የአለልኝ አዘነ ግድያ ተጠርጣሪዎች ፍርድቤት ቀርበዋል።
በቀን 5/2/2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት እንደተገለጸው (የገዛ ባለቤቱ) ሆን ብላ እቤት ውስጥ ያለውን ንብረት በመሰባበር ስልክ ደውላ በቅጽል ስሙ (ሉንጎ ) የተባለውን ተጠርጣሪ መጥራቷን ችሎቱ አስረድቷል ። (የቀድሞ የአርባምንጭ ከተማ ከንቲባ ቦዲ ጋርድ እና የእህቱ ባልም ጭምር ነው ) ።
ተጠርጣሪው ግለሰብ ከመጣ በኋላ ስልኩን ቀምቶ ወስዶ እቃ ለምን ሰበርክ ብሎ በመጠየቅ መደብደብ ሲጀምር ሟች ሮጦ በአጥር በመውጣት ከቤት ቢያመልጥም የገዛ ባለቤቱ ተከተለው ብላ በነገረችው መሠረት ተከትሎት ሄዶ የአንገት አጥንቱን በመምታት ከገደለ በኋላ ለማስመሰል በአቅራቢያ ባለው ስልክ እንጨት ላይ መስቀላቸውን የሚገልጽ በቂ የሰውና የሰነድ ማስረጃ ማግኘቱን ፍርድቤቱ በዋለው ችሎት አሳውቋል።
ፍርድ ቤቱ ቀጣይ በቀን 21/02/207 ዓ/ም የሰው ማስረጃ ለመስማት ቀጠሮ መያዙንም አሳውቋል።
በምርመራው ሂደት የምርመራው ቡድን አባላት ጠንካራ ፣ ፍታዊ እና ከፍተኛ ኃላፍነት የተሞላ የምርመራ ሂደት ማድረጋቸው ለዚህ ውጤት መገኘት መነሻ እንደሆነም ተጠቁሟል ።