Ethiopian Electric Utility


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Career


EEU Official Telegram Channel
Web: www.eeu.gov.et

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Career
Statistics
Posts filter


አዲስ ሃይል ፈላጊ ደንበኞች ማሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች

ውድ ደንበኛችን አዲስ ቆጣሪ ለማግኘት ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላችን ሲመጡ ከዚህ በታች የተገለፁትን ቅድመ ሁኔታዎች እንዲያሟሉ እንጠይቃለን፡፡

የነጠላ ፌዝ ቆጣሪ /Single Phase Meter/ ለማግኘት፡-

• የአመልካቹ የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ፣
• አንድ ጉርድ ፎቶ /3 በ 4 የሆነ/፣
• የኪራይ ቤት ከሆነ ከባለቤቱ የተሰጠ የስምምነት ደብዳቤ፣
• ለኃይል ማሻሻያ ወይም ለተጨማሪ ቆጣሪ ከሆነ የኤሌክትሪክ ፍጆታ የመጨረሻ ክፍያ ደረሰኝ፣
• ጥያቄው ለሽርክና ማህበር ከሆነ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ የሽርክና ማረጋገጫ ሰነድ ኮፒ፤

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ሙሉ መረጃውን ለማግኝት ይህን ማስፈንጠሪያ ተጭነው ያንብቡ: -
http://www.ethiopianelectricutility.gov.et/contents/getting-electricity?lang=am

3.8k 0 27 24 20

ከ21 ሺህ በላይ አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በአገር አቀፍ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም 21 ሺህ 104 አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድርግ ችሏል፡፡

በፕሮግራሙ በተጠናቀቀው የመጀመሪያ ስድስት ወራት ውስጥ ተጠቃሚ ከሆኑ አዳዲስ ደንበኞች ውስጥ 6 ሺህ 455 በኦሮሚያ ፣ 6 ሺህ 306 በአማራ፣ 2 ሺህ 374 በትግራይ፣ 288 በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ 64 በጋምቤላ ክልል እና ሌሎች ደግሞ በሌሎች ክልሎች የሚገኙ ናቸው፡፡

ደንበኞችን ኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ 639 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር፣1 ሺህ 61 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር እና 245 ትራንስፎርመር ተከላ ስራ ተከናውኗል፡፡

በተመሳሳይ በዋናው የኃይል ቋት እና በፀሐይ ኃይል ምንጭ የገጠር ከተሞችን በማገናኘት አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡

ተቋሙ ከዋናው የኤሌክትሪክ መረብ ርቀው በገጠሩ የሃገራችን ክፍል የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን አማራጭ የሃይል ምንጮችን በመጠቀም ኤሌክትሪክ ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


በአዲስ አበባ እና ጋምቤላ የቅድመ ጥገና ሥራ ለማከናወን ሲባል በዕቅድ ኃይል የሚቋረጥባቸውን ቦታዎች ለማወቅ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡-http://www.eeu.gov.et/power-interruption?lang=am


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ተግባራዊ እየተደረገ ሚገኘው የአሰራር ስርዓት ማሻሻያ እና ለደንበኞች የሚኖረው ጠቀሜታ !!


የሃላላ ኬላ ሎጅ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆነ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞን በሎማ ቦሣ ወረዳ የሚገኘው ሃላላ ኬላ ሎጅ በ140 ሚሊየን ብር ወጪ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ እንዲሆን መደረጉን የደቡብ ምዕራብ ሪጅን ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ገብረ ገለፁ፡፡

የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል የሆነዉን የቱሪስት መዳረሻ ተጠቃሚ ለማድረግ የ36 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር ዝርጋታ፣አንድ ባለ 800 ኪ.ቮ.አ ኮምፓክት ትራንስፎርመር ተከላ እንዲሁም አንድ የኤ.ኤም.አይ ስማርት ቆጣሪ መገጠሙን ተናግረዋል፡፡

የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታውን በ6 ወራት በማጠናቀቅ ከጥር አጋማሽ ጀምሮ የቱሪስት መዳረሻው የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡

የሃላላ ኬላ የቱሪስት መዳረሻ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ዝርጋታ ወጪ የተሸፈነዉ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መሆኑን ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


በአዲስ አበባ ከተማ የቅድመ ጥገና ሥራ ለማከናወን ሲባል በዕቅድ ኃይል የሚቋረጥባቸውን ቦታዎች ለማወቅ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡-http://www.eeu.gov.et/power-interruption/detail/1168?lang=am


ተቋማችንን የሚመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች ያስቀመጥነውን የቲክቶክ አካውንት ማስፈንጠሪያ በመጫን እንድትቀላቀሉ በአክብሮት እንጠይቃለን።
👉https://www.tiktok.com/@ethiopian.electri?_t=8rnUn6BN6uO...
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


በአዲስ አበባ እና ሐረር ከተማ የቅድመ ጥገና ሥራ ለማከናወን ሲባል በዕቅድ ኃይል የሚቋረጥባቸውን ቦታዎች ለማወቅ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡-http://www.eeu.gov.et/power-interruption/detail/1167?lang=am


ውድ #የድህረ_ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኛችን የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ክፍያ ከዚህ በፊት በሚከፍሉበት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ተቋሙ በዘረጋቸው ዘመናዊ የክፍያ አማራጮች ይፈፅሙ!ወርሃዊ የቆጣሪ ንባብ እየተወሰደ መሆኑን ያረጋግጡ! የቆጣሪ ንባብ ካልተወሰደ ለተጨማሪ ውዝፍ እዳ የሚዳርግ በመሆኑ ወቅቱን የጠበቀ ንባብ መወሰዱን ያረጋግጡ፤አለመነበቡን እርግጠኛ ከሆኑ በአቅራቢዎ ለሚገኙ አገልግሎት መስጫ ማዕከል በመሄድ ያሳውቁ፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


በአዲስ አበባ እና ሸገር ከተማ የቅድመ ጥገና ሥራ ለማከናወን ሲባል በዕቅድ ኃይል የሚቋረጥባቸውን ቦታዎች ለማየት ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ፡-http://www.eeu.gov.et/power-interruption/detail/1166?lang=am


ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብዎን በቀላሉ፣ የትም ሳይሄዱ ባሉበት ሆነው ከዚህ በፊት በሚከፍሉበት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ካሻዎ በቴሌ ብር፣ በሲቢኢ ብር፣ በሞባይል ባንኪንግ፣ በአዋሽ ብር ፕሮ ወይም በኤም ፔሳ በኩል ይፈፅሙ፡፡

ፍጆታዎ በስልክዎ! ዘመናዊ የክፍያ አማራጭ በመምረጥ ኑሮዎን ያቅሉ!

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


በኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት የኃይል አቅረቦት ተቋርጧል

በነቀምቴ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ትራንሰፎርመር ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት በነቀምቴ ከተማና አካባቢው፣ በወለጋ ዩኒቨርሲቲ፣ በኢትዮ ቴሌኮም ዋና ጣቢያ፣ በአርጆ አዉራጃ ከተማ እና አካባቢዎቻቸው የኃይል አቅርቦቱ ተቋርጧል፡፡

ስለሆነም በኃይል ማከፋፈያ ትራንሰፎርመሩ ላይ የተፈጠረው ብልሽት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል በኩል ተጠግኖ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ ክቡራን ደንበኞቻችን በትዕግስት እንድትጠብቁ በአክብሮት እንጠይቃለን።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


#የጨረታ ማስታወቂያ


የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በግንባታ ላይ በሚገኘው የቴክኖለጂ ልህቀት ማዕከል የሚገኝ ድንጋይን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች ማስታወቂው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡


#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


ለግንባታ ሥራ የተነሱ ዜጎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ሊሆኑ ነው

በአዳማ ከተማ ቁጥር 2 የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ ሲከናወን የተነሱ አራት መቶ አባወራዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ሊደረጉ መሆኑን የአዳማ ሪጅን ዳይሬክተር አቶ ጠሃ አህመድ ገለፁ፡፡

የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያገኙት በአዳማ ከተማ አስተዳደር በቶሌ እና ዋጩ ለፋ ቀበሌዎች የሚገኙ ነዋሪዎች መሆናቸውን ጠቅሰው በአሁኑ ሰዓት የመስመር ዝርጋታ ስራ እየተጠናቀቀ ነው ብለዋል፡፡

በተከናወነው ሥራ 17 ነጥብ 5 የዝቅተኛ እና 3 ነጥብ 5 የመካከለኛ ቮልቴጅ የኤሌክትሪክ ሽቦ መዘርጋቱን ተናግረዋል፡፡

አክለውም 3 ባለ 200 ኪ.ቮ.አ እና አንድ ባለ አንድ መቶ ኪ.ቮ.አ ትራንስፎርመር መተከሉን ጠቅሰው ነዋሪዎቹ እስከ የካቲት ወር አጋማሽ ኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል፡፡

የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ዝርጋታውን ለማከናወን 24 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገ ሲሆን ወጪውም በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መሸፈኑን አብራርተዋል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


በአዲስ አበባ እና ሸገር ከተማ የቅድመ ጥገና ሥራ ለማከናወን ሲባል በዕቅድ ኃይል የሚቋረጥባቸውን ቦታዎች ለማየት ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ፡-
http://www.eeu.gov.et/power-interruption/detail/1164?lang=am


የሥራ ማስታወቂያ

11.8k 0 189 32 68

ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ አለመፈፀም ለተጠራቀመ የፍጆታ ሂሳብና ቅጣት የሚዳርግ መሆኑን ያውቃሉ? እንግዲያውስ እንንገርዎ!! ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ አለመፈፀም ለተጠራቀመ የፍጆታ ሂሳብና ቅጣት ይዳርጋል፡፡ ስለሆነም ውድ የድህረ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞቻችን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳባችሁን በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በወቅቱ እንድትፈፅሙ እናሳስባለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


የመታር ሶላር ሚኒ ግሪድ ፕሮጀክት የመስመር ዝርጋታ 98 በመቶ ደረሰ

በጋምቤላ ክልል ኑዌር ዞን ዋንተዋ ወረዳ መታር ከተማ እየተገነባ የሚገኘው የመታር ሶላር ሚኒ ግሪድ ፕሮጀክት የመስመር ዝርጋታ ሥራ 98 በመቶ ማድረስ ተችሏል፡፡

በፕሮጀክቱ 2.1 ኪ.ሜ የመካከለኛ፣ 17 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ እና የ4 ትራንስፎርመር ተከላ ስራ የተከናወነ ሲሆን የሶላር ሚኒግሪድ ግንባታ አጠቃላይ ግንባታ 40 በመቶ ደርሷል፡፡

እየተጠናቀቀ የሚገኘው የመስመር ዝርጋታ 20 ሚሊየን ብር በጀት የተመደበለት ሲሆን ለኃይል ማመነጫ ግንባታው ደግሞ 532 ሺህ 682.74 ዶላር እና 7 ሚሊየን 231 ሺህ 714 ብር በጀት ተይዞለታል፡፡

የፕሮጀክቱ ግንባታ እየተከናወነ የሚገኘው ሲ.ኢ.ቲ እና ኤን.አር በተባሉ ሁለት የቻይና ኮንትራክተሮች አማካኝነት ሲሆን ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ እስከ 250 ኪሎ ዋት ኃይል የሚያመነጭ ይሆናል፡፡

የፀሐይ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቱን ቀሪ ሥራዎች በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ለማብቃት ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በአካባቢው የሚገኙ የጤና ተቋማት፣ የእርሻ ማዕከላት፣ ትምህርት ቤቶች፣ ወፍጮ ቤቶች፣ የውሃ ተቋማትና ሌሎችም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ያስችላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


በመኖሪያ ቤት የኤሌክትሪክ ኃይል እንዴት በቁጠባ መጠቀም ይቻላል?

የመብራት አምፖሎች አጠቃቀም

• ቀን ቀን መብራት አለማብራት፤ በቀን ክፍለ ጊዜ የፀሐይ ብርሃንን መጠቀም፤
• በማንኛውም ጊዜ ክፍላችንን ለቀን ስንወጣ በመብራት ላይ ያሉ መብራቶችን ማጥፋት፤
• ከኢንካንድሰንት አምፖሎች ይልቅ የኤልኢዲ አምፖሎችን መጠቀም፤
• ፍሎረሰንት አምፑል ከተባላሸ ባላስቱን መንቀል ወይም መጠገን ምክንያቱም ባላስት ከሚመጣው ሀይል እስከ 30% የሚሆነውን ስለሚያባክን፤
• ከማግኔቲክ ባላስት ይልቅ ኤሌክትሮኒክ ባላስት ፍሎረሰንት አምፖል በመጠቀም የሚባክን ሀይል መቀነስ፤
• የአምፖሎችን ፅዳት መከታተል፤

የፍሪጅ አጠቃቀም

• ፍሪጅ የሚገቡ ምግቦች ትኩስ መሆን የለባቸውም፤
• የፍሪጅ ጋስኬት በደምብ መዘጋቱን ማረጋገጥ፤
• ከማብሰያ ምድጃዎች እና ከግርግዳ ጋር አለማስጠጋት
• ቀጥታ ፀሐይ ከሚያስገቡ መስኮቶች ወይም በሮች ፊት ለፊት አለማስቀመጥ፤
• ቴርሞስታቱን ትክክለኛው ቁጥር ላይ ማድረግ (medium range)፤
• በረዶ ከያዘ ቶሎ ማስወገድ፤
• ከሚፈለገው የቅዝቃዜ መጠን በላይ አለማቀዝቀዝ፤
• ማቀዝቀዣዎች በተቻለ መጠን ሙሉ ሆነው እንዲያቀዘቅዙ ማድረግ፤
• የማቀዝቀዣዎችን በር በተደጋጋሚ አለመክፈትና በትክክል መዘጋቱን ማረጋገጥ፤

ለምጣዶችና ምድጃዎች

• የማይክሮዌቭ ኦቭን ማብሰያዎችን መጠቀም፤
• ምግብ በሚያበስሉበት ወቅት ማብሰያውን በትክክል መዝጋትና ቶሎ ቶሎ አለመክፈት፤
• ምግብ ሲያበስሉ 5 ደቂቃ ቀደም ብለው ምድጃውን ማጥፋት፤ ምድጃው በያዘው ሙቀት ቀሪውን ማብሰል ስለሚቻል፤
• ምግብ ለማብሰል ሲዘጋጁ ምድጃውን ለማጋል ከ5 ደቂቃ ላነሰ ጊዜ ብቻ ያብሩ፤

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

9.2k 0 76 27 32
19 last posts shown.