ቢስሚላህ
ጠዋት 2:12 ነበር ቦታው የተገኘነው
ከሱፍዩ ጀመዓ ሸይሆቹም ጭምር በጊዜ ቦታ ቦታቸውን እየያዙ ነው
እስከ 3:45 ማንም የወሀብይ ተወካይ አልተገኘም
ከ3:45 በኋላ አንዲት ሴትና አንድ ወንድ ገቡ
የሱፍይ ሸይሆች መጥተዋል ቦታቸውን ይዘዋል
4:10 ገደማ ሌላ 2 ወሀብይ ገቡ
ከ4:15 በኋላ በነመሐመድ አባተ የተመራ ቡድን ተንጋግቶ ወደአዳራሽ ገባ
ከሱፍዩም ከወሀብዩም ጥሪ የተደረገላቸው 40:40 ሰዎች ነበሩ ግና ስም ቼክ ሲደረግም ቆጠራ ሲካሄድም የወሀብይ 53 አለፈ
3 ጊዜ የ'ኛ ሰዎች እኒህ ናቸው እያሉ ወረቀት ቀያይረዋል
ውይይቱ ሳይካሄድ 6:00 ሰዓት አለፈ
በዚህ መሀከል ሸይህ ቃሲም ታጁዲን ይቅርታ አድርጉልንና ሁላችሁም ውጪ ውጡና ስም እየተጠራ ይግባ ተባለ
ሁሉም ወደውጪ ወጣና እየተጠራ ገባ
ሌላው ውጪ እንዲቆይ በርም ተቆለፈ
ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሀጅ ዑመር እድሪስ ወደ አዳራሹ ገቡ
ሸይህ ቃሲም ታጁዲን የመግቢያ ንግግር አደረጉ
የዛሬው ዓላማችን በልዩነት ነጥቦች ላይ መወያየት ነው ፣ ሌላ አጀንዳ የለንም አሉ
ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሀጅ ዑመር እድሪስ በልዩነቶች እንጂ በሌላ አንወያይም የሚል ሐሳብ አቀረቡ
ዶ/ር ጄይላንም ዛሬ የተገናኘነው በልዩነቱ ለመወያየት ነው አሉ
ከወሀብያ በኩል መነጫጭ ተፈጠረ
እጅ እያወጡ ሓሳቦችን መሰንዘር ጀመሩ
ግማሹ በልዩነት ሓሳቡ እንወያይ ፣ አይ አይሆንም በመተዳደሪያ ደንቡ ነው ምንወያየው የሚሉ ሃሳቦች መነሳት ተጀመረ
ዶ/ር ጀይላን መጀመሪያ ላይ በልዩነቱ ላይ እንወያይ አሉ ቀጠሉና ምንም የልዩነት ሓሳብ የለንም/አላዘጋጀንም/ አንድ ወገን ብቻ ነው ያዘጋጀው ብለው ዋሹ
ሸይህ ቃሲም ታጁዲን ይኸው ያቀረባችሁት የልዩነት ሓሳብ በአረብኛ የተፃፈ ሀርድ ኮፒም ሲዘዋወር የነበረ ሶፍት ኮፒውም ደርሶናል ብለው አሳይዋቸው
ወደ ውይይቱ ይገባ የሚል ዕንድምታ በቤቱ ተወሰነ
ዶ/ር ጀይላን ውይይቱን እኔም ሀጂም አይመሩትም ገለልተኛ ወገን ነው መምራት ያለበት አሉ
ይህንን ንግግር አድርገው እንኳ አልጨረሱም አዳራሹ አላሁ አክበር በሚል ድምፅ ተረበሸ
በትልቅ ጩኸት በሚረብሽ ድምፅ አላሁ አክበር እያለ ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሀጅ ዑመር እድሪስን ለመምታት ወደፊት ተንደረደረ (ኩራባቸው)
የወሀብያ ሰዎች ሁሉም ብድግ ብድግ አሉ
ኩራባቸው የተባለው ጎረምሳ ከሁሉም ጀርባ ነበር የተቀመጠው ከገባበት ሰዓት ጀምሮ እየረበሸ እያዋከበ በአደብ አልቀመጥ እያለ እያስቸገረ ነበር (ተወያይ ነኝ ብሎ ገብቶ የእንግዳ ወንበር ላይ አልቀመጥም በማለት ነበር ከኋላ የተቀመጠው)
ማን ማንን እንደያዘ መለየት በማያስችል ሁኔታ ግርግር ተፈጠረ
ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሀጅ ዑመር እድሪስ ብድግ ብለው ሊወጡ ሲሉ እንዳይወጡና ውይይቱ እንዲካሄድ ተብሎ ቁጭ እንዲሉ ሸይህ ቃሲም ታጁዲን አረጓጓቸው
ኩራባቸውን ይዘው አስቀመጡት
ግርግሩ ግን ሊቆም አልቻለም
በዚህ መሀከል የተቀዳሚ ሙፍቲህ ሀጅ ዑመር እድሪስ ጥበቃዎች (ደህንነቶች) ይዘዋቸው ሊወጡ ተነሱ
ይሄኔ ኩራባቸው የተባለው ግለሰብ ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሀጅ ዑመር እድሪስን ሊደበድብ ያዙት ያዙት እንዳይወጣ ለምን ይወጣል እያለ ወንበር አነሳ አገላጋይ ያዘው በፍፁም እምቢ አለ ጩኸቱ ተበራከተ ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሀጅ ዑመር እድሪስ ይዘዋቸው ከአዳራሽ ወጡ
በብዙ ልመናና ኡኡታ አዳራሹ ፀጥ እንዲል ተደረገ
ሸይህ ቃሲም ታጁዲን ዝሁር ሰግደን ምሳ በልተን እንምጣ ብለው ተወጣ
ምሳ አቀርባለሁ ብሎ የነበረው አቡበከር አህመድ ነበር አላቀረበም
ምሳ ለማቅረብ የተስማማው ውይይቱ ሆቴል ቢሆን እንደነበርና እሱ ሲጠበቅ ተቋሙ ምሳ ለማቅረብ የዘገየ መሆኑ ተገለፀ
ምሳ ሳይበላ ተገባ
የተለያዩ ሃሳቦች ከሁለቱም ወገን ተነስተዋል ነገር ግን በዚህ ስሜታዊነት ውይይት እንደማይካሄድ ታመነበት
ውይይቱ መቋረጡንና ሌላ ጊዜ እናሳውቃለን ብለው ሸይህ ቃሲም ታጁዲን አቀረቡ
በዚህ ተጠናቀቀ