Posts filter


ጊዮን ሆቴል የሚገኘው ግሮቭ ጋርደን ለወንዝ ዳር ልማት መፈረሱን ባለቤቱ አርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ ገልጿል።
#FastMereja


ለ15 ቀን ለኢትዮጵያ እንዲጸለይ ታወጀ

#FastMereja I በመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ባሉት ቀጣናዎች፣ ክልሎች እና አጥቢያዎች በሙሉ አገራችን ኢትዮጵያን አስመልክቶ ከየካቲት 1 ጀምሮ እስከ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በጌታ ፊት ጸሎት እንዲደረግ በመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር መሪዎች ጉባኤ ተወስኗል::


#የስጋ ሞታቸውን ለምነው ያገኙት ቅዱስ አባት


በሀገራችን በኢትዮጵያ ወንጌል አንዲስፋፋ ትልቅ አስተዋጽኦ ካደረጉ አጋጣሚዎች የተስዓቱ ቅዱሳን መምጣት ነው፡፡

በአክሱማዊው ሥርወ መንግሥት በምጽዋና ቀይ ባሕር አድርገው የገቡት ዘጠኙ ቅዱሳን በቅድሚያ የጊዜውን ቋንቋ ግዕዝ ከተማሩ በኋላ በርካታ ቅዱሳን መጻሕፍትን ከተለያዩ ቋንቋዎች ወደ ግዕዝ ተርጉማል፡፡ ከእነዚህ ሀገራችንን በወንጌል ብርሃን እንደ ፀሐይ ካበሯት ቅዱሳን አንዱ ታላቁ አባት አባ ጽሕማ ናቸው፡፡ የትውልድ ሀገራቸው አንጾኪያ ሲሆን አቡነ ጽሕማ የተባሉት ጺማቸው በጣም ረጅም ስለነበረ ነው፡፡ አባ ጽሕማ ገዳም እየገደሙ፣ በዓት እያበጁ፣ ከሣቴ ብርሃን አባ ሰላማ የመሠረተውን የክርስትና ሃይማኖት በከፍተኛ ሁኔታ አስፋፍተዋል፡፡ ገዳማትን አስፋፍተው የወንጌልን ብርሃን በሀገራችን ላይ አብርተዋል፡፡


ትግራይ ዓድዋ አካባቢ የሚገኘው ደብረ ሐተታ የሚባለው ገዳማቸው ትልቅ በረከት ያለበት ስፍራ ነው፡፡ ጻድቁ በጸለዩበት ስፍራ የሚገኘው ፈዋሽ ጸበላቸው  አሁንም ድረስ በርካቶችን ከጭንቀት የሚገላግል ነው፡፡ የተፈጥሮን ሕግ በሻረ መልኩ ይህ ጸበል በጋ ሲሆን መጠኑ ይጨምራል፣ ክረምት ላይ ደግሞ ይቀንሳል፡፡ ሌላው አስገራሚ ነገር በጸበሉ አካባቢ ሣር ወይም እርጥብ ነገር ፈጽሞ አለመኖሩ ነው፡፡ በሰማዕትነት ያረፉት አቡነ ጽሕማ ጌታችን ከሞት ቢያስነሳቸውም እርሳቸው ግን እንደገና ልሙት ብለው ለምነው ነው ያረፉት፡፡  በገዳሙ ውስጥ መካነ መቃብራቸው ካለበት ትልቅ ተራራ ሥር ውስጥ ለውስጥ ወጥቶ የሚመጣው ሙቀት ያለው እስትፋስ ለአስምና ለቁርጥማት መድኃኒት ነው፡፡ በርካታ ሰዎችም ከHiv ኤድስ ድነዋል፡፡


በአንድ ወቅት አቡነ ጽሕማ ኢየሩሳሌም ደርሰው ሲመለሱ የሞተ ሰው ቢያገኙ በበድኑ ላይ የነበሩትን ተባዮች ወደሳቸው ሰውነት አስተላልፈው ተባዮቹ ሰውነታቸውን ሲመገቡ ኖረዋል፡፡ ተባዮቹም ወርቃማ ክንፍ ያላቸው ሆኑ፡፡ እነዚያ ተባዮች ዛሬም ድረስ በዓመት አንድ ጊዜ መስከረም 21 ቀን ላይ ጻድቁ ሰማዕትነት ወደተቀበሉበት ቦታ እየበረሩ ሲሄዱ በግልጽ ይታያሉ፣ ድምጻቸውም ይሰማል፡፡ ከዚያም ይሰወራሉ፡፡ አቡነ ጽሕማ ከገዳማቸው ወጥተው አርድእቶቻቸውን ለመጠየቅ "ወርዒ" በተባለው ቦታ አባ ፊልሞና ገዳም ደርሰው፣ ወንጌልን እየሰበኩ ሲመለሱ ሽፍቶች “አትስረቁ” የሚለን ይህ ደግሞ ማነው ብለው ስለገደሏቸው ለወንጌል ክብር ሰማዕትነት ተቀብለዋል፡፡

ይሁንና ጌታችን ጻድቁን አባት ከሞት አስነሣቸው፡፡ እርሳቸውም ወደገዳማቸው ተመልሰው ለቀናት ሲጸልዩና ለገዳዮቻቸው ምሕረትን ሲለምኑ ቆይተው ከጌታችን ታላቅ ቃልኪዳን ከተቀበሉ በኃላ እባክህ ወዳንተ ውሰደኝ ብለው እንደገና በሰላም ዐርፈዋል፡፡ ገዳማውያን አባቶችና እናቶቻችን የዚህን ዓለም ክብር ንቀው የሰማያዊውን መንግስት ክብር ሽተው “ሊሔዱ ጌታቸውንም ሊያዩ ይወዳሉ፡፡” አቡነ ጽሕማ በመጨረሻ ጥር 19 ቀን ካረፉ በኃላ በወቅቱ የነበረው ደገኛው ንጉሥ ዐፄ ገብረ መስቀል ተዝካራቸውን አድርጎላቸዋል፡፡ ጻድቁም በአካለ ነፍስ ተገልጠውለት እርሱም ኅዳር 30 ቀን እንደሚያርፍ ነግረውትና ባርከውት ዐርገዋል፡፡ ጥር 26ም መታሰቢያቸው ይደረጋል፡፡ ገዳማውያንንነስንደግፍ በዓቸውን ስናጸና በረከታቸውን እናገኛለን፡፡



ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444




የኢትዮጵያ አየር መንገድ መግለጫ

ዛሬ ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ ሕንፃ ውስጥ ወደ በረራ ይዞ መግባት ከሚከለከሉ ቁሳቁሶች መካከል ከመንገደኞች የሚሰበሰብ የሲጋራ መለኮሻ (ላይተር) ጊዜያዊ የማስቀመጫ ስፍራ ውስጥ ጭስ በመከሰቱ ለመንገደኞች ደህንነት ሲባል ሕንፃው ለጊዜው አገልግሎት አቋርጧል።

በመሆኑም በዛሬው ዕለት ወደ ሀገር ውስጥ መዳረሻዎቻችን የምትጓዙ መንገደኞቻችን በዓለም አቀፍ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በኩል ወደ በረራችሁ እንድትሳፈሩ ከታላቅ አክብሮት ጋር እያሳሰብን ከነገ ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በተለመደው የሀገር ውስጥ ተርሚናል አገልግሎት መስጠት የምንቀጥል መሆኑን እናስታውቃለን። ለተፈጠረው መጉላላት መንገደኞቻችንን ይቅርታ እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ


ከአዲስ አበባ የሚወጡ 4 የፍጥነት መንገዶች ለመገንባት ጥናት እየተደረገ ይገኛል

ከአዲስ አበባ በተለያዩ መስመሮች የሚወጡ 4 አዳዲስ የፍጥነት መንገዶችን ለመገንባት የሚያስችል ጥናት እየተደረገ ይገኛል፡፡

ከአዲስ አበባ ደሴ ፣
ከአዲስ አበባ ጅማ ፣
ከአዲስ አበባ ደብረማርቆስ እና
ከአዲስ አበባ ነቀምት በሚዘልቁት መንገዶች ላይ ነው፡፡

አራቱን የፍጥነት መንገዶች ለመገንባት የሚያስፈልገው ወጪ የሚሸፈነው በመንግስትና የግል አጋርነት ትብብር ነው፡፡

ከፍጥነት መንገዶቹ መካከል የአዲስ ጅማ እና አዲስ ደብረ ማርቆስ ፕሮጀክቶች ለገንዘብ ሚኒስቴር የመንግስት የግል አጋርነት ቦርድ የቀረቡ ሲሆን ቀሪዎቹም በቅርቡ ይቀርባሉ ተብለው ይጠበቃል ።

ፕሮጀክቶቹም በገንዘብ ሚኒስቴር የመንግስት የግል አጋርነት ትብብር ቦርድ ከጸደቁ በኋላ ወደ ቀጣይ ስራ ይገባሉ።


ወደ ማረሚያ ቤት እንዳይገቡ  የተከለከሉ ነገሮች እና መዘዛቸው

1. በማረሚያ ፖሊስ አባላት ዘንድ፣

በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የፖሊስ አባላት የዲስፕሊን አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 3/2003 አንቀጽ 31 ቁጥር 24 በሕገ ወጥ መንገድ  አባልና ሰራተኛ ከታራሚ ጋር ወይም አባል እርስ በርስ በመመሳጠር ወደ ማረሚያ ቤት እንዳይገቡ የተከለከሉ ነገሮችን  ማስገባት፤ ለሌሎች መተባባር፣ ድርጊቱ ሲፈፀም እያዩ ለአስተዳደር አለማሳወቅ፣ ከፍተኛ ጥፋት መሆኑ በግልጽ ተመላክቷል፡፡
ወደ ማረሚያ ቤት እንዳይገቡ የተከለከሉ ነገሮች
 ሀሽሽ፣
 የሞባይል ቀፎ፣
 ሲም ካርድ፣
 ሲጋራ፣
 አልኮል መጠጥ፣
  ፈንጅ ፣
 የጦር መሳርያ፣
 ተቀጣጣይ ነገሮች፣
 ስለታም ነገሮች …ወዘተ ማስገባት ወይም አስገብቶ መገኜት ሲሆን፣ ይህ ጥፋት በፈፀመ የማረሚያ ፖሊስ አባል ላይ የሚወሰድ እርምጃ፡- በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በከፍተኛ ዲስፕሊን የሚያስጠይቅ፣ጥፋት ነው፤ ጥፋቱም ከስራ ማሰናበት እስከ ፍርድ ቤት ድረስ የሚሄድ ጥፋት ይሆናል፡፡

2. በሕግ ታራሚዎችና በቀጠሮ እስረኞች ዘንድ፣
በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የሕግ ታራሚዎችና የቀጠሮ እስረኞች የተሻሻለ የሥነ ስርዓት ጥፋት ቅጣት አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 5/2009 በክፍል 02 አንቀጽ 11 ቁጥር 35 የተከለከሉ ነገሮችን (ጫት፣ ተቀጣይ ነገር፣ ስልክ፣ ሲም ካርድ ፣ሲጋራ፣ ጋንጃ፣ ቡሪ፣ አንጋዳ፣ አልኮል መጠጥና …ወዘተ) ወደ ማረሚያ ቤትና ማረፊያ ማዕከል ለማስገባት መሞከር ወይም የገባውን መጠቀም የሚያስከትለው የቅጣት አይነት
 ለ4 ወር እንዳይጎበኝ መከልከል ወይም
 ለ3 ወር ለብቻ ለይቶ ማሰር ወይም
 ከ5 ወር ከ1 ቀን አስከ 6 ወር ለሚደርስ ጊዜ ከሚያገኘው ገቢ 1/3ኛውን በመቀነስ ሥራ ማሰራት ወይም ማግኘት ከሚገባው የአመክሮ እስራት 3/4ኛውን መከልከል፡፡

ቁጥር 36 የተከለከሉ ነገሮች (አደንዛዥ እጽ፣ ጦር መሳሪያ እና ተቀጣጣይ ነገሮች ወደ ማረሚያ ቤት እና ማረፊያ ማዕከል ለማስገባት መሞከር ወይም አስገብቶ መገኘት ወይም ሌሎች እንዲያስገቡ መተባበር፣ ጉዳት ማድረስ (በወንጀል ያለው ተጠያቂነት እንደተጠበቀ ሆኖ የሚያስከትለው የቅጣት አይነት
 ለ4 ወር እንዳይጎበኝ መከልከል ወይም
 ለ3 ወር ለብቻ ለይቶ ማሰር ወይም
  ከ5 ወር ከ1 ቀን እስከ 6 ወር ለሚደርስ ጊዜ ከሚያገኘው ገቢ 1/3ኛውን በመቀነስ ሥራ ማሰራት ወይም ማግኘት ከሚገባው የአመክሮ እስራት 3/4ኛውን መከልከል፡፡

ቁጥር 37 የተከለከሉ ነገሮች (ሀሺሽ፣ ፈንጂ፣ እና ተቀጣጣይ ነገሮች…ወዘተ) ወደ ማረሚያ ቤት እና ማረፊያ ማዕከል ለማስገባት መሞከር ወይም ማስገባት ወይም የገባውን መጠቀም የወንጀል ተጠያቂነት እንደተጠበቀ ሆኖ የሚያስከትለው የቅጣት አይነት
 ለ4 ወር እንዳይጎበኝ መከልከል ወይም
 ለ3 ወር ለብቻ ለይቶ ማሰር ወይም 
 ከ5 ወር ከ1 ቀን እስከ 6 ወር ለሚደርስ ጊዜ ከሚያገኘው ገቢ
 1/3ኛውን በመቀነስ ሥራ ማሰራት ወይም ማግኘት ከሚገባው የአመክሮ እስራት 3/4ኛውን መከልከል፡፡ የሚሉት ይገኙበታል፡፡

በመሆኑም አባላት እና ሰራተኞችም ሆኑ የህግ ታራሚዎች፣የቀጠሮ እስረኞች፣ ጠያቂ ቤተሰቦች ወይም ማናቸውም በዚህ ጸያፍ ስራ ላይ የሚሰማራ ሁሉ አባላትና ሰራተኞችን ከስራ ከማፈናቀል ጀምሮ እስከ ማሰሳር ሊያደርስ የሚችል ጥፋት ሲሆን ለታራሚዎች እና ለቀጠሮ እስረኞች ደግሞ በፍርድ ቤት ከተወሰነባቸው ውሳኔ ወይም ከተጠረጠሩበት ወንጀል ተጨማሪ ጥፋት የሚሆን በመሆኑ ለተጨማሪ ቅጣት እንዲዳርጉ የሚያድርግ  ስህተት መሆኑ ታውቆ አስፈጊላው ሁሉ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል፡፡

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን
ጥር 27/2017 ዓ.ም




በማረሚያ ቤት ውስጥ ፎቶ ተነስተዋል በተባሉት ታራሚዎች ዘንድ ተንቀሳቃሽ ስልክ በፍተሻ መገኘቱን የፌደራል ማረሚያ ቤት አስታወቀ

ከሰሞኑ በማረሚያ ቤት የአየር መንገድ ደህንነትን አደጋ ላይ ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል ተብለው በወንጀል ተከሰው ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው የሚከታተሉ እነ ጆን ዳንኤል ከማረሚያ ቤት ሆነው ለቀውታል በተባለ ፎቶ ዙሪያ ብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን የማረሚያ ቤቱን አስተዳደር ጠይቆ ምላሽ አግኝቷል።

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዋና ዳሬክተር አቶ ገረመው አያሌው ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ስልኩ በፍተሻ ተገኝቷል።

ይህን ባደረጉ አካላት ላይ የማጥራት ስራ ተሰርቶ ጥፋተኛው ላይ በአሰራሩ መሠረት በህግ አግባብ ተመጣጣኝ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም አቶ ገረመው ለብስራት ተናግረዋል።


የሉሲ ቅሪተ-አጽም በአውሮጳ ቤተ-መዘክር ለዕይታ ሊቀርብ ነው

በሰው ልጆች አፈጣጠር ሣይንሳዊ ምልከታ 3.18 ሚሊዮን ዓመት እድሜ እንዳለው የሚገመተው የሉሲ ወይንም ድንቅነሽ ቅሪተ-አጽም አውሮጳ ውስጥ ለዕይታ ሊቀርብ ነው ። በሰሜን ምሥራቅ የኢትዮጵያ ክፍል አፋር ውስጥ ከግማሽ ምእተ ዓመት በፊት የተገኘው ይህ ቅሪተ-አካል ከዚህ ቀደም ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለዕይታ ተወስዶ ነበር ። አሁን በአውሮጳ፤ ቼክ ዋና ከተማ ፕራኅ ብሔራዊ ቤተ-መዘክር ለመጀመሪያ ጊዜ ለዕይታ ይቀርባል ተብሏል ።


በCDC እና USAID የበጀት ድጋፍ በኮንትራት የተቀጠሩ ሠራተኞች ውል እንዲቋረጥ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

ከአሜሪካ መንግሥት በCDC ወይም USAID አማካይነት በተገኘ የበጀት ድጋፍ የሚከናወን ማንኛውም ስራም ሆነ ክፍያ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ከJanuary 24 ቀን 2025 ጀምሮ እንዲቋረጥ ማሳሰቢያ ደርሶናል ሲል ጤና ሚኒስቴር ለሁሉም ክልሎች በበተነው ደብዳቤ ተመልክተናል። በCDC እና USAID የበጀት ድጋፍ በኮንትራት የተቀጠሩ ሠራተኞች ውል እንዲቋረጥ ተወስኗል።


በእሳት አደጋ እናት አባት እና የ8 ወር ህፃን የአንድ ቤተሰብ አባላት ህይወታቸው አለፈ

#FastMereja I አደጋው የደረሰው ምዕራብ ሸዋ ዞን ጉደር ከተማ አስተዳደር ነው። እናትና አባት እድሜው አመት ከ8 ወር ከሆነው ህፃን ልጃቸው ጋር በቤንዚን በተፈጠረው የእሳት ቃጠሎ አደጋ ህይወታቸው ማለፉን የጉደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት አረጋግጧል።

ቅዳሜ ጥር 24 ቀን 2017 ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ በጉደር ከተማ አባገዳ ቀበሌ ውስጥ አቶ ዮናስ ደጀኔ የተባለ የባለ ሶስት እግር ባጃጅ አሽከርካሪ ቤንዚን በጄሪካን ቀንሶ ቤት ውስጥ ሲያስቀምጥ በድንገት በመኖሪያ ቤቱ የእሳት አደጋ መፈጠሩን ፖሊስ ጠቁሟል።

ቃጠሎው ለአንድ ሰዓት የቆየ ሲሆን በመኖሪያ ቤቱ ላይ ከፍተኛ ውድመት እንደደረሰም ተገልጿል ። አቶ ዮናስ የተባለው የባጃጅ አሽከርካሪ እና ባለቤቱ ወይዘሮ ብርቱካን የተባለችው እናት ከእነ ልጃቸው ህይወታቸው ወዲያዉኑ ማለፉ ተነግሯል። አቶ ዮናስ ባለቤቱን እና ልጁን ከቃጠሎ ለማትረፍ ሲሞክር ህይወቱ አልፏል፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎች እንዲሁም ፖሊሶች ግለሰቦቹን ከእሳት ለመማውጣት የሞከሩ ቢሆንም ሳይሳካለቸው መቅረቱን የሟች የወይዘሮ ብርቱካን ንጉሴ ወንድም አቶ ደበሬ ንጉሴ ለብስራት ሬዲዮ ሲናገሩ ተሰምተዋል።


በተለመዶ የጣራና ግድግዳ እየተባለ የሚጠራው የቤትና ቦታ ግብር ያለቅጣትና ወለድ የሚከፈልበት ጊዜ እየተጠናቀቀ በመሆኑ ግብር ከፋዮች ከወዲሁ እንዲከፍሉ ተጠየቀ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተለመዶ የጣራና ግድግዳ እየተባለ የሚጠራ የቤትና ቦታ ግብር የሚከፍሉ ግብር ከፋዮች ግብሩ ያለቅጣትና ወለድ የሚከፈልበት ጊዜ እየተጠናቀቀ መሆኑን በመገንዘብ ከወዲሁ ግብራቸውን እንዲከፍሉ ተጠየቀ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የገቢ አወሳሰንና አሰባሰብ ዳይሬክተር አቶ ወንድማገኝ ካሳዬ እንደገለፁት በመዲናዋ 429 ሺህ 829 ግብር ከፋዮች የቤትና ቦታ ግብር ክፍያ እንዲፈፅሙ ይጠበቃል፡፡

ይሁንና እስካሁን ባለው ሂደት 228 ሺህ 222 ግብር ከፋዮች የቤትና ቦታ ግብር መፈፀማቸውን በመግለፅ ይህም የዕቅዱ 51 በመቶ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አክለውም የቤትና ቦታ ግብራቸውን ከከፈሉ ግብር ከፋዮችም 2 ነጥብ 24 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን ተናግረዋል፡፡

የቤትና ቦታ ግብር በተለምዶ የአፈር፣ የቤትና ጣሪያ በሚሉና መሰል ስያሜዎች እስከ የካቲት 30 ድረስ የሚሰበሰብ የግብር አይነት መሆኑ ተገልጿል።


#... ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ


በዕለተ ሥቅለተ ክርስቶስ ካሕናት አባቶቻችን የዘጠኝ ሰዓት ስግደት ሲሰገድ “ኦ ዘጥዕመ ሞተ በስጋ” “በስጋው ሞትን የቀመሰ ኢየሱስ ክርስቶስ” እያሉ ልብን በሚያሳዝን ዜማ ያዜማሉ፡፡ በመለኮቱ ሕያው ሲሆን በስጋው ግን ሞትን ቀመሰ፡፡ የአዳምን ሞት በሞቱ ሊሽር መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን በገዛ ፈቃዱ አሳልፎ ሰጠ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ክርስቲያኖች ሲጽፍ  “ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን… አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን” ይላል፡፡


የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ቄርሎስም “ለቤተ ክርስቲያን ስትል በአደባባይ በጥፊ የተመታህ አቤቱ ይህን ማድረግህ እርስዋን በከበረ ደምህ ትቀድሳት ዘንድ ነው፡፡ ለእርስዋ ሲል ታሥሮ መጎተት የቻለ የበደለውም በደል ሳይኖር፣ ርኩስ ምራቅን ሲተፋበት የታገሠ መድኃኔ ዓለም በእንጨት መስቀል ላይ ተሰቀለ” በማለት ገለጸው፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር ሰው ሆኖ እንደሚያድነን በመጀመሪያ ለአዳም ቃል ገባለት፡፡ ከዚያም በነቢያት ትንቢት አስነገረ፡፡ በስጋ በተገለጠ ጊዜም የሰቀሉትና የገደሉት አይሁድ ሳይቀሩ እንዲናገሩ አፋቸውን አስከፈታቸው፡፡ አልአዛርን ለአራት ቀናት በመቃብር ከቆየ በኋላ ከሙታን ሲያስነሳው ከአይሁድ ወገን ብዙዎች አመኑ፡፡ አንዳንዶች ግን ወደ ፈሪሳውያን ሄደው ኢየሱስ ያደረገውን ነገሯቸው፡፡


በዮሐንስ 11 እንደተጻፈው ከተአምራቱና ከትምህርቱ የተነሳ ሕዝቡ ሁሉ ትቷቸው እንዳይሔድ የፈሩት አይሁድ ሲማከሩ “በዚያች ዓመት ሊቀ ካህናት የነበረ ቀያፋ የሚሉት ከእነርሱ አንዱ። እናንተ ምንም አታውቁም፤ ሕዝቡም ሁሉ ከሚጠፋ አንድ ሰው ስለ ሕዝቡ ይሞት ዘንድ እንዲሻለን አታስቡም አላቸው። ይህንም የተናገረ ከራሱ አይደለም÷ ነገር ግን በዚያች ዓመት ሊቀ ካህናት ነበረና ኢየሱስ ስለ ሕዝቡ ሊሞት እንዳለው ትንቢት ተናገረ፡፡ ስለ ሕዝቡም ሁሉ አይደለም÷ ነገር ግን የተበተኑትን የእግዚአብሔርን ልጆች ደግሞ በአንድነት እንዲሰበስባቸው ነው እንጂ።” ተብሎ ተጽፏልና፡፡ የቀድሞው የግብጽ ኦርቶዶክሳውያን ሊቀ ጳጳስ አቡነ “ሺኖዳ እኛ ወደ እርሱ መውጣት ሲያቅተን መድኃኔ ዓለም ወደኛ ወረደ” በማለት ይገልጹታል፡፡


አምላክነትን ሲሻ የወደቀ የሰው ልጅን የወደደውን አምላክነት ያገኝ ዘንድ የሰውን ባሕርይ ተዋህዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ፡፡ ከኛ በነሳው ስጋም ወደ ሰማይ አረገ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ይለናል፡፡ “ሔዋንን ዲያብሎስ አሳታት የሞት ምክንያት የሚሆን ቃልን ወለደች፡፡ ድንግል ማርያም ግን መልአክ በአበሠራት ጊዜ ሁሉን ወደ ዘለዓለም ሕይወት የሚመራ አካላዊ ቃልን በሥጋ ወለደች፡፡” በማዳኑ ስራ ውስጥ የቅድስት ድንግል ማርያም ድርሻ ታላቅ ነው፡፡ “የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ልጁን ላከ፡፡” ሲል ቅዱስ ጳውሎስም ለገላትያ ክርስቲያኖች ጽፏል፡፡ ገላ 4÷4 ስለፍጹም የሰው ልጆች ፍቅር መድኃኔ ዓለም “በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፣ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ” ፊልጵ 2÷8 ተብሎ እንደተጻፈ፡፡


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444




ዘማሪት ቼሊና የጥሎሽ ሐር ብራንድ አምባሳደር ሆነች።

#FastMereja I ዘማሪ ቼሊና የጥሎሽ ሐር ብራንድ አምባሳደር ሆና ተፈራረመች። ዛሬ ጥር 26/2017 ዓ.ም በካሌብ ሆቴል በተካሄደ የፊርማ ስነ ስርዓት ለሁለት አመት ቼሊና ጥሎሽ ሐርን ታስተዋውቃለች ተብሏል።

የጥሎሽ ሐር መስራች እና ባለቤት ማራናታ ተኩ ባደረገችው ንግግር ጥሎሽ ሐር ለየት ያሉ እና ገበያው ላይ ያልተለመዱ ምርቶችን ለሙሽሮች ለማቅረብ የሚተጋ ድርጅት እንደሆነ ገልጻ በኪራይ ብቻ ሳይሆን የሙሽራ ቀሚሳቸውን የራሳቸው አድርገው ለማስቀረት ለሚፈልጉ ሙሽሮች የሽያጭ አማራጮችንም አቅርበናል ብላለች።

ጥሎሽ ሐር የሰርግ ቀሚሶችን፣ ማስዋቢያዎችን እና የህንድ እና ተመሳሳይ ባህላዊ ቀሚሶችን ያቀርባል። በአዲስ አበባ ጋራድ ሞል ላይ የተከፈተው ጥሎሽ ሐር የካቲት 1/2017 ዓ.ም ግራንድ ኦፕኒንግ ፕሮግራም እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በመግለጫው ላይ ከጥሎሽ ሐር ጋር አብረውት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አጋር ድርጅቶች እና ወዳጆች ተገኝቷል።


ፓርቲው የጣሪያ ግድግዳ/የንብረት ግብር መመሪያ እንዲቆም የመሰረተው ክስ በፍርድ ቤቱ ተቀባይነት ማግኘቱን አስታወቀ

እናት ፓርቲ የጣሪያ ግድግዳ/የንብረት ግብር መመሪያ እንዲቆም የአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስ ቢሮ ላይ ሐምሌ 17 ቀን 2015 የመሰረተው ክስ  በፍርድ ቤቱ ተቀባይነት ማግኘቱን አስታወቀ።

ፓርቲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ በአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ አማካይነት ሚያዚያ 3 ቀን 2015 የተላለፈው የንብረት ግብር መመሪያ “ሕግን ባልተከተለ መንገድና የከተማ አስተዳደሩ ባልተሰጠው ስልጣን” የወጣ መመሪያ ነው ሲል መመሪያው እንዲሻር ክስ ማቅረቡን ገልጿል።

ተጠሪ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እናት ፓርቲ ለመሠረተው ክስ 1ኛ ፓርቲው የከስ ምክንያት የለውም፣  2ኛ የቀረበው ክስ ፓርቲው መብትና ጥቅማቸው አረጋግጠው ያቀረቡት ክስ አይደለም፣ 3ኛ ክሱ በይርጋ የታገደ ነው በማለት ወደ ፍሬ ነገር ክርክር ሳይገባ ውድቅ ተደርጎ መዝገቡ ሊዘጋ ይገባል በማለት ሶስት የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያ በማቅረብ ተከራክረዋል።

ፍርድ ቤቱ ጥር 9 ቀን 2017 ዓ.ም. ባስቻለው ችሎት መመሪያ ተፈጻሚነት ሊኖረው አይገባም ተብሎ እንዲሻር በሙሉ ድምጽ ውሳኔ መስጠቱን እናት ፓርቲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

ውሳኔው በተሰጠ የሰዓታት ልዩነት ተጠሪ የከተማ አስተዳደሩ ፋይናንስ ቢሮ በውሳኔው ለሚዲያ መግለጫ እንዳይሰጥ አቤቱታ በማቅረቡ ለ15 ቀን አፈፃፀሙ እንዲሁም ለሚዲያ መግለጫ እንዳይሰጥ የዕግድ ትዕዛዝ ተሰጥቷል ብሏል፡፡

ይሁንና እስከ ዛሬ ጥር 26 ቀን ድረስ ቢሮው ያቀረበዉ ይግባኝ ባለመኖሩና የእግድ ትእዛዙ የጊዜ ገደብም ያበቃ በመሆኑ ፓርቲው የፍርድ አፈፃፀም ስልጣን ላለዉ የአፈፃፀም ፍርድ ቤት ፋይል ለመክፈት በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

የከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንትም ለ15 ቀናት የሰጡት የአፈፃፀምና ለሚዲያ መግለጫ እንዳይሰጥ የእግድ ትዕዛዝ ቀነ ገደብ ያበቃ በመሆኑ ይህንን ጋዜጣዊ መግለጫ በዛሬው ዕለት ልንሰጥ ችለናል ብሏል፡፡

እናት ፓርቲ በመግለጫው በቀጣይም "በህዝቡ ላይ ከሕግ አግባብ ውጪ የሚጫኑበትን ሸክሞች ወደ ፍርድ ቤት እያቀረበና በሕግ እየሞገተ የሚያስወግድ መሆኑንና ለዚህም በቁርጠኝነት እንደሚሰራ” ገልጿል ሲል አዲስ ስታንዳርድ ዘገባ ተመልክተናል።



18 last posts shown.