የትውልድ ቦታየ የዳዴ መንደሬ፡
የኔነት ግርማ ነሽ አውቃለው ሀገሬ፡
አንች የዋህ ነበርሽ ግና ምን ያደርጋል፡
አንዳንድ ልጂሽ ነኝ ባይ እንደ እሾክ ይዋጋል፡
እራስ ወዳድነት እንዲህ ተንሰራፍቶ፡
ቦርጩ ራሱ ሆኖ ሆድ ህሊናን ገዝቶ፡
ነፃ ስንወጣ ከጭቆና ቀንበር፡
ያኔ ያኗኗረን ፍትህ እንደነበር፡
አንባገነኖቹ አፄወች ሳይገዙን፡
አሐዳዊ ሆነው መጥተው ሣይበርዙን፡
ኩፋር ሁኑ ብለው ሣይገድሉን በስተፊት፡
መከባበር ነበር ያንች ግሩም ትውፊት፡
የነጃሽይ ሰንደቅ የዒማም አህመድ ሀገር፡
የጀግና መፍለቂያ የፍትህ መነፀር፡
የያኔው ደግነት ልቤ ላይ ተቀርፆ፡
የሰውነት ሚስጥር ባንደበቴ ሰርፆ፡
ወደፊት ተራምደን ያኔ ላይ በወጣን፡
ዳግም እንደገና ፍትህን ባመጣን፡
ሁሉም በቀረብን ውሀችን በጠጣን፡
Nur
የኔነት ግርማ ነሽ አውቃለው ሀገሬ፡
አንች የዋህ ነበርሽ ግና ምን ያደርጋል፡
አንዳንድ ልጂሽ ነኝ ባይ እንደ እሾክ ይዋጋል፡
እራስ ወዳድነት እንዲህ ተንሰራፍቶ፡
ቦርጩ ራሱ ሆኖ ሆድ ህሊናን ገዝቶ፡
ነፃ ስንወጣ ከጭቆና ቀንበር፡
ያኔ ያኗኗረን ፍትህ እንደነበር፡
አንባገነኖቹ አፄወች ሳይገዙን፡
አሐዳዊ ሆነው መጥተው ሣይበርዙን፡
ኩፋር ሁኑ ብለው ሣይገድሉን በስተፊት፡
መከባበር ነበር ያንች ግሩም ትውፊት፡
የነጃሽይ ሰንደቅ የዒማም አህመድ ሀገር፡
የጀግና መፍለቂያ የፍትህ መነፀር፡
የያኔው ደግነት ልቤ ላይ ተቀርፆ፡
የሰውነት ሚስጥር ባንደበቴ ሰርፆ፡
ወደፊት ተራምደን ያኔ ላይ በወጣን፡
ዳግም እንደገና ፍትህን ባመጣን፡
ሁሉም በቀረብን ውሀችን በጠጣን፡
Nur