➡️ ሪያል ማድሪድ ፒየር ኤምሪክ አቡምያንግን ለማዘዋወር ዳኒ ሴባሎስን እና ተጨማሪ ገንዘብ ለአርሰናል እንዳቀረበ ዘገባዎች ጠቁመዋል።
👉 የስፔኑ ጋዜጣ Diario Madridista እንደሚለው፤ መድፈኞቹ ተጫዋቹን በ2021 በጋ በነፃ ከሚያጡት፤ ተጫዋቹን በደና ገንዘብ ለመሸጥ ከወዲሁ ከሎስ ብላንኮሶች ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።
👉 ዘገባው ጨምሮ እንደገለፀው፤ የዚነዲን ዚዳን ቡድን ምንም ያህል አቡምያንግን ቢወዱትም ከሱ ይልቅ ሃሪ ኬንን ወይም እርሊንግ ሃላንድን ቢያገኙ ነው የሚመርጡት።
👉 ይሁን እንጂ ማድሪድ ከቶተነሃሙ ዳንኤል ሌቪ ጋር በጋሬዝ ቤል እና በሉካ ሞድሪች ዝውውር ምክንያት ጥሩ ስሜት ላይ ስላልሆኑ የሃሪ ኬን ዝውውር የሚሳካላቸው አይመስልም፤ ቦርሽያ ዶርትሙንድ ለሃላንድ ሽያጭ የመደበው ብርም የሚቀመስ ባለመሆኑ ማድሪዶች ያላቸው አማራጭ ጋቦናዊው ተጫዋች ብቻ ሆኗል።
👉 SunSport ባለፈው ሳምንት እንደዘገበው ማንችስተር ዩናይትድ በኤምሬት ያለው ውል እያለቀ የመጣውን አቡምያንግን ለማዘዋወር 50 ሚሊዮን ፓውንድ እንዳቀረበ ዘግቦ ነበር።
👉 የ30 አመቱ ተጫዋች በአርሰናል እስከ 2021 የሚያቆየው ኮንትራት ያለው ቢሆንም፤ ተጫዋቹ ውሉን ለማራዘም ምንም አይነት ፍንጭ ስላልሰጣቸው ተጫዋቹን ለመሸጥ እንዲያስቡበት አድርጓቸዋል፣ይሁን እንጂ ማድሪድ፤ አርሰናል ለተጫዋቹ ሽያጭ የሚፈልገውን 50 ሚሊዮን ፓውንድ ላለመክፈል ዳኒ ሴባሎስን የዝውውሩ አካል አድርጎ ለማቅረብ አስቧል።
👉 አቡምያንግ በቅርቡ ስሙ ከባርሴሎና ጋር በተደጋጋሚ የተያያዘ ቢሆንም፤ የአቡምያንግ እናት እንዳሉት ግን ተጫዋቹ ቤርናባው ላይ መጫወት የልጅነት ህልሙ እንደነበር ተናግረዋል። [Via Zena Soccer ]