“በአንድነት ለጋራ ዓላማ መቆም ተግዳሮቶችን ለመሻገር እንዲሁም ለሀገር ዘላቂ ብልጽግናን ለመገንባት አቅም ይሆናል” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
*********
በአንድነት ለጋራ ዓላማ መቆም ተግዳሮቶችን ለመሻገር እንዲሁም ለሀገር ዘላቂ ብልጽግናን ለመገንባት አቅም ይሆናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በባህርዳር ከተማ በተካሄደው የአማራ ክልል የጸጥታ ኃይሎች የእውቅናና የምስጋና መርሀ ግብር ላይ ተገኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግርም በአሁኑ ወቅት የሁሉም ክልሎች ልዩ ሀይሎች በተሻለ አቋምና ብቃት ላይ ይገኛሉ፤ የእነዚህ ሀይሎች የተሻለ ብቃትትና አቋም ላይ መሆን የኢትዮጵያን ሰላም አንድነትና ህልውና ዋስትና ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ጠላቶች ይህንን ሳይረዱ ኢትዮጵያዊያን በብሄር፣ በቋንቋ፣ በሀይማኖት በፖለቲካ ተከፋፍለዋል በሚል የተሳሳተ ስሌት ስህተት እንዳይፈጽሙ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ያሳሰቡት።
በዛሬው እለት የተሰጠው ሽልማት የህይወት እና የደም ዋጋ ለከፈሉ እንዲሁም በገንዘብና በእውቀት ለሀገራቸው አስተዋጽኦ ላበረከቱት መላ ኢትዮጵያዊያን የተሰጠም ነው ብለዋል።
https://t.me/esat_television_official