ጥቅሶች


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


የ ፍቅር ጥቅሶች ♥️
የ ናፍቆት ጥቅሶች 😭
የ ህይወት ጥቅሶች ✨
የ ብቸኝነት ጥቅሶች 💔
አስቂኝ ጥቅሶች 😂🤣
ለ Tg Profile 🖼️
ሁሉም አንድ ላይ ምታገኙበት 😊
@nege_jr

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


#ጥሩ ሕይወትን❤ ለመምራት የሚረዱ10 መርሆች✅

🖤ሰውን አትጥላ፤ ልብህን ንፁህ አድርግ።

💚አትጨነቅ፤ በፈጣሪ ተመካ።

💖ቀለል ያለ ኑሮ ኑር።

😊ባለህ ነገር ተደሰት፤

👏በተሰጠህ ነገር አመስጋኝ ሁን።

🤝ብዙ በሰጠህ ቁጥር ብዙ ታገኛለህ።

😁ፈገግታ አብዛ፤ ፈገግታ ሰደቃ ነው።

❤️በፍቅር ኑር፤ ለፈጣሪህ ብለህ ውደድ።

🙏ብዙ ዱዓ/ፆለት ባደረክ ቁጥር ጥሩ ታገኛለህ።

✅እውቀትህን ለሌሎች አካፍል፤
አንድ አባባል ብትሆን እንኳ።

🙏ፈጣሪህን በብዛት አስታውስ፤
ልብህ እርጋታን ታገኛለችና።


🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟

ልወዳትነውመሰል
. """""""""""""""""""""""""
ልወዳት ነው መሰል ልቤ ጠረጠረ
ቀልቤ እኔን ጥሎ እሷ ጋር በረረ
አያት እንዳልነበር እንደ ንፁህ እህቴ
ታዲያ ምነው ዛሬ እንቅልፍ ማጣቴ
አይኗን ካላየው ድብርት ውስጥ መግባቴ
.
ልወዳት ነው መሰል ትናፍቀኛለች
በደቂቂቃ ሲኮንድ ትዝ ትለኛለች
ከሌላ ጋር ሳያት በቅናት ማበዴ
አፈቀርኳት መሰል ወቸው! በል ዘመዴ
.
ልነግራት ስፈልግ የልቤን አውጥቼ
ፍቅሬ እንድትሆን በፅኑ ጓጉቼ
ግን ደግሞ እንደገና እጠራጠራለሁ
እህትነትሽን እንዳላጣ ሰጋሁ…
.
ልወዳት ነው መሰል ልቤ ጠረጠረ
በቃ! እነግራታለሁ በኔ አልተጀመረ።

✍ተፃፈ በ አቤል


🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟


🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏
አንድ ገበሬ የሚወደው ፈረሱ ይታመምበትና ወደ እንስሳት ሀኪም ጋር ይዞት ይሄዳል። ሀኪሙም ፈረሱ ጉረኖ ድረስ በመሄድ በሚገባ መረመረው። ለገበሬውም - "ተላላፊ በሽታ ስላለበት ለሶስት ቀን መድሀኒት እንስጠውና
ካልተሻለው ወደሌሎቹ ፈረሶች እንዳይዛመት እንገለዋለን" ብሎት ሄደ።

ይሄንን ሲያወሩ ፍየል ተደብቃ ሰምታቸው ኖሯል ለፈረሱ እያለቀሰች ያወሩትን ነገረችውና "እንደምንም ብለህ ተነስ!
ያለበዛ ይገሉሀል" እያለች ተንሰቀሰቀች።
የመጀመርያው ቀን ሀኪሙ መጥቶ መድሀኒቱን ሰጥቶት ወጣ። ወድያው ፍየል ለምለም ሳርና አተላ ይዛለት መጣች ና
"እንደምንም ተነስ!" ብላ ተማፀነችው።
በሁለተኛውም ቀን ሀኪሙ ሲመጣ ፈረሱ ምንም ለውጥ አላመጣም መድሀኒቱን ወግቶት እስከ ቀጣዩ ቀን ጠብቆት ካልተሻለው እንደሚገለው ለገበሬው ነግሮት ሄደ።
ይሄን ግዜ ፍየል ለምለም ሳር ፈልጋ ለፈረሱ በማምጣት አፅናናችው። የመጨረሻ ቀን ሀኪሙ ሲመጣ አሁንም ፈረሱ ምንም ለውጥ አላመጣም ይሄን ጊዜ ከገበሬው ጋር ቢገሉት እንደሚሻል በር ላይ ቆመው ሲያወሩ ፍየል ቀስ ብላ ተደብቃ ፈረሱ ጋር ገብታ እየተንሰቀሰቀች-
"በናትህ አኔንም ጓደኛ አታሳጣኝ ካልተነሳህ ይገሉሀል" ብላ አለቀሰች። ፈረሱ በፍየሏ ግፊት ቀስ ብሎ ተነሳ።
ፍየል ደስ አላት። "ጎበዝ አስኪ እሩጥ" እያለች አበረታችው። ፈረሱ በወኔ በፊት
ከሚሮጥበት ፍጥነት በላይ ሮጠ። ይሄን ጊዜ ፍየል በደስታ ጮኸች። ገበሬውና ሀኪሙ የምን ጩኸት ነው ብለው ሲያዩ
ያዩትን ማመነን አቃታቸው።ፈረሱ በሓይል አየሮጠ ነው። ገበሬው በደስታ ብዛት ሀኪሙን አንቆ ሳመው። እረኛውን ጠርቶት "ዛሬ እኔ ቤት ትልቅ ድግስ አለ! ስለዚህ ቶሎ በሉ ፍየሏን እረዱልኝ! ምሳ እዚህ ነው" አለ።

✍አንዱ የሌላው መሰላል ነው። ለአንዱ ሂወት ለሌላው ሞት ነው። ለሀብታም ሂወት የደሀው ችግር ግድ ነው። ለአንዱ ማለፍ የሌላው ውድቀት ወሳኝ ነው።
አለም የምትመራበት ህግ ነው።

🙌መልካም ቀን ቸር ያውለን


ባልና ሚስት ናቸው። ከተጋቡ ጀምሮ ወሲብ ሚባል ነገር
ፈፅመው አያውቁም ። በተለይ ባልየው ፣ ወሲብ ምን ይሁን
ምን ምንም ሚያውቀው ነገር የለም! ። ሚስት በዚህ ነገር ሁሌ
እንደተበሳጨች ነው በቃ ፣ አንድ ቀን ታድያ ሚስት ያላትን
ብልሃት ተጠቅማ ማታ ከሥራ ሲመጣ ፣ በመከራ ወሲብ አደረጉ
ባልዬው በጣም ተመችቶት "አንቺ ይሄ ነገር በጣም ነው
ሚጣፍጠው ባክሽ " ብሎ ሁለተኛውን ደግሞ ተኛ ።
በማግስቱ ማታ የባል አባት በእንግድነት መጣ ።
እራት ቀርቦላቸው ተበላ ተጠጣ ። ከዛ ሚስት እጃቸውን
እያስታጠበች ፣ ባልዬው " ማሬ " ብሎ ጠራት (ወሲብ ካደረጉ
በኋላ ነው ማሬ ብሎ መጣራት የጀመረው) ሚስት "አቤት "












" እስቲ ማታ ካቀመሽኝ ከሚጣፍጠው ነገር ለአባዬም
አቅምሺው ይየው እስቲ " ብሏት እርፍ
😂😂😂😂
ይሄ ባል ነው "አባል" ነው
የተመቸው 👍
⚠️አደራ ስትስቁ ጥርሳቹን ብርድ. እንዳይመታቹ ጠንቀቅ በሉ 😉
እናላቹ እናንተም እስኪ እያቀመሳቹ ኧ 😂😂😂
Join and ቀኑን ሙሉ


‹‹የእራስ ወዳድነት አስተሳሰቦች አነሰም በዛም ለጭንቀት ይገፋፋሉ!››

★★★★★★★★★★★★
:
☞ጭንቀት እና መከራ ትክክለኛ ያልሆነ አስተሳሰብ ውጤቶች ናቸው። ሰው ከውስጣዊ ማንነቱ ጋር አብሮ መሄድ ሲያቅተው፤ በሰብዓዊ ህግ ስር ተገዝቶ መኖር ሲሳነው የመከራን ቀንበር ይሸከማል።
:
↪የጭንቀት ማብቂያው ነፍስን ማጽዳት ፣ እንዲሁም አይምሮን የሚያጎድፉ ነገሮችን ሁሉ ማስወገድ ነው።
:
↪መንፈሱ ንጹህ የሆነ ሰው ጭንቀት አያደፍረውም። ወርቅ ንጹህ ወርቅ እስኪሆን ድረስ በእሳት ይፈተናል እንጂ፤ ንጹህ ወርቅ ከሆነ ባኋላ በእሳት ብናቀልጠው ዋጋ የለውም።
:
↪ልክ እንደ ንጹህ ወርቅም፤ በመንፈሱ ንጹህ የሆነ ሰው በመከራ እና ጭንቀት ከልክ በላይ አይፈተንም።
:
↪ሰው ከአይምሮው ጋር ሰላም ሲኖረው መልካም ሁኔታዎችን በዙሪያው ይፈጥራል፤ ከራሱ ጋር ሰላም መፈጠር ሲሳነው ግን ለመጥፎ አጋጣሚዎች እራሱን ያጋልጣል።
:
↪የትክክለኛ አስተሳሰብ መገለጫ ሰላማዊ መሆን ሲሆን ደስተኛ ያልሆነ ወይም ዝብርቅርቅ ያለ ኑሮ ደግሞ ትክክለኛ ያልሆነ አስተሳሰብ መለያ ነው።
:
↪ሰው የተባረከ፤ ነገር ግን ድሃ ሊሆን ይችላል፤ ወይም ደግሞ የተረገመ ግን ደግሞ ሃብታም
ሊሆንም ይችላል።
:
↪ሰላማዊ ኑሮ እና ባለጸግነት አብረው የሚሄዱት፤ ሃብትን በአግባቡ እና በትክክለኛው መንገድ
መጠቀም ሲቻል ብቻ ነው።
:
↪ከልክ ያለፈ ድህነት እና ከልክ ያለፈ ቅንጦት እርካታ የሌለው ህይወት ተቃራኒ ጥጎች ናቸው። ሁለቱም ለአይምሮ ህመም ይዳርጋሉ።
:
☞አንድ ሰው ትክክለኛ ሁኔታ ላይ ነው ያለው የሚባለው፤ ሃብቱ፤ ጤናው እና ደስታው ተጣጥመው መሄድ ሲችሉ ነው።
:
►ሃብት፣

►ጤናና፣

►ብልጽግና፤ የውጫዊ እና ውስጣዊ ማንነቶች የስምምነት ውጤቶች ናቸው።
:
☞ሰው እንደ ሰው ኖረ የሚባለው፤ ነገሮችን ማማረር ፤ሌሎችን መውቀስ ሲያቆም እና ህይወቱ የሚመራበትን ድብቅ ፍትህ መመርመር ሲጅምር ብቻ ነው።
:
►ወደራሱ መመልከትን ልምድ ሲያደርግ፤ ላለበት ሁኔታ ሌሎችን መውቀሱን ይተዋል።
:
►ውስጡን ያጠነክራል፤ አይምሮውን በጠንካራ አስተሳሰቦች ይገነባል።
:
►ከሁኔታዎች ጋር በጭፍን መጋፋጡን ትቶ፤ እራሱን ለመለወጥ እና በውስጡ ያለውን ድብቅ ሃይል እና ጉልበት ለመፈለግ እንደምክንያት ይጠቀመባቸዋል።
:
✿︵♡︵♥︵♡︵♠︵♡︵♥︵♡︵✿
:
#ውድ አንባቢያን ወዳጆቼ፥
:
√አለም በበላይነት በህግ እንጂ ግራ በመጋባት አትመራም፤ የህይወት መሰረትም ፍትህ ነው፤

√አለምን በመንፈሳዊ መንገድ የሚያስሄዳት ትልቁ ሃይልም በህሊና ላይ የተመሰረተ ትክክለኛ ድርጊት ነው።
:
√ስለዚህ ሰው አለም ትክክለኛ መሆኗን እና አለመሆኗን ለመገንዘብ በመጀመሪያ እራሱ ትክክለኛ መሆን ይጠበቅበታል።
:
√ይህንን ለማውቅ በሚያደርገው ጥረትም፤ እራሱን በትክክለኛ መንገድ ሲያስሄድ ፤ የእሱ መለወጥ በሰዎች እና በሁኔታዎች ላይ እንዴት ተጽዕኖ እንደሚያደርግ ያስተውላል።

☞የዚህ እውነታ ማረጋገጫም በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ አለ። እራስን በመፈተሽ ማረጋገጥም ይቻለል። ለምስሌ፦

➊.አንድ ሰው አስተሳሰቡን ሙሉ በሙሉ ቢለውጥ፤ በህይወቱ ውስጥ የሚከሰተው ፈጣን ለውጥ ያስገርመዋል።
:
➋.ሰዎች አስተሳስብ ተደብቆ የሚቀር ይመስላልቸዋል፤ ነገር ግን በአይምሮ ውስጥ ያለ ሃሳብ ተደብቆ ሊቀር አይቻለውም፤ ወደ ልምድ (ባህሪ) ይለወጣል እንጂ።

➌.ልምድ ደግሞ ሁኔታዎችን እና አጋጣሚዎችን ይፈጥራል።
:
➍.ሰው እንደ ሰው ማሰብ ሲሳነው ደካማ አስተሳሰቡ ወደ መጠጥ ሱሰኛነት፤ ሴሰኛነት የመሳሰሉ የህይወት ልምዶች ውስጥ ይከቱታል። እነኚህ ልምዶች ደግሞ ለበሽታ እና ድህነት የሚያጋልጡ ሁኔታዎችን ይፈጥሩለታል።

➎.የተበከሉ አስተሳሰቦች በሙሉ ግራ በሚያጋባ አኗኗር ይገለጻሉ።
:
➏.በፍርሃት፤ በጥርጣሬ እና በመዋዠቅ ላይ የተመሰረቱ አስተሳሰቦች ፤ ደከማ እና ለውሳኔ የሚከብዱ ባህሪ እና ልምዶችን ሲያስከትሉ፤ እኒህ ባህሪ እና ልምዶች ደግሞ ውድቀትን፤ ድህነትን እና ጥገኝነትን ይፈጥራሉ።
:
➐.የስንፍና አስተሳሰቦች ሰው ንጽህናውን እንዳይጠብቅ እና ታማኝ እንዳይሆን ያደርጉታል፤ ሲቀጥልም ለልመና እና ለጥፋት ያደርሳሉ።
:
➑.የጥላቻ አስተሳሰቦች ለእረብሻ እና ለጦርነት ይዳርጋሉ፤ እረብሻ እና ጦርነት ደግሞ ሰዎች
የሚጎዱባቸውን ሁኔታዎች ይፈጥራሉ።
:
➒.የእራስ ወዳድነት አስተሳሰቦች አነሰም በዛም ለጭንቀት ይገፋፋሉ።

➓.በአንጻሩ መልካም አስተሳሰቦች በመልካም ሁኔታዎች እና አጋጣሚዎች ይገለጻሉ።
:
➊➊.ከክፉ ነገር የጸዳ አስተሳስበ፤ እረጋ ያለ ባህሪ እንዲኖር ሲያደርግ፤ እረጋ ያለ ባህሪ ደግሞ ሰላምን ይሰጣል።
:
➊➋.በራስ መተማመን እና ወኔ ላይ የተገነቡ አስተሳሰቦች ደግሞ ለስኬት የሚያደርሱ ባህሪዎች እንዲፈጠሩ ያደርጋሉ።
:
➊➌.ነጻ የሆኑ እና ጉልበት ያላቸው አስተሳሰቦች ይቅር ባይ፤ ቀና እና ጠንካራ ማንነትን ያጎናጽፋሉ።
:
➊➍.በፍቅር እና ሌላውን ባማከለ መልኩ የሚጸነሱ አስተሳሰቦች ከራስ ወዳድነት የጸዳ ባህሪን ያላብሳሉ።
:
➊➎.ከራስ ወዳድነት የጸዳ ባህሪ ደግሞ እውነተኛ ሃብት እና ብልጽግናን የሚሰጡ ሁኔታዎችን ያመቻቻሉ።
:
➊➏.ሰዎች ሁኔታዎችን እና የህይወት አጋጣሚዎቻቸውን በቀጥታ መምረጥ አይችሉም፤ ነገር ግን አስተሳሰባቸውን መምረጥ ይችላሉ።
:
➊➐.አስተሳሰባቸውን ሲመርጡ በተዘዋዋሪ ሁኔታዎችን እና የህይወት መንገዳቸውን መረጡ ማለት ነው።
:
✿︵♡︵♥︵♡︵♠︵♡︵♥︵♡︵✿
:
#እናም ወዳጄ በመጨረሻም አንድ ነገር ልበልህማ፥

☞በህይወትህ ሰው ረሳኝ ብለህ ፈጽሞ አትጨነቅ። ምክንያቱም፦

➊.ጊዜ አይቶ→የማይከዳህ፣
:
➋.ብትወድቅ→የሚያነሳህ፣
:
➌.ብትበድለው→ይቅር የሚልህ አምላክ ሁሌም ከጎንህ ነውና!......ይቀጥላል✍
:
#አምላክ ጭንቀትን ከልባችን ያርቅልን!(አሜን)


👉👉 ልምከርሽ👈👈

ውበትሽን አይቶ የተመኘሽ እና ከውበትሽ ጀርባ ያለውን
ማንነትሽን አውቆ ያፈቀረሽ ሰው የተለያዩ ናቸው።
ለምን ነገርከኝ እንዳትይ?
እኛ ወንዶች የፈለግነውን እስክናገኝ ሴትን ንግስት ማድረግ እናውቅበታለን። ያፈቀረ ግን ተብታባ ነው፤ ውበትሽን ለመግለፅ እንኴን አንደበት የለውም፤ ነገር ግን በውስጣዊ ማንነትሽ እሱነቱን አጥቶ ሌት ተቀን አንቺን በምናቡ ሲያወጣና ሲያወርድ፣ የአንቺን ህይወት ለማድመቅ የራሱን ሲያፈዝ፣ ከሰው በላይ የነበረው መቀመቅ ሲወርድ ያኔ ላንቺ ያንስብሻል። ያኔ ላንቺ ተራ ሰው ይመስልሻል።

እናም ፍቅርሽን ገላሽን ለተመኘው ትሰጪና ደግመሽ ብትፈጠሪ እንኳን የማታገኝውን ንፁህ አፍቃሪሽን ልብ አንኮታኩተሽ ትሰብሪዋለሽ። እሱም ለዘለዓም ልቡ ታሞበት እንደማቀቀ ፍቅሩን ተቀምቶ አዝኖ አፈር ይሆናል። አንቺ ሳታውቂ ራስሽን የሰጠሽው ግን አውቆ ይተውሻል። በቃላት ድርደራ በስጦታ ጋጋታ ንግስት ያስመሰለሽ ያሻውን ፈጽሞ ሲያበቃ ከጥፍሩ ቆሻሻ እንኳን አይቆጥርሽም። ለዚ ነው የተመኘሽ እና ያፈቀረሽ የተለያዩ ናቸው ያልኩሽ።


ቃል…
(ሰለሞን ሳህለ)
--------------
ከጎጆው አጠገብ በረንዳው ላይ ቆሞ
ስለሷ እያሰበ ደጋግሞ ደጋግሞ
የጻፈውን ግጥም እያነበበችው
የናፈቀው ፊቷን በእንባዋ አጠበችው
‘’ቃልሽ ቀን ነበረው…
ቃልሽ ቅን ነበረው…
ቃልሽ ቀን ገደለው…’’
የሚለውን መግብያ ዘጠኝ ጊዜ አንብባ
ቃሏንና ቀኗን አንድ ላይ አስባ
መአልትና ሌቱን አንድ ላይ ሰብስባ
የገደለችውን ቀን ልክ እንዳወቀችው
የናፈቀው ፊቷን በእንባዋ አጠበችው
‘’ህይወት ውጣ ውረድ የትሙ ብዙ ነው
ቀን የገደልሽውም አውቀሽ ሳታውቂ ነው
በፀሀይቱና በጨረቃ መሀል
በሰዓታት እጣ በቀን ማታ ክፍል
ከአንደኛው ትንፋሼ ቀጣዩ ሲቀጥል
ስጠብቅሽ ነበር ከእስትንፋሴ እኩል
እዛው ነሽ አውቃለሁ እዚህ ነሽ መጥተሻል
ልቤ ገራገር ነው እስከዚህ ያምንሻል!’’
የሚለውን መዝጊያ ዘጠኝ ጊዜ አንብባ
ፎቶ ደብዳቤውን አንድላይ ሰብስባ
ፍቅር የሰጣትን በፍቅር አስባ
ልበ ገራገሩን…
ልቡን እንዳደማች ልክ እንዳወቀችው
የናፈቀው ፊቷን በእንባዋ አጠበችው !!


የፍቅር ምሽት
# ወዳጄ ፥

ከድካምህ ብዛት የተነሳ እንቅልፍህ የሞት ያህል ይከብድሃል።
:
ከመዛልህ የተነሳ አርብና እረቡ ራሱ ትዝ አይልህም።
:
ከመድከምህ የተነሳ ልክ የሆነዉና ያልሆነዉ እንኳ ከህሊናህ ጠፍቷል።
:
ደግመዉ ደጋግመዉ ከመስበካቸዉ የተነሳ ሊሞቱ ወራት የቀራቸዉን የካንሰር ህሙማት እንኳ ከአምላክ መንገድ ይልቅ ወደ ከንቱ ደስታ ሲመሯቸዉ ስታይ እንኳ ልክ ይመስልሃል።

እዉነትን ምቾትና ሃብት የሚያብራሩት ይመስልሃል።

ዉበትና እዉቀት ሃቅን የያዙ ይመስልሃል።
:
ቆሻሻና ድሃ የሆነ ህዝብ እዉነትና ክብር ያለዉ መሆኑን ትዘነጋለህ።
:
በምድር ሁሉ ያለ ምቾት እስከእድሜ ልክ ቢቀርብላቸዉ እንኳ ማተባቸዉን ከአንገታቸዉ የማይለዩ ዝም ያሉ ሚሊየን ወንድሞች እንዳሉህ ትዘነጋለህ።
;
ባይናገሩም፥ ባይጮሁም፥ ባይለፈልፉም ለክፉ ቀን በነፍስህ እንኳ የምትተማመንባቸዉ የእናትህ ልጆች እንዳሉ ትዘነጋለህ።
:
በየቤቱ በመንፈቀ ሌሊት ነቅቶ ስለ ሃይማኖቱና ስለእናት ሃገሩ የሚያለቀስ ዉጩ ተራ የሚመስል እንደ ሰደደ የሚነድ እሳት አዝሎ የሚዞር ወንድም እንዳለህ ትዘነጋለህ።
:
ሺ ቢያፈርሷቸዉ፥ ሺ ቢንዷቸዉ ለህሊና የሚያስቸግር ብርታት ያላቸዉና በተቆረጡት ቁጥር የሚተኩ ሚሊየኖች እንዳሉ ትዘነጋለህ።

➊.ስለእነዚህ ሚሊየኖች ስትል ሃሳባቸዉና ድርጊታቸዉ ሁሉ ከረከሱት ሰዎች ራቅ።
:
➋.በማንም ላይ ተንኮል አታስብ።

➌.የሚሰማህን ነገር ለሚመለከተዉ ሰዉ ተናገር።

➍.ሃይማኖትህንና የሚጠቅምህን የአባቶችህን ባህል በማተብህ ምለህ ያዝ።
:
➎.ከእዉነትና ከፈጣሪ ዉጪ ሌላ ዳኛ አይኑርህ።

➏.ድካምህን አስብ።

➐.ስንፍናህን ልብ በል።

➑.ለአንድ ቀን እንኳ ነቅተህ መቆየት የማትችል አቅመ ቢስ መሆንህን ልብ እያልክ ኑር።

❀︵♡┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈♡︵❀


​💞#የፍቅር_ግንኙነትን_ረጅም_ጊዜ_ለማቆየት_ሚረዱ_ነጥቦች💞

🗝አንደኛውና ዋነኛው ነገር #ኩርፊያን 😒ማቆም ነው ትንሽዋ ነገር ምትገነው በኩርፊያ ም/ክ ነው በምንም ነገር ከማኩረፍም ሆነ ከመበሳጨት በፊት ተነጋገሩ።

🔑ሁለተኛው ነገር ምንም ነገር አትመዝኚ/ን ለምን አይደውልም ለምን ቴክስት አይፅፍም ……………ለምን ሚለውን ነገር ባጠቃላይ ከአይምሮዋቹ አሶጡት ምንም ነገር አትመዝኑ ሁሉም የሆነበት የራሱ ም/ክ አለ።

🗝ሶስተኛው እና ግን ቀዳሚዊ ነገር ለሁሉም ነገር አትቸኩሉ በአንዴው ስለ አንድ ሰው ማንነት ሳታውቁ አበድንልህ ሞትንልህ አትበሉ በስተመጨረሻ ስለ አፍቃሪያቹ ስሰሙ መጨረሻው መዘዙ ለናተው ነው።

🔑ለወሲብ አትቸኩሉ ከስጋዊ እርካታ በፊት ልባዊ ፍቅራቹን ማጠንከር አለባቹ ወሲብ አስቀድማቹ ኃላ ፍቅራቹን ረስታቹ ሁሌም ለስጋዊ እርካታቹ ብቻ መገናኘት ትጀምራላቹ በመጨረሻም ግንኙነታቹ ይፈርሳል።

🗝ሌላው ደሞ ሁሌም እንደምለው #ትኩረት #ትኩረት #ትኩረት ትኩረት አስፈላጊው ነገር ነው ለአጋራቹ ትኩረት እና ጊዜ ስጡ።

🔑ካለሱ ወይም ካለስዋ መኖር አልችልም ብላቹ አስቡ ባሰባቹ ቁጥር ለአፍቃሪያቹ ትልቅ ቦታ እየሰጣቹት ትመጣላቹ

🗝ቅናትን አጥፉ❌
ወሬ አትስሙ❌
በሆዳቹ ቂም ከመያዛቹ በፊት መነጋገር ልመዱ💯

🔑ይሄ ቢሄድ ያይመጣል ምትሉትን ሁሉ ከሀሳባቹ አውጡ ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥም ዝም ብላቹ 10ፍቅረኛ ከመያዝ ይልቅ ለህይወታቹ ሚያስፈልገውን ሰው መርጣቹ መስዋት ብትከፍሉለት ይሻላል።

ወንድሜ እህቴ መለያየትን እንደመፍትሄ አትውሰጂ/ድ መለያየት መፍትሄ አይደለም ፍቅር እንደ ህፃን ልጅ ነው በትግስትና በእንክብካቤ ነው ማደግ ያለበት ትግስት ይኑራቹ ያለፈውን አታስታውሱ ባለፈ ሚዛን አትመዝኑ👍።
🍃❤️


​1🍃•➫ ✰" የሌለኝ እስኪኖረኝ ያለኝ በቂዬ ነው !

2🍃•➫ ✰ በዝምታህ ውስጥ ብዙ የምትናገረው ነገር እንዳለህ ሁሉ በሳቅ ውስጥም ብዙ ምትደብቃቸው ህመሞች አሉ !

3🍃•➫ ✰ ፍቅር ስጦታ እንጂ ብድር አይደለም ‼️

4🍃•➫ ✰"አባቴ" አንተ ለኔ ልዩ አባት ነህ !

5🍃•➫ ትልቅ ምኞት አለኝ እስከመጨረሻው ድረስ " አባቴ " አጠገቤ እንደሚሆን !

6🍃•➫ የሚቆጨኝ ያሳለፍነው ሳይሆን ተስፋ ያደረኩት ነው ! 🙎‍♂

7🍃•➫ ሙሉ ማንነትህን ያልተቀበለህን ሰው ለማሳመን አትሞክር ለዛሬ ነው እንጂ ለነገ አይሆንህም !

8🍃 •➫ አንዳንዱ ዛሬ የሚያስደስተውን ሲያገኝ ትላንት መስዋእት የሆነለትን ይረሳል !

9🍃•➫ ኩራትህን ዋጥ አድርገህ ስህተትህን ተቀበል ይህ እድገት እንጂ ውድቀት አይደለም !

10🍃➫ መጥፎ ሰው እንዳላለይ ብለህ አይንህን አትጨፍን ጥሩ ሰው ሲያልፍ ያመልጥሀልና !

@ethiotksoch


1❤➫ የባከነ ተጨማሪ ሰአት በኳስ ሜዳ እንጂ ፣ በህይወት የለም ጊዜህን ተጠቀምበት !
━━━━━━━━━━━━
2❤➫ አንዳንድ ሰዎች ችግራቸውን ከሌሎች የበለጠ ጎልቶ ስለሚታይ እንጂ ከችግር ነፃ የሆነ ሰው የለም !
━━━━━━━━━━━━
3❤➫ ብዙ ጓደኞችእንዲኖሩ አትጣር አንድ "አንድ" ጓደኛ ይበቃሀል የጓደኞች ማነስ ካሳሰበህ አስመስል አንድ ሺ ጓደኛ ታገኛለህ
━━━━━━━━━━━━
4❤➫ ነገሮች ሲበላሹብህ አብረህ አትበላሽ : የነገውን ቀን ለማየት ቀና በል !!
━━━━━━━━━━━━
5❤️➫ " ማንም እንባህን የሚያይልህ
የለም
ማንም ሀዘንህን የሚያህልህ
የለም
ማንም ህመምህን የሚያይልህ
የለም

• ሁሉም ግን ስህተትህን ያያሉ ‼️
━━━━━━━━━━━━


For any comment @nege_jr


❌❌❌❌ @Love33211 ❌❌ የሚለው የቴሌግራም account የኔ ኣይደለም በኔ ፎቶ ተጠቅሞ ለሰዎች የሚያበሳጩ ነገሮች እየሰራ ነው ። ለመናገር ሚያሳፍሩ ነገሮችን ❌

ተጠንቀቁ ❌❌❌
0961354386


😱😱😱

Instagram
@nege_jr


H.B.D TO ME 🎂🎂🎂
@nege_jr










“አይገርምህም ለዚህ #ሽሮ ህዝብማ እኔ #ጥብስ ነኝ” አላለችም?🙊🙉😏

ለዚህ ነዋ የብዙዎች ፆም መፍቻ የሆንሽዉ 😜

እሄን አለ ብላቹ ሰምና ወርቅ ለማዉጣት የምትታገሉ ነገረኛ ሰዎች አርፋቹ ተቀመጡ 😂🤣

🤝 Join & Share @sakitajr


ለቅሶ ቤት ገብቶ ምግቡን ድብን አርጎ ከበላ በኃላ ካመት አመት ያድርሰን ብሎ ወጣ😱😱

#ጀለስ_ሆያሆዬ ጭፈራ ላይ ያለህ መሰለህ እንዴ 😡

@sakitajr
@sakitajr
@nege_jr

20 last posts shown.

316

subscribers
Channel statistics