ምኲራብ
አቢይ ጾም ከገባ አሁን ሦስተኛው ሳምንት ላይ ደርሰናል። ይህ ሶስተኛው ሣምንት ደግሞ ስያሜው ምኲራብ ተብሎ ይጠራል ምኲራብ የተባለበትም ምክንያት ጌታችን ከምኩራብ ገብቶ ማስተማሩ ድውያንን መፈወሱ እና በምኲራብ የተለያዩ ተአምራቶችን ማድረጉ የሚነገርበት ሳምንት በመሆኑ ነው።
ምኲራብ
ምኲራብ የስሙ ትርጉም እንደ ኮረብታ እንደ ተራራ ያለ ታላቅ ህንፃ ቤት ማለት ነው።
መንፈሳዊ ትርጉሙም የጸሎት ቤት ማለት ነው ።
በዚህም አይሁዳውያን እየተሰባሰቡ 🙏ጸሎት ያደርሳሉ። ሕገ ኦሪቱን ይማራሉ ትንቢተ ነቢያትን ይሰማሉ። ምኲራብ ዋና አገልግሎቱም መንፈሳዊ ነገር ብቻ የሚከናወንበት እግዚአብሔር የሚመለክበት ነው። በዘመኑ የነበሩ የምኲራቡ ሹማምንት ግን ይህን መንፈሳዊ አገልግሎት ቸላ በማለት ለመንፈሳዊ ነገሮችም ግዴለሽ በመሆን። የጸሎት ቤት እና የአምልኮ ሥፍራ የሆነውን ይህን ምኲራብ የገቢያ ቦታ አደረጉት ።
እግዚአብሔርን ሣይሆን ገንዘብን ፈለጉበት።
ለእግዚአብሔር ትተው ለገንዘብ ተሯሯጡበት።
በዚህ የተነሣ ጌታ ወደምኲራብ በመግባት በምኲራብ የሚሸጡትን የሚለውጡትን በጅራፍ እየገረፈ ከምኩራብ አስወጣቸው። እንዲህም አላቸው “ርግብ ሻጪዎችንም፦ ይህን ከዚህ ውሰዱ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት አላቸው።”ዮሐንስ 2፥16
ምክንያቱም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእሱ የመጀመርያ የሆነውን ታላቁን የፋሲካን በዓል ለማክበር ወደኢየሩሳሌም ከወጣ በኋላ አገልጋዮቼ ካህናት እንዴት ናቸው? መስዋዕት እየሰው ነው ወይ፣ ጸሎትስ እያደረሱ ነውወይ፣ ሕዝቡንስ እየባረኩ እያስተማሩ ነው ወይ? በትንቢት የናፈቁኝ በሱባኤ የጠበቁኝ እኔ ሥጋ ለብሼ እነሱን ተዛምጄ ወደ እነርሱ ወደ ወገኖቼ መጥቻለሁና እስኪ ካህናቱን ልያቸው ብሎ ወደ ምኲራብ ገባ።
ወደ ምኲራቡ ገብቶ ያገኘው ግን ሊደረግ ቀርቶ ሊታሰብ እንኳ የማይገባውን ነውር ነበር።
ካህናቱ ሲያስተምሩ ሕዝቡም ቁጭ ብለው ሲማሩ፣
ኦሪቱ ሲነበብ ሕዝቡም ጸጥ ብለው ሲሰሙ፣
ካህናቱ ሲባርኩ ሕዝቡም ተባርኮ ጌታ ሆይ አንተ ታውቃለህ? እያሉ የውስጣቸውን ለአምላክ አደራ ሲሉ አይደለም። ይልቁንም አገልጋዮች ለዋጮች ሆነው፣ ተገልጋዮች አስለዋጮች ሆነው እና
መቅደሱም የገበያ ማእከል ሆኖ ነበር ያገኘው።
ጌታም የጸሎት ቤቱ የገብያ ማእከል ሲሆን አልታገሰም።
በመቅደስም በሬዎችንና በጎችን ርግቦችንም የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፤
የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፥ የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፥ርግብ ሻጪዎችንም፦ ይህን ከዚህ ውሰዱ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት አላቸው።ዮሐንስ.2፥14-16 ሁሉንም ግልብጥብጡን አወጣው ገለባበጠው።
አዎ ስለ መቅደሱ የሚጨነቅ የመቅደሱ ባለቤት ነው ስለልጅ የሚጨነቅ የወለደ ነው እንደሚባለው። የእግዚአብሔር መቅደስ የከብቶች ገብያ እና የለዋጫች መፈንጫ ከሆነ ሰነባብቷል። አማናዊ የእግዚአብሔር መቅደስ ሰውነታችን የእንስሳዊ ጠባይ ከተላበሰ ቆይቷል። እንደ እንስሳም ሆኖአል።እንስሳ ሲነዱት የት ልትወስዱኝ ነው ብሎ አይጠይቅም። ሰውም እንደ እንስሳ ሊታረድ ወደሞት እየሄደ የት ነው? ብሎ የማይጠይቅበት ዘመን ነው። ።እንስሳ የሚኖረው ለሥጋው ነው ።ሰውም የሚኖረው ለሥጋው ብቻ ሆኗል ። እንስሳ የዘወትር ሐሳቡ ሆዱ ነው ።ሰውም የነፍሱን ነገር ረስቶ ለሆዱ የሚተጋበት ዘመን ነው ።
እግዚአብሔር ዛሬም ቤቴ የጸሎት ቤት ነው ይላል ።
እናንተ ካህናት እየሰማችሁ ነው? ቤቴ የጸሎት ቤት ነው ። አትለዋወጡበት፣ አትጨቃጨቁበት፣ አትካሰሱበት፣ ጉቦ አትብሉበት፣ አትቀልዱበት የቅጥር መሥሪያ ቤት አታድርጉት። ተቀጣሪ አትሁኑ አገልጋዮች ሁኑበት እንስሳትን አስወጥታችሁ ጸሎት ሰአታት ኪዳን አድርሱበት። እግዚአብሔርን ፈልጉበት ገንዘብን አትፈልጉበት የእግዚአብሔር ቤት ባንክ ቤት አይደለምና። ቤቴ የጸሎት ቤት ነው።ዮሐንስ.2፤16
እናንተም ምዕመናን እየሰማችሁ ነው ?
ቤቴ የጸሎት ቤት ነው ።
ዝሙት አትስሩበት፣ አትጋደሉበት፣ አትጣሉበት፣ ቂም አትያዙበት፣ በቀል አትቋጥሩበት፣ ቤቴን አታርክሱት፣
ዘር አትቁጠሩበት፣ ጭፈራ ቤት አታድርጉት ግሮሰሪ አታድርጉት ቤቴ የጸሎት ቤት ነው ። እናንተ የእግዚአብሔር መቅደስ ናችሁ። " ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:19-20)
ቤቴ የጸሎት ቤት ነው 🙏
መልካም የጾም ሳምንት
✍️Ermi
@Ewntegna