Forward from: በእውቀቱ ስዩም እና ሌሎችም
የጥቅምት መስክ ነኝ !!
ሰው ለሰው ይፈርዳል
ልብን ዘልቆ ሳያይ
ላልቃሽ እያዘነ
በፈካ ገፅ ውስጥ ያደፈጠን ስቃይ
-ማነው የመዘነ?
የይስሙላም ይሁን፣ከልብ ያለቀሰ
አያጣም አይዞህ ባይ
ካንጀት ይሁን ካንገት ፣ እንባ ላፈሰሰ
አይጠፋም ከምንገድ ፣መሀረብ አቀባይ
ይብላኝ ላሳሳች ፊት፣አፅናኝ ለማይጋብዝ
አንዳንድ ሀዘን አለ
ከላይ ተሰውሮ ፣ ልብ የሚበዘብዝ
የጥቅምት ብሩህ መስክ፣ አደይ የለበሰ
ስንቱን ጉድ አዝሎታል፣ስሩ ከተማሰ!!
የጥቅምት መስክ ነኝ ፣አደይ ያደመቀው
ፈገግታ ቢውጠው፣ዘበት ቢደብቀው
የኔን ብቻ ህመም፣እኔው ነኝ የማውቀው።
➲ ከበእውቀቱ ስዩም
━━━━━━✦✗✦━━━━━━
✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @bewketuseyum
@bewketuseyum
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟
ሰው ለሰው ይፈርዳል
ልብን ዘልቆ ሳያይ
ላልቃሽ እያዘነ
በፈካ ገፅ ውስጥ ያደፈጠን ስቃይ
-ማነው የመዘነ?
የይስሙላም ይሁን፣ከልብ ያለቀሰ
አያጣም አይዞህ ባይ
ካንጀት ይሁን ካንገት ፣ እንባ ላፈሰሰ
አይጠፋም ከምንገድ ፣መሀረብ አቀባይ
ይብላኝ ላሳሳች ፊት፣አፅናኝ ለማይጋብዝ
አንዳንድ ሀዘን አለ
ከላይ ተሰውሮ ፣ ልብ የሚበዘብዝ
የጥቅምት ብሩህ መስክ፣ አደይ የለበሰ
ስንቱን ጉድ አዝሎታል፣ስሩ ከተማሰ!!
የጥቅምት መስክ ነኝ ፣አደይ ያደመቀው
ፈገግታ ቢውጠው፣ዘበት ቢደብቀው
የኔን ብቻ ህመም፣እኔው ነኝ የማውቀው።
➲ ከበእውቀቱ ስዩም
━━━━━━✦✗✦━━━━━━
✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @bewketuseyum
@bewketuseyum
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟