በአዲስ አበባ ከቱርክ መጣ የተባለው ሶፋ ከነ ሙሉ የማዕድ ጠረዼዛ 4.5 ሚሊዮን ብር ይሸጣል።እቃዎቹ ዋጋ የወጣላቸው የብር የመግዛት አቅም በገበያው እንዲመራ ከተወሰነ በወኃላ ከውጭ የገቡ ናቸው።
በዚህ የገበያ ማዕከል 12 ካሬ ምንጣፍ 53,000 ብር ይሸጣል።
በዲዛይኑ፣ በደረጃው ተመሳሳይ ነው የተባለ 6 ካሬ ምንጣፍ ደግሞ 38,000 ብር ይሸጣል።
ይህን ለመረዳት ሰሞኑን በአዲስ አበባ በአንደኛው የገበያ ማዕከል ዘለቅን።
በገበያው ማዕከል የተለያዩ የመኖሪያ ቤት እቃዎች፣ ፈርኒቸሮች ገዥያቸውን የሚወስዳቸውን ተዘርግተው እየጠበቁ ተመለከትን።
ወደ ሽያጭ ባለሞያዋ ቀርበን ዋጋዎቹን፣ አይነቶቹን ጠየቅን።
በዚህ መሰረት አንድ ሶፋ ከነ ሙሉ የማእድ መመገቢያ ጠረዼዛ (ዳይኒንግ ቴብል) የሚሸጠው 4.5 ሚሊየን ብር መሆኑን ተነገረን።
ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?
ለመድሀኒት፣ ለነዳጅ፣ ለፋብሪካ ጥሬ እቃ መግዣ በብዙ ዶላር የምትፈልገው ሀገር በአንድ በኩል ቅንጡ የሚባሉ እቃዎች መግዣ ሲሆን ዶላር ስትቸገር አይታይም።
እንዴት ያለ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ቢኖር ነው ይህ መሳይ ገበያ በአዲስ አበባ የሚታየው?
ከውጪ የሚገቡ እቃዎች በምን መሳይ የውጭ ምንዛሪ ግኝት LC አልፈው ወደ ሀገር ውስጥ ይገባሉ?
ከቱርክ ገባ የተባለው የ4.5 ሚሊየን ብር ሶፋ በተመለከተ የገበያውን ቅኝትና የባለሞያ ሀሳብ አካተን ጠይቀናል።
@ethio_mereja_news@ethio_mereja_news