FutureX


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Education


The future starts here!

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Education
Statistics
Posts filter


🛑 ሁለተኛ ሳምንታችን ሊፈፀም ነው‼️ ያልጀመራችሁ ጀምሩ!

9ኛ ክፍልን ግማሹን ጨርሰናል። ዛሬም በዓላማ ተነስ። እሁድ የእረፍት ቀን ሳይሆን የሳምንቱ ቁልፍ ቀን ነው። በዚህ ከቀጠልክ አይምሮህ ውስጥ ወዳሰብከው የኢንትራንስ ውጤት እየተጠጋህ ነው፤ ካቆምክ ግን ጸጸት ይጀምራል፣ ውስጥህ ሰላም አይኖረውም።

ዛሬ የምናጠናው English Unit 2 እና Grade 9 Maths Unit 4 ነው። ከዛ እሱን ስንጨርስ የትላንቱ ጥናት ላይ ፈተና እንፈተናለን። ወደኋላ የቀራችሁ ይሄን ቀን ተጠቀሙበት! ነገ ወደ 12ኛ ክፍል ጥናት ነው የምንገባው። ዳይ ወደ ጥናት!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!


🛑 ሰኞ 12ኛን እንጀምራለን! ከዚህ በኋላ የሚባክን ጊዜ የለም‼️

አብረን 9፣ 10፣ 11 እና 12ን ፅድት አርገን በ 6 ወር ውስጥ  እንጨርሳለን። መጋቢት ላይ ክለሳ እንጀምራለን። ስለዚህ ቀን የምትማሩትን 12ኛ ክፍልን ከዜሮ ጀምረን ሰኞ መስከረም 25 ማጥናት እንጀምራለን፤ እሱን ትንሽ ገፋ አድርገን ደግሞ ወደ 9ኛ-11ኛ ክፍል ጥናት እንመለሳለን።

በዚህ አመት በዲስፕሊን ተዘጋጅተን ኢንትራንስን በምርጥ ውጤት ማለፍ አለብን! ያልጀመራችሁ ቶሎ ጀምሩ! ካንተ የሚጠበቀው ቆራጥ ሆነህ በቀን 5 ሰዓት መመደብ ብቻ ነው። ከፈጣሪ ጋር አብረን ታሪክ እንሰራለን! የኛ ጀግኖች ተዘጋጁ!!

ቆንጆ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!

4.8k 0 11 159 123

🛑 ቅዳሜ፡ ለብሔራዊ ፈተና ወሳኝ ቀን! ለኢሬቻ እንኳን አደረሳችሁ 🙌

በውጤት ቀን የቤተሰቦችህን ኩራት አስብ። ያ ደስታ በዛሬው ጥረትህ ይወሰናል። ሰበብ የለም። በመቶ ሺዎች ከሚቆጠሩ ተፎካካሪዎችህ የምትበልጠው ቅዳሜና እሁድን ጥግ ድረስ ስትጠቀም ነው። በሙሉ ትኩረት አጥና።

ዛሬ የምናጠናው Bio Unit 3 & 4 እና Eco Unit 4 & 5 ነው። የዛሬውን ጥናት እንደጨርሰን ትላንት ያጠናነው ላይ ፈተና እንሰራለን። ሞዴል ተፈታኞች ዛሬ Grade 10 Phy, Hist እና SAT ነው ፈተናችሁ። ቅዳሜያችን መባከን የለበትም! ዳይ አሁን እንጀምር!

✳️ Update ካደረጋችሁ በኋላ ኮርሶቹን የቆለፈባችሁ ወይም ክፈሉ የሚላችሁ ተማሪዎች አትደንግጡ፤ Logout ብላችሁት ድጋሚ Login ነክታችሁ ስልክና Password አስገብታችሁ ግቡ። Password ከጠፋባችሁ ወይም ሌላ ችግር ካጋጠማችሁ @futurexhelp ላይ በቴሌግራም አውሩን።

መልካም ኢሬቻ! መልካም ቅዳሜ!
@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!

6k 0 16 218 80

🛑 ወሳኝና አስቸኳይ መልዕክት‼️ ሰኞ ሁላችንም 12ኛ ክፍልን ማጥናት እንጀምራለን!!

በዚህ ድምፅ

1️⃣ ስለ አዲሱ አፕሊኬሽን እና የተማሪዎች ጥያቄ አጭር ማብራሪያ

2️⃣ አዲስ ጀማሪዎችም ሆነ ክረምት የነበራችሁ ሁላችንም እኩል 12ኛ ክፍልን ሰኞ ማጥናት እንጀምራለን። ስለሱ ያብራራል

3️⃣ አዲሱ አፕሊኬሽን ላይ አዲስ ስለተጨመረው እናንተን ጎበዝ የሚያደርግ የሽልማት Feature ያብራራል።

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!

6.8k 0 98 287 257

🛑 FutureX አፕሊኬሽን Update አርጉ፤ ሁላችንም 12ኛ ክፍልን ሰኞ ማጥናት እንጀምራለን‼️

ከአሁን ጀምሮ FutureX አፕሊኬሽን ገና ስትከፍቱት Update የሚል ያመጣላችኋል፤ እሱን ስትነኩ Playstore ላይ ይወስዳችኋል፤ ከዛ በኋላ Update ብላችሁ መጠቀም ነው።

✳️ ማስታወሻ: Update ስታደርጉ  Download ያደረጋችሁት ኖት እና ቪዲዮ በፍፁም አይጠፋም። ደግማችሁ Loginንም ማለትም የለባችሁም።

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!

6.8k 0 16 366 97

🛑 አርብን መዘናጋት አይቻልም! እስከ ጥግ እንጠቀምበታለን፤ ‼️

አእምሮህ አርብን መዝናናት ይፈልጋል። "የዛሬን ሳልጨርስ አላርፍም!" ማለት አለብህ። እንደዚህ አይነት ቆራጥ ውሳኔዎች ናቸው የሚያልፈውን እና የማያልፈውን የሚለዩት። ወጥ አቋም (Consistency) ከጉብዝና ይበልጣል። ሌላው አርብን ሲዘናጋ አንተ ጠንክረህ በሞራል አጥና።

✳️ ዛሬ የምናጠናው Grade 9 Chem Unit 4፣ Hist Unit 6 እና Geo Unit 4 እናጠናለን። እሱን እንደጨረስን የትላንቱ ጥናት ላይ ፈተና እንሰራለን።

✳️ ከክረምት ጀምሮ አብራችሁ የነበራችሁ ተማሪዎች ዛሬ የ 10ኛ ክፍል ሞዴል ፈተናችሁ ይጀምራል፤ ፈተናችሁ English እና Math's ነው በጥንቃቄ ተፈተኑ። መልካም ፈተና!

🚀 ስለ አዲሱ የFutureX አፕሊኬሽን ዛሬ እናሳውቃችኋለን። Update አርጉ ስንላችሁ ማድረግ ብቻ ነው፤ ድጋሚ ስልክና Password አስገቡ አይላችሁም፤ Download ያረጋችሁትን ቪዲዮም አያጠፋባችሁም።

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!


🛑 ኢንትራንስ በምርጥ ውጤት ለማለፍ 3 ነገር በቂህ ነው‼️

1ኛ ቆራጥ መሆን አለብህ (ከኔ የሚጠበቀውን ሁሉ አደርጋለው ብለህ ወስን!)

2ኛ በፕሮግራም አጥና (ጊዜህን አታባክን፣ በየቀኑ በምናወጣልህ ዕቅድ አጥና!)

3ኛ ዲስፕሊን ይኑርህ (ደበረህ ደስ አለህ በየቀኑ ተዘጋጅ፤ በየቀኑ ከ 4 ሰዓት ለጥናት መድብ )። አለቀ እነዚህን 3 ነገሮች ካደረክ ኮርተህ ታልፋለህ።

የዛሬውን ጥናት እና ፈተና ጨረስክ? ካልጨረስክ አልጋው እንዳይነካህ! ሁሉም ተማሪ ማለፍ ይፈልጋል፤ ፍላጎት በቂ አይደለም፤ የሚያልፈው ለአላማው ሲያጠና የሚያድረው ወይም ዕቅዱን ለማሳካት ሳይሰለች ዋጋ የሚከፍለው ነው!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!

7k 0 10 149 74

🛑 ለዩኒቨርስቲ Freshman (የመጀመሪያ አመት) ተማሪዎች አጭር ጥያቄ‼️

በዚህ አመት ወደ ዩኒቨርስቲ የገባችሁ ተማሪዎች ይሄ የመጀመሪያ አመት በጣም ወሳኝ ነው! ምክንያቱም የኢንትራንስ ውጤታችሁ እና የመጀመሪያ አመት የዩኒቨርስቲ ውጤታችሁ ተደምሮ ነው የምትፈልጉት ዲፓርትመት የምትገቡት።

የመጀመሪያ አመት ውጤታቸው ዝቅ በማለቱ ምክንያት ብዙ ልጆች የማይፈልጉትን ትምህርት ይማራሉ፤ ዩኒቨርስቲ የገቡ ታላላቆቻችሁን ጠይቋቸው፤ የማትፈልጉትን ነገር እንደመማር አስቸጋሪ ነገር የለም! ቀጣዮቹን ሁለት ሴሚስተሮች ምርጥ ውጤት ካመጣችሁ ግን የምትፈልጉት ዲፓርትመንት ትገባላችሁ።

✅ እኛም ምርጥ ውጤት እንድታመጡ ለመርዳት ሁሉንም የዩኒቨርስቲ Common ኮርሶች እናስጠናችኋለን።

ከዛ በፊት ግን ፍላጎታችሁን እና አሁን ያላችሁበትን ሁኔታ በደምብ ማወቅ አለብን። ከታች ያለውን ጥያቄ መልሱ፤ ጥያቄዎቹን ለመመለስ 5 ደቂቃ ብቻ በቂ ነው።

ከታች ያለውን ሊንክ ነክታችሁ ሁሉንም ጥያቄ ከመለሳችሁ በኋላ "Next" ወይም "ቀጣይ" እያላችሁ ሁሉንም ጥያቄዎች ከመለሳችሁ በኋላ መጨረሻ ላይ "Submit" ወይም "አስገባ" የሚለውን ንኩ፤ ያኔ መልሳችሁ ይደርሰናል።

ሊንኩ ይኸው👇👇
https://forms.gle/wvevMmTZx3iZTe8GA

7.7k 0 26 35 40

🛑 በዚህ ሞራል ከቀጠልክ ማለፍ ብቻ ሳይሆን ከ 500 በላይ ግዴታ ነው‼️

ውጤትህን የሚወስነው እስከዛሬ የነበረህ ጉብዝና/ስንፍና ሳይሆን፤ በዚህ 10 ወር በሚኖርህ ጥረት ነው። በየቀኑ በፕሮግራም እና በዲስፕሊን ካጠናህ ማለፍ ብቻ ሳይሆን 530 ወይ 550 ወይ 580 አምጥተህ አባትህን፣ እናትህን፣ ጓደኞችህን ሁሉ አስገርመህ ታልፋለህ!

ዛሬ ናቹራሎች የ9ኛ ክፍል Phy Unit-3 እና 4 እናጠናለን፤ ሶሻሎች ከዛሬው Hist Unit-5 እና Geo Unit 3 እናጠናለን። ከዛ እረፍት አድርገን የትላንቱ Math's ላይ ፈተና እንሰራለን። ለአላማችን በቀን ከ 4 ሰዓት በላይ ማጥናት ካለብን እናጠናለን!💪

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!


🛑 ለFutureX አባላት ሶስት ወሳኝ ዜናዎች‼️ የዋጋ ጭማሪው ዛሬ ያበቃል!

1️⃣ የFutureX የአባልነት ክፍያ ከነገ ጀምሮ የዋጋ ጭማሪ ይደረጋል።

2️⃣ አዲስ የFutureX አፕሊኬሽን ይዘን እየመጣን ነው፤ በተለይ እናንተን በኢንትራንስ ይበልጥ ውጤታማ የሚያደርግ አስገራሚ Feature ይዘን መተናል። ነገ ወይ ከነገ ወዲያ ታዩታላችሁ።

3️⃣ አዲስ ጀማሪዎች የዛሬን ጥናት ጨርሳችሁ የነገን ፈተና ስሩ። ከክረምት ጀምሮ አብራችሁን የነበራችሁ ተማሪዎች ደግሞ በደምብ ከልሱ፤ አርብ የ 10ኛ ክፍል ሞዴላችን ይጀምራል። ከዛ ሰኞ 12ኛ ክፍልን ማጥናት እንጀምራለን!

ከፈጣሪ ጋር ይሄ አመት የኛ ነው!💪
@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!

8k 0 11 144 113

🛑 ብታጠናም ባታጠናም 10 ወሩ በፍጥነት ያልቃል! ስለዚህ ጀምር! ዛሬ ክፍያ ሊጨምር የመጨረሻ ቀን ነው ‼️

ጊዜው ይሮጣል፤ ሰኔ ፈተናህ ሳይደርስ አብረኸው መሮጥ አለብህ፤ በፕሮግራም አጥና! በዕቅድና በዲስፕሊን ስታጠና ለኢንትራንስ መጨነቅ ታቆማለህ! እዚህ ለመድረስ 12 ዓመት ለፍተሀል፤ የዚህ 10 ወር ልፋትህ ብሔራዊ ፈተናን በምርጥ ውጤት ያሳልፍሀል! ካልጀመርክ ቶሎ ጀምር!

የFutureX አባላት ዛሬ ሁላችሁም Math's Grade 9 Unit 3 እንጨርሳለን። እሱን አጥንተን ስንጨርስ የትላንቱ ጥናት ላይ ፈተና እንፈተናለን። ዛሬ ከፍተኛ ጥረት ይፈለጋል፤ ሌሎች ሲዘናጉ አንተ ጥረትህን ጨምር። እያንዳንዱን ሰከንድ ተጠቀም። የሚባክን ጊዜ የለም!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!

8.3k 0 15 93 78

🛑 የከፈላችሁ ተማሪዎች ታገሱን እናስጀምራችኋለን‼️

8.1k 0 47 50 117

🛑 ነገ የመጨረሻ ቀን ነው! ክፍያ ይጨምራል‼️

የFutureX አባል የሆናችሁ ተማሪዎች ኢንትራንስ ተፈትናችሁ እስክትጨርሱ ድረስ ሁሉንም ነገር በነፃ ነው የምታገኙት ደግማችሁ አትከፍሉም!!። አባል ያልሆናችሁ ተማሪዎች ከጭማሪው በፊት ተመዝገቡ። መስከረም ሊያልቅ 10 ቀን ነው የቀረን፤ ከዛ 9 ወር ብቻ ነው ለኢንትራንስ ዝግጅት የሚኖረን፤ ማጥናት ያልጀመራችሁ ቶሎ ጀምሩ!

በፕሮግራም የምታጠኑ ተማሪዎች የዛሬን ጥናት ጨርሱ! ትላንት ባጠናችሁት ዙሪያም ፈተና ስሩ! ከክረምት ጀምሮ 9ኛ እና 10ኛን ያጠናችሁ ተማሪዎች ለዚህ ሳምንት የ 10ኛ ክፍል ሞዴል ፈተናችሁ ክለሳ በደምብ አርጉ! ከዛ ቀጣይ ሳምንት ሁላችንም 12ኛ ክፍልን ማጥናት እንጀምራለን!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!

9k 0 27 134 69

🛑 ዲስፕሊን ካለህ በዚህ 10 ወር የማታሳካው ነገር የለም‼️

ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ከዜሮ ጀምረን በዚህ 6 ወር አጥንተን እንጨርሳለን። ከዛ ቀሪውን 4 ወር ከ 9-12 ሙሉ ስንከልስ፣ ብዙ የኢንትራንስ፣ የሞዴል ፈተና ስንሰራ፣ በጣም ወሳኝ Shortnote ስንሰጣችሁ "ከፈጣሪ ጋር ከ 500 በላይ ማምጣት እችላለሁ" ትላላችሁ። ሁሉም ነገር አይናችሁ እያየ ይሳካል!

የዛሬ ዕቅዳችን ናቹራሎች Grade 9 Phy Unit 3 እና Chem Unit 3፤ ሶሻሎች Eco Unit 3 & 4 እናጠናለን። ስንጨርስ ትላንት ባጠናነው ዙሪያ ፈተና እንሰራለን። ከዛ ስንጨርስ ፈታ እንላለን! በርቱ ሁሌም ከጎናችሁ ነን! በዚህ 6 ወር የሚባክን ጊዜ የለም!

✅ ከክረምት ጀምሮ የነበራችሁ የ FutureX አባላት በዚህ ሳምንት ለሚኖረን የ 10ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና ክለሳ አድርጉ ብዙ ጥያቄ ስሩ!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!

9.1k 0 19 77 85

🛑 የተማሪዎች ተደጋጋሚ ጥያቄና መልስ❓

1⃣ የFutureX አባል ከሆንኩኝ ደግሜ እከፍላለሁ?

✅ አትከፍልም፤ የFutureX አባል ከሆንክ ኢንትራንስ ተፈትነህ እስክትጨርስ ድረስ ሁሉንም ነገር በነፃ ታገኛለህ።
-----------------------------------------------------------
2⃣ ለኢንትራንስ በፕሮግራም የምታስጠኑን እንዴት ነው?

✅ ለአዲስ ተማሪዎች ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ለማጥናት ባለፈው ሳምንት ጀምረናል። ለክረምት ተማሪዎቻችን ደግሞ 11ኛ እና 12ኛ ክፍልን ማጥናት ሰኞ መስከረም 25 እንጀምራለን።
------------------------------------------------------------
3⃣ መቼ ልጀምር?

✅ አሁን ጀምር! ጊዜህን ተጠቀምበት፤ ከመስከረም 20 በኋላ የዋጋ ጭማሪ እናደርጋለን።
-----------------------------------------------------------
4️⃣ የFreshman (የመጀመሪያ አመት የዩኒቨርስቲ) የጥናት ፕሮግራም መቼ ይጀምራል?

✅ በጥንቃቄ ት/ቶቹን እያዘጋጀን ነው፤ በጥቂት ቀናት ውስጥ መቼ እንደምንጀምር እና ዝርዝሩን ሁሉ እናሳውቃችኋለን።

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!

9.3k 0 14 72 83

🛑 አዲስ ቪዲዮ ለቀናል‼️

ከክረምት ጀምሮ አብራችሁን የነበራችሁ ተማሪዎች ከሰኞ መስከረም 25 ጀምሮ እስከ ኢንትራንስ እንዴት አብረን እንደምንዘጋጅ የሚያሳይ ቪዲዮ ተለቋል በዚህ ሊንክ ገብታችሁ ተመልከቱ። 👇
https://youtu.be/5B2SsFun5BQ?si=aCnCnmATb9lbmjus

ለአዲስ ጀማሪዎች ደግሞ የ 10 ወር የጥናት ፕሮግራም ባለፈው ሳምንት መጀመራችን ይታወቃል። ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል እንዴት እንደምናስጠና የሚሳይ ቪዲዮ ይኸውና። 👇 https://youtu.be/J7tbCZ8pAp4?si=WbYYhauD7-KOldao

ከዚህ በፊት የነበረው ውጤታችሁ ዝቅተኛ፣ መካከለኛ ወይ ከፍተኛም ሊሆን ይችላል፤ ይሄን ቪዲዮ አይታችሁ የጥናት ፕሮግራሙንና የፈተና ቻሌንጁን ወደ ተግባር ከቀየራችሁት ኢንትራንስን ማለፍ ብቻ ሳይሆን ከ 500 በላይ ታመጣላችሁ!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!

9.3k 0 22 21 45

🛑 የ2ኛ ሳምንት የጥናት ፕሮግራም ዛሬ ተጀመረ‼️

እንዴት አደርክ የነገው የዩኒቨርስቲ ተማሪ? ይሄ ሳምንት በብሔራዊ ፈተና ውጤታማ ለመሆን ወሳኙ ነው! በዚህ የ10 ወር ዝግጅት በብሔራዊ ፈተና በጣም የምትፈልጉትን ትልቅ ውጤት ማምጣት ትችላላችሁ! ከእናንተ የሚጠበቀው በየቀኑ የጥናት ፕሮግራሙን በዲስፕሊን መተግበር ብቻ ነው!

በዛሬ ፕሮግራም ናቹራሎች Grade 9 Bio እና Phy Unit 2፤ ሶሻሎች Grade 9 Eco Unit 2 እና 3 እናጠናለን። ሁለቱም ዩኒቶች አጠር አጠር ያሉ ናቸው። እነሱን ጨርሰን ትላንት ያጠናነው ላይ ፈተና እንሰራለን። በርቱ ፈጣሪ ይርዳችሁ! መልካም የጥናት ሳምንት!🙏

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!

9.3k 0 28 104 96

🔥 ሳንጨናነቅ 10 ወሩን እንዘጋጃለን! የዋጋ ጭማሪ ልናደርግ ነው‼️

የመጀመሪያ ሳምንት ጥናት ጨርሰናል። ለኢንትራንስ ዝግጅት ጥናት ያልጀመራችሁ ያለፈው ጊዜ አልፏል፤ 10 ወር ለተጠቀመበት ብዙ ነው። እስከዛሬ ሳይገባህ ያለፈ ወይም የረሳኸው ካለ አሁን አብረኸን አጥና፤ በዚህ አመት ለኢንትራንስ በፕሮግራም የሚያጠና ተማሪ ታሪክ ይሰራል።

ሁሉንም ነገር ከዜሮ ስለምንጀምር ሳትጨናነቅ ቶሎ አብረኸን ማጥናት ጀምር። በዚህ ሳምንት የጀመራችሁ የዛሬን የጥናት ፕሮግራም ጨርሱ። ✅ ከክረምት ጀምሮ አብራችሁን የነበራችሁ የ FutureX አባላት ከነገ ጀምሮ የ10ኛ ክፍልን ክለሳ ጀምሩ።

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!


🛑 የመጀመሪያ ሳምንታችን ሊፈፀም ነው‼️

እንኳን አደረሳችሁ፤ መልካም የመስቀል በዓል! ዛሬ 7ኛ ቀን ደረስን። የመጀመሪያው ሳምንት ዛሬ ይፈፀማል። በዓላማ ተነስ። እሁድ የእረፍት ቀን ሳይሆን የሳምንቱ ቁልፍ ቀን ነው። በዚህ ከቀጠልክ አይምሮህ ውስጥ ወዳሰብከው የኢንትራንስ ውጤት እየተጠጋህ ነው፤ ካቆምክ ግን ጸጸት ይጀምራል።

ዛሬ ናቹራሎች Grade 9 Maths Unit 2 Part 3ን እንጨርሳለን፤ ጥያቄ በደምብ ስሩ። ሻምፒዮኖች እንዲህ ነው የሚዘጋጁት። ሳምንቱን በድል አብረን እንጨርሳለን! ዳይ ወደ ጥናት!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!

10.6k 0 10 140 97

🛑 ዕቅድ + ዲስፕሊን = ምርጥ ውጤት‼️

ይሄ 10 ወር የሁሉም ተማሪ ህይወት የሚቀየርበት ነው። 9ኛ-11ኛ ክፍል የረሳኸውን፣ ያልገባህን ሁሉ በዚህ 6 ወር አብረን ስናጠና ገብቶህ መጨረስ አለብህ። ከዛ ወደ ክለሳና ሞዴል ፈተና እንቀጥላለን። ከመስከረም 25 ጀምሮ ደግሞ ቀን የምትማሩትን 12ኛን አብረን ማስኬድ እንጀምራለን።

ከእናንተ የሚጠበቀው የምንላችሁን በዲስፕሊን ማድረግ ነው። የዛሬው ጥናት እንዴት እየሄደ ነው? በትላንቱ ላይ ፈተና ሰራችሁ? የጨረሳችሁ ልጆች ፈታ በሉ፤ ነገ እንቀጥላለን፤ ያልጨረሳችሁ አሁኑኑ በሞራል የዛሬን ጥናት ጨርሱ! ዳይ ወደ ጥናት!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!

20 last posts shown.