አሩስ
«ፉአድ ሙና»
.
ጋብቻ ነው ጥላው፣
ትዳር ነው ከለላው፣
ሪዝቅን የሚሞላው፣
የአንቢዮ‘ች ምሳሌ!
አህመድ ኸይረል ወራ
አሩሱል ከማሌ!
ስልክ ደወለች። እሷ ስትደውል ጥሪዬ ይለያል። ደውላለች ተዘጋጅ የሚል ይመስለኛል። ልብ ድረስ የሚዘልቅ ድምጿን ለመስማት... «እወድሀለሁ» ስትል ከጥፍር አስከ ፀጉሬ የሚሰማህን ንዝረት ለመቻል... ተዘጋጅ የሚል ይመስለኛል። አነሳሁት።
«ፉዬ.. »
«የኔ ውድ!»
«ሁሉንም ጨራረስክ የኔ ጌታ?»
«አዎ የኔ ወድ!»
«አንድ ቀን ብቻ ቀረን አይደል?»
«ጊዜው ግን ፍጥነቱ አይገርምም?»
«መኪናዎቹ ቶሎ ይደርሱልሀል አይደል?»
«አዎ!»
«ዲኮር ራሳቸው ሰርተው ነው የሚልኩልህ ወይስ?»
«አትጨነቂ ውዴ... ቢረሱት ራሱ ካንቺ በላይ ዲኮር አያስፈልገውም!»
«አትቀልድ በአላህ... »
«እና ላልቅስ ውዴ?»
«አንተ ግን አልጨነቀህም? እኔ እኮ ምንም ሳይጎድል የሆነ የቀረ ነገር ቢኖርስ እያለ የሚያስጨንቀኝ መንፈስ አለ።»
«አንድ ቀን ብቻ ነው የቀረው እሁድ ጭንቀቱ ያልቃል... አይዞን»
ተሰነባብተን ስልኩ ተዘጋ።
ውስጤ አምቄው እንጂ ከእሷ በላይ ጨንቆኛል። ሰርግ የሆነ የሚያስጨንቅ ነገር አለው።
ከሰርጉ በኋላ እሷን እንደማገኝ ሳስበው በእኔና በእሷ መሀል የተዘረጋ ሲራጥ ይመስለኛል።
በቃ ፉዬ... በቃ ተነስ ይበቃል... በቃ ንቃ! የቁም ቅዠት ተው ባንን! ንቃ!
ላጤ ባይገባውም እኔ እቃዥሻለሁ።
ላለመደናቀፍ፣
ላለመወናከፍ፣
ማግባት ነው መሸከፍ፣
ከሀላል ቀበሌ!
አህመድ ኸይረል ወራ
አሩሱል ከማሌ!
.
@Fuadmu