✍
እንዲህ ተተርኳል........
ሁሌም ፈጅር ላይ እየጮኸ ሰፈርተኛው የሚቀሰቅስ አንድ አውራ ዶሮ ነበር። ከዕለታት በአንዱ ቀን የዶሮው ባለቤት ወደ ዶሮው ይመጣና....
"ጠዋት ጠዋት ድምፅህ በጣም እየረበሸኝ ነው; ወይ መጮህ ታቆማለህ አልያም ትታረዳለህ" ይለዋል።
አውራ ዶሮው ከራሱ ጋ ቲንሽ ከተወያየ በኋላ....
"ለደሩራ ሲባል እኮ የተጠላ ነገርም ይሰራል፤ ለእኔም መስለሀዉ ከአቋሜ ቲንሽ ለቀቅ አድርጌ ሕይወቴን ባተርፍ ነው፤ ደግሞም እኔ ዝም ብል እንኳ ሰዉን የሚቀሰቅሱ ሌሎች አውራ ዶሮዎች አሉ።" በማለት ጩኸቱን ለማቆም ተስማማ።
በዚሁ ስምምነት ወራቶች አለፉ። ባሉካው በድጋሚ ወደ አውራ ዶሮው መጣና.....
"በሕይወት መኖር ከፈለክ እንደ ሴቷ ዶሮ ታስካካለህ; ካልሆነ መታረድህ ነው" አለው።
አውራ ዶሮው አሁንም ቲንሽ ካሰበ በኋላ የባለፈውኑ ውሳኔ ደገመው።
"ይህም ጊዜ ያልፋልና በሕይወት መኖሬ የተሻለ መስለሀ አለው" በማለት, ያልኖረበት ያልተፈጠረበት የሆነው ባህሪ ተለማምዶ ማስካካት ጀመረ።
በዚሁ መልኩ ወራቶች አለፉ። ሰውየው ግን አላረፈም፡ አሁንም ወደ አውራ ዶሮው በመምጣት......
"መኖሮ የምትፈልግ ከሆነ እንደ ሌሎች ዶሮዎች ዕንቁላል ልትጥል ነው; ካልሆነ ለእርድ ተዘጋጅ" አለው።
የዛኔ ነበር አውራ ዶሮው ሴራው ጥንሰሳው የተረዳው። በዚሁ ጊዜ ታሪክ የማይረሳው የፀፀት ቃሉ ተናገረ........
"ምን ነበር ማንነቴን ሳልለቅ እየጮህኩ በተገደልኩ!!"
እንዲህ ነው ሚያደርጉህ.......
ቀስ...በቀስ ቀስ...በቀስ አሽመድምደው አሽመድምደው ማንነትህን ክብርህን ያስለቅቁህና ዋጋ ቢስ በሆንክ ጊዜ ይቀነጭሩሃል።
"ይህም ጊዜ ያልፋል ልታዘዛቸው" ብለህ ብታጎነብስ ሚያልፍብህ ስቃይ እንጂ ሚያልፍልህ ጊዜ አለመኖሩን አውቀህ በማንነትህ ላይ ፅና።
ትጠነክር ዘንድም ፅና!!
ኮፒ
https://t.me/Abueshek/9529https://t.me/Abueshek/9529