Forward from: ዓለም ከመልእክታቱ አንፃር...
🟢🟡🔴
ኅዳር 25 | #ቅዱስ_መርቆሬዎስ ሰማዕትነት ተቀበለ።
#ቅዱስ_መርቆሬዎስ ስሙ ፒሉፓዴር (ፒሉፓተር) ይባላል። ትርጉሙም "የአብ ወዳጅ" ማለት ነው። በኋላ ሊቃውንት መርቆሬዎስ አሉት። መርቆሬዎስ ማለት ገብረ ኢየሱስ ክርስቶስ (የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ) ነው።
የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ደግሞ ለሰማዕቱ ያላቸውን ፍቅራቸውን ጨምረው አቡ ሰይፊን (Abu Seifin- ባለ ሰይፉ አባት) ይሉታል።
ቅዱስ ገብርኤል በርበሮችን እንዲያጠፋ ከንጉሥ ዳኬዎስ ጋር ሲዘምት ሰይፍ ያቀዳጀው፣ ገጸ ከልብ (ፊቱ የውሻ፣ መኻሉ የሰው፣ እግሩ የአንበሳ፣ ታቹ የጋለ ነሐስ የሆነ ፍጡር) ጓደኛው የሆነ፣ እርሱ ሰማዕት ከሆነ በኋላ ጥቁሩ ፈረሱ ወንጌልን የሰበከ ቅዱስ ነው።
ከበርበሮች ጋር ጦርነቱ በእግዚአብሔር ኃይል ከተፈጸመ በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረግ በዓልን ሊያደርግ ወደደ። ቅዱስ መርቆሬዎስ ግን አብሮት አልወጣም ወደ ቤቱ ሔደ እንጂ። በዚያንም ጊዜ ንጉሥ መልእክተኞችን ልኮ ቅዱስ መርቆሬዎስን ወደርሱ አስመጥቶ ለአማልክት ዕጣን አሳርግ እና ስገድ አለው።
በዚያንም ጊዜ ትጥቁንና ልብሱን ወረወረለትና ንጉሡን እንዲህ አለው፦ "እኔ ክብር ይግባውና ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክደውም! ለረከሱ ጣዖታትም አልሰግድም።"
ንጉሥ ዳኬዎስም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ። እርጥብ በሆኑ የሽመል በትሮች እንዲደበድቡት አዘዘ። ሁለተኛም ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ ይገርፉት ዘንድ አዘዘ።
በዚያንም ጊዜ የአገር ሰዎች ስለ ቅዱስ መርቆሬዎስ እንዳይነሡበት ፈርቶ ወደ ሆነች ወደ ቂሣርያ በብረት ማሠሪያ አሥሮ ላከው። በዚያም እንዲአሠቃዩት አዘዘ።
ከአሠቃዩትም በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ እንዳዘዘ ራሱን በሰይፍ ቆረጡትና ተጋድሎውን ፈጽሞ በመንግሥተ ሰማያት የሕይወት አክሊልን ተቀበለ።
◦◦🌿◦◦
T.me/Ewnet1Nat