የጥፋት ዘመን.....#share
*ከዮዲት ጉዲት በኋላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ከባዱን ፈተና ያስተናገደችው በግራኝ ዘመን ነው።በግራኝ የተቃጠሉ አብያተክርስቲያናት እና ገዳማት መካከል፦
1.በ1523 ዓ.ም. ሚያዝያ 12 ቀን ደብረ ብርሃን ከተመዋን አውድሞ በዙሪያዋ የሚገኙትን ቤተ ክርስቲያኖች አቃጠላቸው።
2.እንደገብጣን ላይ ዐፄ ልብነ ድንግል ለልጁ ፊቅጦር አሰርቶ የሰጠው ፊቅጦር ቤተ ክርስቲያን አቃጠላት።
3.ዐፄ እስክንድር በይፋት በወርቅና በብር ያሠሯት ቤተ ክርሰቲያን አቃጠላት።
4.ሐምሌ 24 ቀን 1523 ዓ.ም.ግራርያ የሚገኘው ደብረ ሊባኖስ አቃጠለው።
5. በ1524 ዓ.ም ኅዳር 1 ደብረ ሐንታን፤
6.በ1524 ዓ.ም.ኅዳር 2 ደብረ ድማኅን፤
7.በ1524 ዓ.ም.ኅዳር 7 መካነ ሥላሴን፥
8.በ1524 ዓ.ም.ኅዳር 7 ደብረ ነጎድጓድን፥
9.በ1524 ዓ.ም.ኅዳር 7አትሮንስ ማርያም፤
10.በ1524 ዓ.ም.ኅዳር 12 ገነተ ጊዮርጊስን፤
11.በ1524 ዓ.ም.ኅዳር 17 ደብረ ጎልን፤
12.በ1524 ዓ.ም.ኅዳር 19 ታእካ ነገሥትን፤
13.በ1524 ዓ.ም ኅዳር 28 ጋሥጫንና
14.በ1524 ዓ.ም ታኅሣሥ 7 ደብረ እግዚአብሔርን አቃጠላቸው።
15.በ1524 ዓ.ም.ታኅሣሥ 10 ደብረ ሐይቅ እስጢፋኖስን ዘረፏት።
*እነዚህ በወርቅና በብር የተጌጡ፣በስነ-ስእል የተንቆጠቆጡ፣የሀገር ቅርስ የያዙና የዘመኑን የኪነ-ህንጻ አሰራር የሚመሰክሩ አብያተ ክርስቲያናት፣በታላላቅ ሊቃውንቶች የተጻፉና የተተረጎሙ የተለያዩ ብራና መጻሕፍትና የቤተ መንግሥት ንብረቶች እንደ ደመራ እሳት ነደው ቀሩ።
16.ሚያዝያ ወር 1525 ዓ.ም.ላሊበላን በረበሯት።
17.ጥቅምት 1526 ዓ.ም.ወደ አኩስም ሲያቀና ዐፄ ልብነ ድንግል ወደ ደምቢያ፤ ጥቅምት ላይ ወደ ወገራ፤ታህሳስ ወደ ጸለምት፤ጥር 11 ቀን ወደ አኩስም ከዛም ወደ ጸገዴ ሲሸሽ ግራኝ እየተከተለ እግረመንገዱንም ገዳም እያቃጠለ አሳደደው።ግራኝ አኩስም በሄደ ጊዜ በአኩስም አቅራቢያ ባለ ተራራ በፍራቻ የሰፈሩትን 10,550 ክርስቲያኖች በመክበብ ጭንቅላታቸውን በሰይፍ አስቆርጧቸዋል።
18.1526 ዓ.ም.ደብረ ዓባይን አቃጥሎ በገዳሙ ውስጥ የሚኖሩትን 500 መነኮሣት እንደ በግ አርዷቸዋል።
19.ጥር 23 ቀን 1526 ዓ.ም.የአባ ሳሙኤልን ገዳም ዋልድባን አቃጠለው።
20.ኅዳር 19 ቀን 1527 ዓ.ም.ቤተ አምሐራ ላይ ዐፄ ልብነ ድንግልና ስምዖን ባደረጉት ውጊያ ብዙዎች ሞቱ።በዚሁ ዓመት አኩስም፣ሃሌሎ፣በንኮል፣ለጋሶ፣ደብረ ከርቤና ሌሎች ታሪካዊ ገዳማት ተቃጠሉ።ወገራን፥ስሜንን፥ደምቢያን፥በጌምድርን መሪዎቻቸውን ገድለው ተቆጣጠሯቸው፤የጦር ሰፈራቸውንም እዚያ አደረጉ።
21.ግራኝ 1528 ዓ.ም.የጎጃምን ሕዝብ በመደዳ ጨፈጨፈው።
22.ግንቦት 23 ቀን 1529 ዓ.ም.ጣና ደሴት የምትገኘውን ደብረ ገሊላን አቃጠሏት።
23.በ1532 ዓ.ም.ወደ ሲሬ ሄዶ ታኅሣሥ 10 ቀን ምጥባቤላን፣ታኅሣሥ 15 ቀን ጉትማንን መነኩሴዎችን እየገደለ አቃጠላቸው።ጥር ወር ላይ ዛና የሚገኘውን ክብርቶን ቤተ ክርስቲያንን፤የካቲት 13 ቀን ደብረ ከርቤን፤የካቲት 16 ቀን ሽሬ ውስጥ የሚገኘውን ብሳይጢስን ዘርፎ የካቲት 22 ቀን ግሼን ተደፈረች፥ተዘረፈች።
24.ግሼን የአማራ ሕዝብ ታሪክ ዋነኛዋ ማጠንጠንያ ነበረች።ሰሎሞናዊያን ነገሥታት ልጆች የሚመሩባት፤የቤተ መንግሥት ዕቃ የሚከማችባት የንጉሦች አንባ ነበረች።ግራኝ ወደ ኮረብታው ሊወጣ ሲሞክር በድንጋይ ናዳ ለመከላከል ሙከራ ቢደረግም ማስቆም አልተቻለም።ኮረብታው ላይ ወጥተው ልዑላኑን ፈጇቸው።ከይኩኖ አምላክ እስከ ልብነ ድንግል ድረስ የተከማቸውን የወርቅ ዘውድ፣ሥዕል፣የወርቅ ጽዋ፣የወርቅ ጻሕል፣የወርቅ መስቀል፣ግልገል ወርቅ፣የወርቅ ጌጣጌጥ፣የሐር ልብሳልብስ፣መጻሕፍት ወዘተ የዘረፉትን ዘርፈው የማይፈልጉትን አወደሙት።መስከረም 5 ቀን 1533 ዓ.ም.ንጉሥ ልብነ ድንግል አረፈ፤ደብረ ዳሞ ላይም ተቀበረ።
*የይኩኖ አምላክ፥የአቡነ ተክለ ሃይማኖት አገር ኢትዮጵያ ልቧን ተወጋች፤አነባች፤ፀሐይ እያቆለቆለች ምድሪቱ በጽልመት ተዋጠች።የድሆች፥የመነኮሳት ደም በከንቱ ፈሰሰ።ከዋክብትና ጨረቃ ወደቁ የፀሐይም ብርሃኑ ስለጠፋ ጨለመ አሳቢና ጠባቂም ታጣ...ሁሉም ነገር ጨለመ፣ኢትዮጵያ ሥልጣኔ አይታ የማታውቅ አገር ሆነች። #ታደለ ጥበቡ
*Youtube subscribe ያድርጉ።
https://www.youtube.com/channel/UC6m-V3zA2xrlwPPWtXLJ33A