በአለም ላይ ትልቁ ባለስልጣን እራሱን የሚቆጣጠር ነው
አህያው ዛፍ ስር ታስሮ ነበር። በአጋጣሚ ሰይጣን መጣና አህያውን ከታሰረበት ፈቶ ለቀቀው። አህያውም ወደ ማሳው እየሮጠ ገብቶ ሰብሉን ማውደም ጀመረ።
ይህን ያየችው የገበሬው ሚስት አህያውን በጥይት መታችው። የአህያው ባልተቤት ተበሳጨና የገበሬውን ሚስት ገደላት። ገበሬው መጣና ሲያይ ሚስቱ ሙታለች። ወዲያው አጸፋውን መለሰና የአህያው*ን ባለቤት ተኩሶ ገደለ*ው።
የአህያው ባልተቤት ሚስት ልጆቿን ጠራችና የገበሬውን ቤት እንዲያቃጥሉ አዘዘቻቸው። ልጆቹም አመሻሹ ላይ እናታቸው ያዘዘቻቸውን ለመፈጸም ገበሬውም በውስጥ ሲቃጠል እያሰቡ በደስታ ሄዱ። ወዲያውም ቤቱን አቃጥለው ተመለሱ። እንዳጋጣሚ በሚያሳዝን ሁኔታ ገበሬው እቤት አልነበረምና ተመልሶ መጥቶ የአህያ*ውን ባልተቤት ሚስትና ልጆቹን ገድሎ ተመለሰ።
ሲመለስ ግን ሰይጣንን መንገድ ላይ ያገኘዋል። ገበሬው ትንሺ ሰከን ሲል የሆነውን አስታውሶ ነበርና ሰይጣንን ይህ ሁሉ እንዴት ሊሆን እንደቻለ ይጠይቀዋል? ሰይጣንም እንዲህ አለ፦ እኔ ምንም አልሰራሁም። አህያው*ን ብቻ ነው የፈታሁት። ግን ሁላችሁም የውስጣችሁን ሰይጣን ፈታችሁት። ሁሉንም ነገር ያደረጋችሁት እራሳችሁ ናችሁ።
ሌላ ጊዜ ለምንም ነገር ምላሺ ከመስጠታችን ፣ ውሳኔወችን ከማሳለፋችን በፊት ለአፍታ ቆም ብለን ማሰብ ይኖርብናል። ብዙጊዜ ሰይጣን የሚያደርገው ውስጣችን ያለውን አህያ መልቀቅ ነው። "በአለም ላይ ትልቁ ባለስልጣን እራሱን የሚቆጣጠር ነው!"
SHARE||@ethio_tksa_tks