ግጥም ከብሩኬ አንደበት


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


መንፈሶን በግጥም ያድሱ🆎
ግጥም የውስጥን ገላጭ ነውና🅾
ፈጥነው ይ🀄️ላ🀄️ሉን😍
👇👇👇👇👇👇
@getem_besamuel
Comment👉 @Lanchisel
#ሂወት_ወደፊት_ተጓዥ_ናት
መመለስ_አይኖርም

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


I ሰው


Forward from: N£xt Dr€amer$🔱


ምነው አትመጪም ወይ?

#ገጣሚ ብሩክ የገኒ ልጅ (ብሩኬ)

ዘወትር እያለምኩ
ለወሰደሽ መንገድ ድርሳን እያነበብኩ
አምና ብትቀሪ ለዘንድሮ እያልኩ
ይኸው ስንት ሌሊት ይኸው ስንት ንጋት
በስቃይ ያለፉ ጨለማ ዘመናት
ስጋዬን አራቁተው አጥንቴን አሳስተው
በናፍቆትሽ ሰበብ ህልሞቼን ቀምተው
ይኸው እከፍላለው
የማይታመን ሰው የማመኔን እዳ
በተስፋ ስካሬ
ምሽቱን ስትቀሪ ስጠብቅ ማለዳ
መቅረጥሽ ሲገርመኝ
አሻግሬ እያየው ሰፋ ካለው ሜዳ
ይኸው እኖራለው
ከሚኖሩት በታች ከሞተ ሰው በላይ
ግ'ዝት ተገ'ዝቼ
አትሜው እንድኖር ምስልሽን ካይኔ ላይ
ምነው አትመጪም ወይ?
ጠብቄሽ ደከመኝ
ትዝታሽ ልቤ ውስጥ
ረመጥ ሆኖ ፈጀኝ
ሳስብሽ መኖሩ ማለም ቢታክተኝ
ቢደርስ እርግማኔ
እነደዚህ እያልኩ መራገም አሰኘኝ
ካለሽበት ቦታ
ከባድ አውሎ ንፋስ ይዞሽ በነጎደ
እያወዛወዘ እያንገዳገደ
ደራሽ ጎርፍ ይውሰድሽ
ግንድ እያላተመ ስርቅ ስርቅ እስኪልሽ
ውሃውም ንፋሱም ምናልባት ወደኔ
አምተው ቢጥሉሽ!
ብስራቴ ቢያረጉሽ!

@Lanchisel

join as👉 @Berukpoem
join as👉 @Berukpoem
join as👉 @Berukpoem




°
°
JOIN US👇👇
@getem_besamuel
@getem_besamuel




ሆድ ከሀገር ይሰፋል

#ገጣሚ ብሩክ የገኒ ልጅ (ብሩኬ)

ሆድ አይችለው የለ

በደል እና ችግር ቋጥኝ እያከለ

ሰውኛ ብሂሉ ሰውን ካላደለ

ኖርኩት አይባልም ሸክም ካልቀለለ

ብቻ ምን ቢሆንም

ካለመኖር መኖር ደርሶ ቢያሳምንም

ለነብስ ተብሎ

ለመኖር ይሞታል ጉልበት ይገበራል

ጥሬም ተቆርጥሞ ሌቱን ይታደራል

ፍጡር ቢበደልም

ጎጆ እየቀለሰ ችግር ቢታክትም

ችሎ መኖር ደጉ እስኪያልፍ ያለፋል

ተረቱም እንዲያ ነው

ሆድ ከሀገር ይሰፋል!

@Lanchisel


አላቹ ወይ ተጠፋፋን አደል
እስቲ አለን የምትሉ በላይክ ምልክቷ አሳዩኝ



ችዬ ላላስቀርሽ

#ገጣሚ ብሩክ የገኒ ልጅ (ብሩኬ)

ክረመቱ እየባሰ ውርጩ እየከበደ
ያዘለው ደመና ዶፍ እያወረደ
እደጅ አያስወጣ ብርዱ መከራነው
ይሄኔን እያየሽ ልሂድ የምትይኝ
ምን ብበድልሽ ነው?
ላንቺም አይመችሽ መንገዱ ጭቃ ነው
ለኔም አይመቸኝ ከሌለሽኝ አንቺ
ቅዝቅዝ ይልብኛል ጎጆዬ ኦና ነው
ትንፋሽሽ ካልሞቀው ገላዬ ባዳ ነው
ልንገርሽ ሂወቴ .....
ከጎኔ መሆንሽ ለኔ መኖሪያ ነው
ድምፅሽን ካልሰማው አይንሽን ካላየው
የለመደሽ ውስጤ ፍፁም ወዳቂ ነው
የምልሽ የለኝም የምለው ይሄው ነው
ከሰማሺኝ መቼም ካዘነልኝ ልብሽ
በጋው እስኪመጣ አይቁረጥ አንጀትሽ
ግዴለም የኔ አለም ክረምቱ እስኪወጣ
ካጠገቤ ሁኚ እንደው ልማፀንሽ
ክረምቱ በቃኝ ሲል አኔው ነኝ ምሸኝሽ
የምቴጂው መንገድ
ብዬ ጨርቅ ያልግልሽ
እንባ እያነቀኝ ሁነኛው ወዳጅሽ
ቆርጠሻል መሰለኝ ችዬም አልመልስሽ



°
°
JOIN US👇👇
@getem_besamuel
@getem_besamuel




ካልሰሩ ላይኖር!

#ገጣሚ ብሩክ የገኒ ልጅ (ብሩኬ)

ትግል ነው አለሙ
መነሳት መሰበር
ማፈግፈግ ምንድነው
ለፍቶ ነው መከበር
ሲያዩት ያላማረ
ሲበሉት ያቅራል
አንድ ቀን የሰው ፊት
ማየት ይቸግራል
አትሰስት ጉልበትን
ድካም ከፍ ያረጋል
ካልጠነከሩማ
ሂወት በቀላሉ
መቼ ይበገራል!!



°
°
JOIN US👇👇
@getem_besamuel
@getem_besamuel



ይግለፅሽ ብዕሬ

#ገጣሚ ብሩክ የገኒ ልጅ (ብሩኬ)

ምን ብዬ ልጀምር
እንደምን ልግለፅሽ
ቃል አጣው እናቴ ላንቺ የሚሆንሽ
ለአብራክሽ ክፋይ ሞተሽ የምትኖሪ
በሰሀን ለሠጠሽ በቁና ሰፋሪ
ያንቺ ልፋትማ ሽልማት አይበቃው
የንግስቶች ካባ
ፍቅርሽን ላውራ ብል ይቀድመኛል እንባ
እማዬ እማአለም አያውቅሽ ኩነኔ
አንቺው ነሽ ያለሺኝ ከእግዜር በታች ለኔ
ሰዎች ፍቅር ብለው ደርሰው ቢሯሯጡ
ከእናት በላይ ፍቅር ከወዴት ሊያመጡ
ዘመን የማይሽረው የማይኖረው አቻ
የእናት ፍቅር ብቻ !!!
አዎ እናት አለም ለስቃይሽ ዋጋ
ክፍያ እንደሌለው
የወለድሽው ልጅሽ ይሄን አዋቂ ነው
እንዳይርበኝ ርቦሽ እንዳይጠማኝ ጠምቶሽ
ይደግልኝ ስትይ ደምሽ ጠብ ብሏል
ውለታሽን ዛሬ
ያጠባሽው ጨቅላ አድጎ ይመሰክራል
ዘውድ ነሽ እናቴ ሁሌም የምወድሽ
ከስኬቴ በላይ ዘውትር የማኖርሽ
መስዋት ከፍለሻል ተመን የማይኖረው
እድሜ ልኬን ብኖር ከፍዬ ማልችለው
ፍቅርሽ ቀለቤ ነው ባንቺነት ነው ክብሬ
ያንቺን ገደልማ ባይገልፀውም ቃሌ
ልፃፍ በጥቂቱ ትንሽ ጀማምሬ
ቢያቅተውም አፌ ይግለፅሽ ብዕሬ



°
°
JOIN US👇👇
@getem_besamuel
@getem_besamuel




ከቻልሽ ምላሹን

#ገጣሚ ብሩክ የገኒ ልጅ (ብሩኬ)

መንገድ አየሽ አሉ
ከወደ ልቤ ጋር
ወስዶ የሚያመጣሽ
እውነቱን ሳታውቂው
እንዲው ደጅ ጠናሽ
ልቤ ፀባይ የለው
ቢያንኳኩም አይከፍትም
ጎራ ያለ እንግዳ
ብዙ አይጫወትም
እንዳይመስልሽ እቴ
የሚያዛልቅ ማዶ
መከረኛው ሆዴ
ካንጀቱ ሰው ወዶ
አልመለስ ብለሽ
ብትከርሚ ተይ ስልሽ
ፈትኚው ግዴለም
ልቤም ከተኛልሽ



°
°
JOIN US👇👇
@getem_besamuel
@getem_besamuel



በቃን

#ገጣሚ ብሩክ የገኒ ልጅ (ብሩኬ)

በልተነስ አንበሳው
ቤትህን ደፈሩት
የታገስክ እንደሆን
ከፍራት ቆጠሩት
በቃኝ በል አታንባ
ተጭኖብህ ዝግባ
በደጃፍ ከመሞት
ታግለህ ካፈር ግባ
ነፍጥህን ከፍ አርገው
እንዲታይ ከሩቁ
ስምህ ለጠፋቸው
ጀግና መሆንህን አይተውት ይወቁ
ነገር የከፋ ለት ግማሽ ስጋህ ጎሎ
ውሎ አይሰጥለት ከመጣብህ ምሎ
መመለስ አይኖርም መቀመጥ ዝምብሎ
ሸኘው በመጣበት ይበቃኛል እስኪል
ነገም እንደትናንት
ከድንበርህ ገብቶ ገድያለው ከሚል
ታግል ጎበዜዋ ያታግላል በደል
አሳደህ አስገባው ጨምረው ከገደል
ግፍ እየበዛበት ፍርድ የታጣ ለታ
እምቢኝ ያለ እንደሆን ከታጠቀ አይፈታ
ስበርና ውጣ ጠላት ካጠመደው
ልክ ልኩን ስጠው ክብር ላልወደደው
ታሪክህ ታላቅ ነው ያሚያወሳው ሀገር
ቆርጠህ ከተነሳህ ክንድህ አይበገር
እምቢ በል ያገር ሰው ትግሉን አሳምረው
እምቢ ያለ ሰው ነው ተከብሮ ሚኖረው
ጀምርው ዳርዳሩን ዝለቅ ወደ መሃል
ከቶ ከዚ በላይ ምን ይመጣብሃል
ሴረኛው ተኩላ
ጨርሶ ሊበላህ ጥላ እጥልቶብሃል
መክት በአንድነት
ክብርህ በውሾች ተረግጦ እንዳይጣል
ታገል ለነፃነት ትግል ነፃ ያወጣል



°
°
JOIN US👇👇
@getem_besamuel
@getem_besamuel



ሂወት ውል የሌላት

#ገጣሚ ብሩክ የገኒ ልጅ (ብሩኬ)

ሂወት ትሰጣለች
ደግሞም ትነፍጋለች
አንዱን ስታነሳ
አንዱን ትጥላለች
ኩራዟን ለኩሳ እድል እያዜመች
ሲያሻት ከብርሃን
ስትፈልግ ከጭሱ ታከፋፍላለች
ሂወት እንደዚ ነች
ከቶ ማትገመት ውሏ ያልታወቀ
ድንገቴነቷ ሰው እያሳቀቀ
ጥቁር ስታለብስ ነብስ እየማቀቀ
ያደለች እንደሆን
በሠጠችው ፀጋ ውስጥም እየሳቀ
ግፋ በለው ስትል
ተስፋ እየሰጠች ሆድ የምታባብል
ትንሽ እያሳየች ልብ የምታማልል
ከዚያኛው ቀምታ ለዚኛው መስጠትን
ደርሶ ማደላደል ሁሉን የታካነች
ሂወት እንደዚ ነች
ሂወት እንዳሻት ነች
አዎ በትክክል ቃሉን እመንበት
በሰጠችህ ዛባያ ሳታቆም ዙርበት
ከቶ አታፈግፍግ
ጀርባህን ግረፊኝ ብለህ አታሳያት
ጀግነህ ቁምና ከፊት ተጋፈጣት
ክፉውን ካልወጣህ
ደግን ላታገኘው
ጠንክር ወንድም አለም
አይዞኝ እህት አለም
በርችልኝ እናቴ በል ግፋው አባቴ
ግርፋቷን ፈርቶ ከሩቅ ለሚሸሻት
ገፍታ ብትጥለው ወድቆ ለቀረላት
ቦታ እንኳ የሌላት……………
ሂወት እንደዚ ናት



°
°
JOIN US👇👇
@getem_besamuel
@getem_besamuel



አወይ መሸታ ቤት

#ገጣሚ ብሩክ የገኒ ልጅ (ብሩኬ)

ደስ ያለው የደስታ እያለ ሲጋብዝ
ያዘንው ብቻውን ጠጥቶ ሲተክዝ
ሞቅ ያለው ሲጨፍር ተነስቶ በሆታ
የበቃው ሲወጣ ባሳር በጉተታ
ሌላው ሲበሻሸቅ ቃል እየሸጎጠ
ለቤቱ አዝማሪ ግጥም እየሰጠ
ሆድ ያባው በብቅል ጉዱን ሲዘረግፍ
ዝም ያለው ለወሬ ጆሮን ሲያሰፈስፍ
እከሌ እንዲ ሆነ
ሀገር እንዲ ሆነች
ዜናው እንዲህ አወራ
ሲባል በመሸታው ጨዋታው ሲደራ
ያየው የሰማውን ለጠጪው ሲነግር
ሁሉም ከየአፉ ያለውን ሲገብር
ልክ ነው አይደለም ሲጧጧፍ ክርክር
ከየፓለቲካ አያሌው ሲቃመስ
ደግፍ አትደግፍ ጎራው ሲወቃቀስ
ሃሜቱ እንደጉድ እንደ ውሃ ሲፈስ
ቂም የተያያዘ ነገር ሲመዛመዝ
ቅስሙን የተነካ ለዱላ ሲጋበዝ
አሳላፊ ሲባል መጠጡ ሲቀዳ
ገሚስ አይኑን ሲጥል ሲከጅል ኮረዳ
ተቀበል ሲባባል በጭብጨባ ሲያመሽ
እጅ ይዞ ተነሱ ትከሻ ሲፈተሽ
ለጉድ መንበሻበሽ
ለጉድ መረባበሽ
የሞላበት ቅኔ ከየዘርፉ ያዘለ
አወይ መሸታ ቤት
ምን ያማይወራ የማይታይ አለ

@Lanchisel

°
°
JOIN US👇👇
@getem_besamuel
@getem_besamuel



እረፍት ያጡ ነብሶች

#ገጣሚ ብሩክ የገኒ ልጅ (ብሩኬ)

ገዳይ ሲሞላለት
ካራ ተሸክሞ
በበልፅግ ባይ አቻው
ነፃነት ቢሰጠው
እግር እጁን ስሞ
ሸፍጥ ሲያቀጣጥል
ባልታጠቀ ምስኪን
ታጥቆ ሲያውደለድል
መስዋት ሲያረገን
ሲያስመታን ቸነፈር
ታርደን ስንበሰብስ
አማን ካጣው መንደር
ሰምተው እንዳልሰሙ
ሳያሻቸው ማዘን
አወይ ባለተራ
ባለጊዜ መሆን
ቀባሪ እያሳጡን
ዘውትር ቢበድሉን
በዝሆን ጆሮዋቸው
ዝንብ እያስመሰሉን
ድረሱልን ብንል
ቆመው አስገደሉን
አወቸው መከራ
ያልተገራው ጨቅላ
ሲመዘን ከስሩ
ደም ያበለፅጋል
ሆኑዋል መፈክሩ

#እግዚአብሄር_ይፈርዳል!

@Lanchisel

°
°
JOIN US👇👇
@getem_besamuel
@getem_besamuel



የአባይ ዳር ፍቅር

#ገጣሚ ብሩክ የገኒ ልጅ (ብሩኬ)

ከአባይ ፏፏቴ እግድም ዳር ቤቷ
ታጫውት የለም ወይ ያቺ ልጅ ካንጀቷ
ስቃ ስታስቀኝ ሳቋን ብውድላት
የታደማት አይኔ ቀልቤ ሸፈተላት
ፍቅሯን ስታወጋኝ በአባይ ዳር ጨዋታ
ውስጤን ስታሞቀው በከንፈር ሰላምታ
የወንዙ መግነጢስ እያስተሳሰረን
በሰመመን መንፈስ ስሎ ሲሰውረን
በመውደድ ወላፈን ሀሴት ስንፈጥም
ቃል ስንገባባ ልባችን ሲገጥም
ኧረግ አባይ ፈካ ፍቅር ስናጣጥም
ሳንተያይ ውሎ መሽቶ እዳይነጋ
ፎጣዬን ለብሼ ስበር ወራጁጋ
ቆማ አገኛታለው ጥለቷን ጣል አርጋ
ከእቅፌ ገብታ በራ ስትሸጎጥ
ራስ ይላል ናፍቆቴ ያቃጠለኝ ረመጥ
ያቺ ልጅ ላንድ ቀን ያልመጣች እንደሆን
ጭንቀት በሆዴ ላይ ብሶት ያሳርፋል
ልቤም አይችልልኝ አባይም ያኮርፋል

@Lanchisel

°
°
JOIN US👇👇
@getem_besamuel
@getem_besamuel



የፍቅርሽ መጋኛ

#ገጣሚ ብሩክ የገኒ ልጅ (ብሩኬ)

አዳም ያልከፈተው ንፋስ ያላገኘው
ጎራም ያላሉበት ማንም ያልጎበኘው
እዳው ላንተ ቢለኝ!•••••
ቅደም ስባል ካላይ ፊተኛው ቢያረገኝ
ከማላውቀው ልቧ ከኦናው ሰደደኝ
አንጃለት ነገሬ በጠራራ ፀሃይ
ይበርደኝ ጀምሯል!
ልቤም እየደቃ እንቅጥቅጡም ንሯል
ጠበል አያሽረው የሌለው መፍትሄ
በቀረብኝ ነሮ.........
ልቤን ባላሳትፍ ከልቧ ጉባኤ
አልችለው ብል ፍቅሯን እያንገበገበኝ
ውልብኝ እንደበላ እያውለበለበኝ
ቆማ ከደጃፏ ፈዛ እያየችኝ
ምነው ምን ባጠፋው?
በፍቅሯ መጋኛ ጨክና አስመታችኝ
መቼም ሆኖልሻል.......
እኔነቴ ሞላው ተንበርክኮልሻል
ሳይቸግር ሲያቀብጠኝ ውስጥሽ ተነክሬ
መላ አጣው መውጫውን ከዳኝ ጥንካሬ
ልቤ ነጋሪቱን ሲደልቅ ይውላል
በይ መተሽ አቁሚው መፈንዳት ከጅሏል



°
°
JOIN US👇👇
@getem_besamuel
@getem_besamuel



ይታሰባል በሆድ!

#ገጣሚ ብሩክ የገኒ ልጅ (ብሩኬ)

ሆድ በነገሰበት
ስም በሌለው አለም
ጭንቅላት ተይዞ
ባዶ ሲሆን ቀለም
አዕምሮ ተርቦ
ምነው አጉራሽ የለም?
ሆድ እየተሞላ
ይኖራል ዘላለም!

@Lanchisel

°
°
JOIN US👇👇
@getem_besamuel
@getem_besamuel




ክብር ያጣው ውለታ

#ገጣሚ ብሩክ የገኒ ልጅ (ብሩኬ)

ላይሽር ጠባሳዬ
አርገው በበደሉኝ
ደስታን አሳጥተው
ሃዘን ባሸከሙኝ
ሃገሬን ሲገፏት
ዘብ እየሆንኩላት
ክደው እስኪበሉኝ
መስዋት ሆኜላት
ደሜን አፍስሼበት
ቆሜ ስለክብሯ
ቃላት ባማይገልፁት
ላንገብጋቢው ፍቅሯ
ሞቼ ባመጣሁት
ድሏን በአጥንቴ
ገደል ሲሰዱብኝ
ያን ሁሉ ልፋቴ
ነፃ ብለው ሸኙት
ደስ አለው ጠላቴ
ደርሶ ላሳረደኝ
ክብርን ከሰጡት
ልጣል መለዮዬን
አሁን ነው የሞትኩት

#ውለታቢሶች

@Lanchisel

°
°
JOIN US👇👇
@getem_besamuel
@getem_besamuel





አድዋ

#ገጣሚ ብሩክ የገኒ ልጅ (ብሩኬ)

የጥቁሮች ኩራት የሀበሻ ገድሉ
ነጭን ያዋራደ በወርቃማው ድሉ
በአይቀጡ ቅጣት አለም ያስደነቀ
ለጭቁኖች ፋና ብርሃን ያፈለቀ
የእምዬ ዘሮች ነብስን የገበሩ
ደማቸውን ሰጥተው ሀገር ያስከበሩ
እኒያ ባለወኔ ልበ ደፋር ጀግኖች
ታሪክን ሰርተዋል ዛሬ ላሉት ስሞች
ከምስራቅ ፣ ከምዕራብ
ከሰሜን ፣ ከደቡብ
በአንድ የዘመቱ የኢትዮጲያ ልጆች
ሀገር ስትደፈር የነደዱ ልቦች
ድልን ያወረሱ አሁን ላለን ህዝቦች
ምስክር ተራሮች...!
ሶሎዳ ተራራ ሲከተም ለጠላት
የማሪያም ሸዊቶ ቁልቁለት አቀበት
በአዲ ተቡን ግንባር ከፊት ሲዋደቁ
በእግዚሃር አሳየኝ ሱሬ ሲያሶልቁ
ይመስክር ተራራው!
ያንበረከክንበት ነጭን ከነ ጎራው
አወይ የዛን ግዜ አወየው ክተት
እናት ስትነካ ያልተፈራው ሞት
አንገት የሰጡበት ድንበር ላለፉት
በደማቅ ተፅፏል ከታራኮች አውራ
የምኒልክ ጀብዱ የጣይቱ ስራ
የባልቻ አይፈሬነት የሺዎች ፉከራ
ሠራዊት ፈረሱ ሲበር እንዳሞራ
የጋሻውን እምብርት በመሬት ሲያጠቅሰው
ጎራዴውን ባየር ደርሶ እየቀዘፈው
በቆረጠ ቁጣ በሚሳብድ መንፈስ
ወራሪን ከስሩ.........
ደባለቁት ካፈር ሀሞቱ እስኪፈስ
ድል ተጎናፀፉ ዳግማዊ ከበረ
ቀኙን ስለሠጠው ቆሞ በአንድ እግሩ
በእንዳማርያም ላይ..........
ምስጋና አቀረበ ለታላቅ እግዜሩ
አድዋ..... አድዋ..... ጠላት ያፈረበት
የኢትዮጲያዊን ኩራት
ያፍሪካዊያን ኩራት

@Lanchisel

°
°
JOIN US👇👇
@getem_besamuel
@getem_besamuel





ችኩል ነው ልቦናሽ

#ገጣሚ ብሩክ የገኒ ልጅ (ብሩኬ)

መውደዴ ሳይንስሽ
ቅሬታሽ አይሎ ካሰኘሽ የበታች
ነገርኩሽ አለሜ.......
ፍላጎትሽ ንሮ ሁዋላ እንዳንሰላች
ቀን እየቆጠርኩ......
ልብሽን ከልቤ እያበጀው ግማድ
ጉንጉን እንዳትፈቺ ባልበቃኝም ልማድ
ያላየሽው ልቤ.........
መውደድን ያዘለው ካንቺነትሽ ዘንዳ
ሌላም አያቅተው ምነው ሰጋሽ ታዲያ
ሰከን ብሎ ልብሽ ታግሶ ከዋለ
ምን ችግር ሆድዬ........
ይሰረኝ ከልብሽ ፍቅር ከተሻለ!

@Lanchisel

°
°
JOIN US👇👇
@getem_besamuel
@getem_besamuel

20 last posts shown.

98

subscribers
Channel statistics
Popular in the channel