ልትኖር ከምትቃትት
አንዲት ደቃቃ ነፍስ የተላከዉ መልዕክት
አትያዙኝ ልዉደቅ ብዬ እየጮኩኝ
እጣ ፋንታ ሆኖኝ
መሳቅ ብርቅ ሆኖብኝ
ለማከም ስሞክር የህመሜን ቁስል
ባትኖር ምን ነበረ ባለሁበት ክልል
ሂድ ራቅ ይሸታል
የቆሰለዉ እኔነቴ ይከረፊል
መጠላት ገንዘቡ
መወደድ ርሃቡ
መፈለግ ምኞቱ
መተዉ የግል ሃብቱ
ለሆነዉ እኔነቴ
እንዴት ልንገርልህ
እንዴት ላስረዳልህ
ምንስ ልበልልህ
ለመተዉ ሚቸኩል ልቤን በምን ቃል ላስረዳዉ
ወዶሃል እያይኝ በምን ቃል ልንገረዉ
ጨነቀኝ አለሜ ምገባበት ጠፊኝ
ልኖር መጓጓቴ ይባሱኑ ጎዳኝ
የኔ ያልኩት አለም ራሴኑ አደማኝ
አንዲት ደቃቃ ነፍስ የተላከዉ መልዕክት
አትያዙኝ ልዉደቅ ብዬ እየጮኩኝ
እጣ ፋንታ ሆኖኝ
መሳቅ ብርቅ ሆኖብኝ
ለማከም ስሞክር የህመሜን ቁስል
ባትኖር ምን ነበረ ባለሁበት ክልል
ሂድ ራቅ ይሸታል
የቆሰለዉ እኔነቴ ይከረፊል
መጠላት ገንዘቡ
መወደድ ርሃቡ
መፈለግ ምኞቱ
መተዉ የግል ሃብቱ
ለሆነዉ እኔነቴ
እንዴት ልንገርልህ
እንዴት ላስረዳልህ
ምንስ ልበልልህ
ለመተዉ ሚቸኩል ልቤን በምን ቃል ላስረዳዉ
ወዶሃል እያይኝ በምን ቃል ልንገረዉ
ጨነቀኝ አለሜ ምገባበት ጠፊኝ
ልኖር መጓጓቴ ይባሱኑ ጎዳኝ
የኔ ያልኩት አለም ራሴኑ አደማኝ