወዳዳሪ የለውም ሆኖም ይህን መሰል እጅግ የቅንጦት ህይወት ውስጥ የምትኖር ሴት ብትሆንም ፡ ልክ እንደ ቢሊየነሩ ባለቤቷ ፡ እሷም እጅግ ተግባቢ ፡ አዛኝ እና ትሁት ወይም down to earth person የሚሏት አይነት ሴት ነች ። በዚህ ተወዳዳሪ በሌለው መኖሪያ ቤቷ ውስጥ የሚያገለግሉ ፡ በመቶ የሚቆጠሩ ሰራተኞች ያሉ ሲሆን ሁሉም ፡ እሷን ማዳም ባለቤቷን ደግሞ ሚስተር አምባኒ ብለው መጥራት አይችሉም ። ይህ የቤቱ ህግ ነው ፡ ሁሉም ሰራተኞች ፡ ባልየው ወንድሜ እሷን ደግሞ እህቴ በማለት በወንድምና በቤተሰብ ስሜት እንዲጠሩ እንጂ ፡ ቅጥ ባጣ አክብሮት እንዲያሳዩ አይጠበቅባቸውም ።
..................
እነዚህ ባልና ሚስቶች ቀኑን በሙሉ በየተከፋፈሉት የስራ መስክ ቢዚ ሆነው ስለሚውሉ ፡ የምሳ ሰአታቸውን በአብዛኛው አብሮ ለማሳለፍ አይችሉም ፡ ነገር ግን በእራት ሰአት ላይ ኒታ አምባኒ ቀድማ ብትገባ እንኳን ባለቤቷ ሳይመጣ ፈፅሞ ራት አትበላም ። በስራ ምክንያት ቢያመሽም እስኪመጣ ትጠብቀዋለች ። እናም እንደመጣ ከአለም ዙሪያ የተሰበሰቡ ቅጠላ ቅጠል የሚበዛባቸውን ምርጥ ምግቦችን እየተመገቡ የቀን ውሏቸውን ያወራሉ ። እርሱም ለሚስቱ ያለው ፍቅር ልዩ ከመሆኑ የተነሳ የልደት በአሏን ሰርፕራይዝ የሚያደርጋት በልዩ ሁኔታ ፈርኒሽድ የተደረገ የግል ጄት በመስጠት ነው ።
............
ኒታ አምባኒ በአለም ላይ ውስን ቁጥር ያለውን Audi A9 chameleon ን ጨምሮ በልዩ ትእዛዝ የተሰሩ መርሰዲሶችና ውድ መኪኖች ቢኖሯትም አንዳንዴ ነሸጥ ሲያደርጋት በተለይ ልጆቿ ታዳጊ በነበሩበት ወቅት ፡ በህዝብ አውቶብስ ወደ ትምህርት ቤት ይዛቸው ትሄድ ነበር ። በሀብት በተከለለ አለም ውስጥ ብቻ ተከልለው መኖር የለባቸውም ፡ የህብረተሰቡ አካል በመሆናቸው ፡ ኑሮውን በቅርብ ማወቅ አለባቸው የሚል መርህ አላት ።
.............
ህይወቷን በዚህ አይነት መልኩ የምትመራው ኒታ አምባኒ ፡ እና ቤተሰቧ ሰርተው ያገኙትን ገንዘብ ከግል መጠቀሚያ ባለፈ ፡ በበጎ አድራጎት ስራዎችም በህንድ ውስጥ የሚስተካከላቸው የለም ፡ በዚህም በ2020 የአለም አቀፍ የበጎ አድራጊ ግለሰቦች ሽልማትን አግኝታለች ። የኮቪድ ወረርሽኝ በተከሰተ ጊዜ በህንድ ውስጥ የመጀመሪያውን የኮቪድ ማገገሚያ ትልቅ ሆስፒታል ያሰራውም ይሄ ቤተሰብ ነው ።
በዋሲሁን ተስፋዬ