አፍህን ዝጋ ከማለት...
አዞ ከምድራችን እንስሳት ሁሉ እጅግ ሀይለኛ የመንከስ አቅም ያለው ፍጥረት ነው። ለምሳሌ የሰው ልጅ በመጨረሻ አቅሙ ቢናከስ 162 PSI ( pounds per square inch) የመንከስ ሀይል አለው። አንበሳ ፣ ጅብ ወዘተ 1000 pSI! ይታያችሁ. በዚህ ንክሻ ነው አጥንት የሚሰባብሩት፣ እንስሳትን የሚገነጣጥሉት! አጅሬው አዞ በአንዴ የሚያሳርፍባችሁ ሀይል 5000 Psi ይደርሳል። የአንበሳን 5 እጥፍ ማለት ነው!
የሚገርመው ታዲያ አዞ ንክሻው እንዲህ ሀይለኛ ቢሆንም የመንጋጋ ጡንቻው ደካማ ስለሆነ አፉን እንዳይከፍት ሰው በእጁ አፍኖ ሊይዘው ወይም በተልካሻ ክር ሊያስረው ይችላል። አንዴ አፉን እንደምንም ከከፈተ ግን የተጠጋውን ሰው ይሁን እንስሳ እንጨት ይሁን ድንጋይ ብትንትኑን ነው የሚያወጣው። በሌላ አባባል አዞ አፉን እንዳይከፍት ማድረግ በጣም ቀላልና ትንሽ አቅም የሚጠይቅ ሲሆን፣ ከከፈተ በኋላ ማዘጋት ግን ህይወትን ጭምር ሊያስከፍል ይችላል።
ምን ለማለት ነው? ለራሳችንም ቢሆን አንዴ የከፈትነውን አፍ ለመዝጋት ከመታገል ይልቅ መጀመሪያውኑ አለመክፈት ቀላሉ መንገድ ነው። አፍ ካለነገሩ ከተከፈተ የሌሎችንም የራሳችንንም አጥንትና ሕይወት ካልሰባበረ በቀላሉ አይዘጋም። እንግዲህ ታዘቡ፣ በየሶሻል ሚዲያው በየመድረኩ ጨዋ የሚባሉ፣ የፖለቲካ ፣ የእምነት ወዘተ ሰወች አንዴ አፋቸውን መተሳሳተ መንገድ ከከፈቱ ስንቱን የሞራል አጥንት እንደሚሰባብሩት። ከከፈቱት በሰላም አይዘጋም። ራሳቸውንም ሌላውንም በልቶና አባልቶ፣ ደቀው እና አድቅቀው ወይ እንደከፈቱት ያልፋሉ አልያም ክፍታፍነትን መሳሪያቸው፣ ማስፈራሪያና መኖሪያቸው አድርገውት ይቀጥላሉ።
©አሌክስ አብርሃም
@ethio_tksa_tks