ቤተ-ግጥም እና ፍቅር


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Art


ግጥም '''ስሜቶች ከተደበቁበት ወረቀት ላይ ሰፍረዉ እልፍ ትዝታዎች ከተበተኑበት ተሰብስበዉ የሚቀመጡበት የጸሃፊያን ሀሳብ ማረፊያ የአንባቢያን መጽናኛ ነች''።
በዚ ቻናል @betagitim
ግጥሞች🔥💌
ደብዳቤዎች✍️💌 ያገኛሉ።
ሃሳብ እና አስተያየቶን በዚ 👇👇👇
ያናግሩን @YOTORAWIII

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Art
Statistics
Posts filter


አለሁም..........የለሁም
እንዲህ ይሰማኛል
መሬት ላይ ቁጭ ብዬ ሰላም ይነሳኛል
በሰው ተከብቤ ሰው እናፍቃለሁ
ሀሳብ እያጋራሁ ሰሚውን አጣለሁ
ልቤ አዝኖ ሲደማ መደበቂያ ሳጣ
ራሴን በራሴ በስቃይ ስቀጣ
ናፍቆት አደካክሞኝ ጉልበቴ እየዛለ
ዛሬም ምስኪን ልቤ ሰው ናፍቆ አለ
ደክሞኛል እላለሁ መድከም አላቆምም
✨እኔስ ግራ ገባኝ አለሁ ወይ የለሁም!!!!

✍️ቃል
@betagitim
@zemenenbegetem
@e_n_k_u_0


አንዳንዴ ማድረግ እያለብን የማናደርጋቸው ነገሮች........የሆነ ቀን ዋጋ ያስከፍሉናል🖤
ዛሬን አስበን ነገን እንገንባ
✨✨ሠናይ ቅዳሜ በድጋሚ ተመኘን🙌💞
@betagitim
@betagitim


አሞኛል🤕
ቃል አውጥቼ የማልተነፍስበት፣እህህህህህህ ብዬ የልቤን ሀዘን እንዲህ ነው ብዬ የማልገልፀው ህመም
ባስታወስኩህ ቁጥር በናፈከኝ ቁጥር የፍቅርህን ፍም በመዳፌ እያፈስኩኝ የሚወስድልኝ እስከማጣ ታምሜልሃለሁ🖤🖤
ከቃጠሎ መዳፌ፣ከነደደው ነብሴ፣ከከሰለው ልቤ መጥተህ ለአንድ አፍታ ብታድነኝ ምነው?
ደርሰህ ብትፈውሰኝ፣
በእቅፍህ ብታውለኝ
ከዚህ አለም ሁካታ ደርሰህ ብትሸሽገኝ

ብዬ እመኛለሁ.......ከንቱ ምኞት💔
✨ብቻ እየሞትኩም ቢሆን ፈውስህን እሻለሁ🙌✨
✍️ቃል
@betagitim
@betagitim
@e_n_k_u_0


ለምንወዳቸው የማንፈልገውን ነገር የምናደርገው ከዛ ሰው ደህንነት ስንል ነው♥️
ስንወድ ከነፍሳችን
ስንሰዋ እንደራሳችን
ግን አንዳንዴ ከንቱ ያደርጉብናል🖤
✨ ✨ ✨ ✨
ሠናይ ቅዳሜ✨🙌♥️
@betagitim
@betagitim


የቀዘቀዘ ቡናህን አትውቀሰው
ትኩስ ነበር ችላ አልከው
እንጂ!🙌


መውደድ........
ከልብ መዋሀድ
መናፈቅ
እየሄዱም እየመጡም ደርሶ እንደመጠበቅ
ናፍቆት እንደ ህማም
የልብን ስር ድካም

በትዝታ ቋጥኝ ተዘፍቆ መገኘት
በማፍቀር ሰንሰለት ተጠፍሮ መዋተት
ፍቅር...
በምሽት ጨረቃን ደርሶ እንደመጎብኘት
በማለዳ ፀሀይ ሞቆ እንደመደሰት
በሀሩር ቃጠሎ በዝናብ እንደመራስ
ከቀዝቃዛ በረዶ በሙቀት ነፍስን አንስቶ እንደማደስ
ትዝታ....
ተለያይቶም ደርሶ ታስሮ በትላንቱ
ይታወስ ሲጀምር ሲደረደር ስንቱ
ፍቅር ተጀምሮ
ናፍቆት ተደምሮ
ትዝታ እያሰረ
እየደረደረ
ነፍስን ከስጋ ከአለም አላቆ
✨ሞትን አስመኝቶ ህይወትንም ነጥቆ
✨በጭላንጭል ተስፋ ነፍስን እንደመስቀል
✨ፍቅር ይሉት ጉዳይ ራስንም ያስረሳል

✍️ቃል
@betagitim
@betagitim


Forward from: ቤተ-ግጥም እና ፍቅር
ሰክን ሀሳብ ስክን ማፍቀር
የሷ አመል የኔም አመል ነበር
ፍቅር ሲስብ የምድር ሰዉ
እሷን ሳበ አምላክ ፍቅርን መስላዉ


ተለየቺዉ አላመነም..ፍቅሩ አልበረረችም
ትመለሳለች የምድሩን ነገር አልጨረሰችም
ትመጣለች ..ታየዋለች ናፍቆቱን ተረድታ
አለዉ ትለዋለች ተመለሳ መጥታ!!!???
 
ጥያቄ...!!!???
ተነስ አለዉ እግዜር!!??
        ክንፍ ልስጥህ ትበራለህ??
ከሰማይ ወጥትህ ....
         ናፍቆትህን ትወጣለህ!?
ወይስ ዛሬ ማታ
   ነፍስህን ከስጋህ ለይቼ
     ላሳይህ እሷን አንተን ከሰማይ አዉጥቼ!??
  የቱን መረጥክ!!!??
     አንዱን በላ ወይ ስክን በል!?
  በፍቅርህ ዉስጥ እሷን ምስል
  እሷን አፍቅር፣
ከከፍታዉ ከሰማዩ እንድትበር!!!

ተጻፈ ✍️ በዳዊት


🗣ናትናኤል (ያላለቀ ሀሳብ)



@betagitim
@betagitim


የሽቶ ጠርሙሱን መስበር ጠረኑን ተጋኖ እንዲሸት ያደርጋል፤ ግን ለመጨረሻ ጊዜ ነው!።

@betagitim
@betagitim


ስትሄጂ ምን አለ ዝም ብለሽ ብትሄጂ ለምን አቀፍሺኝ💔


ይኽውልሽ አለሜ...ከሄድሽ ጀምሮ
ሰውነት ተረት ነው ስሜቴ ተቀብሮ
ካፊያ አመል ትርጉም
አልባ ኩንቱ መኖር
እየሄድኩኝ ወደ ማላውቀው
      የህይወት መስመር
የጣልኩትን የሚያነሳ
ንግግሬ የሚጥመው
ስላጣውኝ ለማወራው
ትኩረት የሚሰጠው
ብቸኛ ወዳጄ ወረቀት ሆነና
መጻፌን ነው ማውቀው
    ጉዳቴን ልረሳው ልቤን ከሀዘን ላቀና
በዚያች ጠባብ የወረቀት መስመር
ህመም ስቃዬን እንባዬን ስቀብር
ቅስምን የሚሰብር አሳዛኙ ቅኝት
ግጥሜን ሳነበው እንባ ይሞላል ከኔ ፊት
ባየሽ ...ባየሽ እያልኩ
  ትመጪያለሽ ብዬ ልቤን  በተስፋ ስሞላው
   ቤቴ ናፍቆሻል እያልኩ ስንቴ እንደማጸዳው
የሃሳብ ባሪያ ሁኜ ግዞተኛው
ለምን ሄደች እያልኩ ከዕድሜዬ አመሸው
እድሜ ላንቺ ህይወት ላይ ሸፈትኩ
ከሄድሽበት መንገድ በቁም ታሰርኩ
ዘንድሮ ከከረምኩኝ ካለውኝ በህይወት
እንዳምና አልጠብቅሽም
     ግጥምም አልጽፍ እውነት!!

✍️ዳዊት

@betagitim
@betagitim


እሱን ነበር የፈለኩት........አንድ እሱን ብቻ
እንዲወደኝ፣እንዲያፈቅረኝ፣እንዲመኘኝ አልጠበቅኩም።በየትኛውም ነገር ላይ እንዲያገን እንዲጎዳ አልፈለኩም
ሳቀርበው ስወደው ላፈቅረው ስነሳ ከቶም ከሱ አንዳች ምላሽ አልጠበቅኩም።
"እወድሃለሁ" አልኩት አላንገራገረም "እሺ"ነበር ያለኝ።
"ታስፈልገኛለህ"ስለው መጥቀሙን ያለምንም ስስት አሳይቶኛል።
መውደዴ ብሶ ድንገት ተሳስቼ ማፍቀሬን ባሳየው የልብ ምኞት አይቀር እሱም ቢያፈቅረኝ የሚል ትልቅ ምኞት መሰነቅ አይቀርም።
አልሆነም እንደማይሆንም አውቅ ነበር።በሱ በኩል አንዳች ስሜት እንደሌለ በስንት ጉዳጉድ ታጥሮ አንዳች እስርቤት ውስጥ መኖሩን አውቄ ሁሉን ልተውለት ከቶ ላላነሳ ራሴን አሳምኜ.......ልክ እንደ ጓደኛ የራስ ሰው እንደምንለው የሱን ደህንነት አስቀደምኩኝ
አንድ ነገር አውቃለሁ..... ስሜቶቻችን ከእኛ በታች መሆናቸውን.....ምንም ከሱ አልጠበቅኩም ምክንያቱም ታሳሪ ምንም አያደርግምና፤መልስም አልጠበቅኩም ግን ሁሉም ቀርቶ ጓ-ደኝነቱ ይቅር የሚል አንዳች ሀይል ሀሳቤን መና አስቀረው.....አውላላ ሜዳ ላይ እንደ ጉድ ተሰጣሁ.........ብቻ ስሙኝማ የሱ ነገር ይለያል አንዳች ተዐምር ተፈጥሮ ደህንነቱ ቢመለስ ለኔ ደስታዬ ነው ምንም አልጎደለኝ እሱ ስለነበር አሁን ግን መሄዱን ስረዳ መጉደሌን አመንኩኝ
.......መጉደል.......
.......ይከታል ከገደል........

✨ቃል ነበርኩኝ✨
🙌ሰናይ ቀን ተመኘሁ🙌
@betagitim
@zemenenbegetem


ናፈቅሽኝ
****

መናፈቅ ምንድን ነው?
ምንድን ነው ሰው ማስብ፤
እሩቅ ያለን ፀሀይ እሩቅ ያለን ጀንብር
ሲመሽ እንዲህ መራብ።

እያወቁ መሄድ እያወቁ መራቅ
ከማለም መናጠብ፤
ከመፈቀር ማለቅ… …

መናፈቅ ምንድን ነው?

ከጉዞ መደንቀፍ ከመሄድ ፈር መሳት
ከሰጡት እልፍ ደስታ ያፍቃሪን ሳቅ መስረቅ

መናፈቅ ምንድን ነው
ምን ይሆን ትዝታ
ፍርሃት ፍርሃት የሚል
ሲመሽ ወደ ማታ።

kidus kass

@betagitim
@betagitim


እድሜ ላንቺ መሆን ማልፈልገው ሰዉ ስላደረግሺኝ💔😣


🫡ማለፊያ

ህይወት በጊዜ የታጠረች አጥር ናት እና በዚያ አጥር መሃል ሁነን በምናከናውነው ተግባር የህይወትን ትርጉም እንረዳለን ለዛም መሰለኝ ሁላችንም ለህይወት ያለን አመለካከት ፍጹም የተለያየ የሆነው ...
🫡🫶🫶🫶🫶🫶🫶🫶🫶🫶
✍️ዳዊት

🫡@betagitim


ደህና ነኝ🤗........... ማለት እፈልጋለሁ🗣 ግን ደግሞ ደህና አይደለሁም🥹............. መሆን እፈልጋለሁ፤ግን ደግሞ ከባድ ሆኖብኛል🙄ምናልባትም ብጮህ😫😫ማንም ሳያስቆመኝ ባለቅስ😭.............. ወይም የውስጤን ሚያዳምጠኝ👂ሰው አግንቼ ብነግረው🗣 .......ወይም ውስጤን ከፍቼ ማሳየው👀 ብቻ አላውቅም😶 ........አሁን ላይ ምከፋበት🥺😞...... እንጂ የተደሰትኩበት😄 ጊዜ እረስቼዋለሁ🙃 .......አንዳንዴ "አምላክ ያውቃል" ትል ነበር አያቴ ነብሷን ይማረውና👵 እሱን እያሰብኩ ልፅናና እሞክራለሁ😑 ግን ውስጤ የሆነ ከገሞራ እሳት የበለጠ🥵......... ሚያቃጥል ከውቅያኖስ ስር ካለው የበለጠ ቅዝቃዜ🥶 .......ውስጤን ይሰማኛል.................ግን አንድ ነገር እወቁ
...............ደህና ነኝ.............
✍️ቃል
@betagitim


እንታረቅ --?
=======

ትወደኝ እንደሆን?
አውቃለሁ በመላ፣
ጠላሁሽ አትበለኝ…
ዛ'ሬ ብንጣላ ።

ፀብ በቀን ይሻራል
መውደድ ዘላለም ነው፤
አንተን ከሞት በቀር…
የሚነጥቀኝ ማን ነው ።

በል እስኪ ንገረኝ?
ይቅር የማያስብል ጥፋት ካለ ባ'ዓለም
ሁሉም ሲኦል እንጂ …
ገነት የሚገባ አንዳችም ነ'ፍስ የለም።

እንታረቅ ውዴ?
መለያየት እን'ጣፍ እርቀት እንስፋ?
ለንፋስ አንፍቀድ… …
ሽንቁር ልባችንን ገብቶ እንዳያሰፋ።

እንደዚህ ነው አትበል?
እንደዚያ ነው አትበል?
ከምድር የሚገዝፍ…
ፍቅር ተቀምጦ እኔ'ና አንተ መሀል።

ተጣልተን አንቅር!?
የሚስቀው ሰይጣን ስንታረቅ ያልቅስ?
ፍቅር ያሸንንፋል…
የሰራነው ገደል በይቅርታ ይፍረስ።

Kidus Kass

@betagitim
@betagitim


መሄድ ካለብህ ስንብት አታብዛ😐


አይሄዱም ያልሻቸው ከጎንሽ
የሉም፣ተውከኝ ያልሽው ፈጣሪሽ ነው
የቀረሽ እሱ ደግሞ ከሁሉም
ይበልጣል🙏

@betagitim
@betagitim


#ቃል_ና_አንቺ

 ሀሳብ ና ህልምሽ የዉድቀት
ማሰቡን አስቢ ገላሽ ምነው ቢቀርበት
ልቤ ሸንገላሽን ለምዶ እየኖረ
በጣፋጭ ውሽትሽ ወይን እየሰከረ
  ያልሺኝ እያስብኩ ፍቅር ሰንጀምር
    ቃልሽን አምኜ አንቺኑ ሳፈቅር
ልብሽ ዉሎ ከኔ ገላሽ ግን ከሌላ
ለልቤ ምክኒያት ባይሆን አንቺን           
          እንዲጠላ
ከማመን በሽታ ይገላግለኝና
ቃል እና አንቺ ታረቁልኝና
 
  ለሀጥያት ንስሃ በቅተሽ  ለሱባዬ
  በአመት ዣንጥላ አለኝ ለጌታዬ።
   

✍️ዳዊት

2013
@betagitim
@betagitim
@betagitim


የፃፍኩልሽን ደብዳቤ አታንብቢው!
             (ልዑል ኃይሌ)


ሞኝ ነው ወረቀት
የፃፉለትን ቃል ያምናል ተቀብሎ፤
አልወዳትም የሚል
ፅሁፍ ሰፈረበት የኔን እውነት ጥሎ፤
ከንዴት ስነቃ
ወረቀት የያዘው ረገምኩት ያንን ቃል፤
መውደዴ እንዴት ጠፋው
በብጣሽ ወረቀት እንዴት ፍቅር ያልቃል?፤
.
ይህን የውሸት ቃል
የውሸት ደብዳቤ ጨምድጄ እንዳልቀደው፤
እንዲሠጥሽ ብዬ
አዘጋጅቼለት ፖስተኛ ወሠደው፤
ግን ደግሞ ፈራሁኝ
በዚህ ቅፅበት ምክንያት አንቺን እንዳላጣ፤
የፍርዴን ደብዳቤ
የሚሽርልኝን ቅፅበት ከየት ላምጣ?፤
.
ሌላ ደብዳቤ ፃፍኩ!..
ይድረስ ለማልወድሽ
ለማትናፍቂኝ ሴት ለማልፈልግሽ ሠው፤
ከሃዲ ነች ብልም
ሰሚ ስለማጣ ዓለሙ ይቅመሠው፤
ሂጂለት ሕዝበ-አዳም
ምን ተዳዬ 'ኔ ብቻ ለምን 'ታመማለሁ፤
ማመን የፈለገ ይምጣና ይጎብኘኝ
ስታርጂኝ የቀረ ጠባሳ ይዣለሁ፤
ካመንሺም እመኚ
ካላመንሺም ይቅር፤
ከእንግዲህ በቅቶኛል
የዕቃቃ ጨዋታ የማስመሠል ፍቅር፤
.
ደገምኩት!ያንን ቃል
የላዩን መልዕክቴን የፊቱን ደብዳቤ፤
ሞኝ ነው ወረቀት
ምንም አልገባውም
ባሠፈርኩበት ቃል እንዲያ መንገብገቤ፤
.
ደግሜ መከርኩት
'አትመልከትብኝ የልቤን ስብራት'፤
ይልቅ እንዳልታመምኩ አስመስለህ ጥራት፤
ብዬ ብገስፀው
እያስተሳሰረ ከልቤ ሕመም ጋራ፤
እውነቴን መሸፈን
ክህደቴን መሸፈን ወረቀቴ ፈራ፤
.
እውነት ነው!
.
ሞኝ ነው ሞኝ ነው
ሞኝ ነው ወረቀት፤
እንዴት ብሎ አመነኝ
ባሰፈርኩበት ልክ በፃፍኩበት ርቀት፤
.
(ቲሽ!...ቀደድኩት!..)
.
(በቃ ትቼዋለሁ)
ለማስፈር ከበደኝ
ለዛኛው ደብዳቤ ማስተባበያ ቃል፤
ባስተባብለውም
የብዕሬ ቀለም ከልቤ እውነት ርቋል፤
.
ደጋግመሽ ብትጥይኝ
ያላንቺ ማትወጣ ጀምበር ታቅፌያለሁ፤
ይሄንን እያወቅኩ
አልወድሽም ብዬ እንዴት እፅፋለሁ?፤
ስለዚህ ሲደርስሽ
"ወረቀት ሞኝ ነው" የሚል ቃል አስታውሺ፤
ሞኝ አያጣላንም
ቀዳድደሽ ጣዪና ደግመሽ ተመለሺ፤

ታኅሳስ 5,2012 ዓ.ም.
🦋🙏
@betagitim
@betagitim.
@betagitim

20 last posts shown.