መለስ ብየ ሳስብ አብዘሃኛውን የስራ ህይወቴ ከአንድ ስራ በላይ(over employed: multiple Full Time and part-time Jobs at the same time ) እየሰራሁ እንደነበር አስተዋልኩ:: ኮቪድ በሰው ልጆች ህይዎት ላይ ካመጣቸው ለውጦች አንዱ አብዘኛው ሰራተኛ ስራን ከቤት የመስራት(remote-work) ልምድ እንዲያዳብር ማድረጉ ነው።
Remote Work ጋር ተያይዘው ከመጡ መልካም ጉዳዮች አንዱ ከአንድ ስራ በላይ በተመሳሳይ የስራ ሰዓት መስራት ሲሆን አብዘሀኛው በ IT ዘርፍ የተሰማሩ ሰራተኞች የዚህ መልካም እድል ተጠቃሚዎች ናቸው።ተመሳሳይ አይነት privilege በሚሰጥ ሌላ የስራ ዘርፍ ላይ የተሰማሩም ሰራተኞች የዚህ መልካም እድል ተጠቃሚዎች ናቸው።
Over Employment ሁለትና ከሁለት በላይ ስራን መስራት የራሱ የሆነ መልካም ጎኖች ቢኖሩትም የራሱ የሆነ መልካም ያልሆኑ ገጾችም አሉት።
ከመልካም ጎኖቹ ስንጀምር
ከአንድ በላይ ስራን በመስራት ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ማግኘት የሚቻል ሲሆን ይህም የፋይናንስን ግቦችን ለማፋጠንና ከፍተኛ የሆነ የፋይናንስ ደህነንት ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል።
በተለያየ ድርጂት መስራት በአጭር ግዜ የተለኣይዩ ክህሎቶችን እንድሳድግና ባለብዙ ክህሎቶች እንድሆን ያደርጋል።
ከአንድ በላይ ስራን በመስራት የስራ ደህንነትን ይፍጥራል በዚህ ባልተራጋጋ ኢኮኖሚ ሁለት ስራ ቀርቶ አብዘሀኛው ወጣት አንድም ስራ ባጣበት ዘመን ከአንድ በላይ ስራን መስራት የተረጋጋና ከስጋት ነጻ የሆነ ኑሮ ለመምራት ይጠቅማል።
ከአሉታዊ ገጾቹ መካከል አብዘሀኛው ሰው ቅንጦት አድርጎ የሚያስበው የስራና የግል ህይዎት(work-life balance) ሚዛን መሳትና በከፍተኛ የስራ ጫና የሚመጣ ድካም ዋናወቹ ናቸው።
አንድ ስራ ብቻ መስራትን ስራ መፍታት የሚመስላቸው የስራ ባልደረቦች አሉኝ እዚህ ደረጃ የሚደረሰው ጠንካራ የሆነ የ ሰዓት አጠቃቀምና የለት ተለት ስራን አቅዶ የመስራትን ክህሎት በማዳበር እንዲሁም ከፍተኛ የስራ ጫና ዉስጥ ሁኖ ስራን ማከናዎን ልምድን በማዳበር ነው
@mohammedBurahaba