✨✨✨ እንኳን አደረሳችሁ !!! ✨✨✨
⚜️⚜️⚜️ መዝሙር ዘዘወረደ ሰንበት ⚜️⚜️⚜️
ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ወተሐሠዩ ሎቱ በረዓድ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ ባዑ ቅድሜሁ በተጋንዮ ወውስተ አዕፃዲሁ በስብሐት እመንዎ (እ) ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ ወንትፋቀር በበይናቲነ (እ) አክብሩ ሰንበተ ተገበሩ ጽድቀ እስመ ሰንበትሰ በእንተ ሰብእ ተፈጥረት (እ) ምሕረተ ወፍትሐ አሐሊ ለከ እዜምር ወዕሌቡ ፍኖተ ንጹሐ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ አባግዓ መርዔቱ።
⚜️ ምስባክ አመ ፲፮ ለወርኃ የካቲት ሰንበተ ክርስቲያን ወበዓለ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት
ዘነግህ
መዝሙር ፻፲፪ ቁጥር ፱-፲
ዘያነብራ ለመካን ውስተ ቤቱ ፤
ወያስተፌሥሓ ለእመ ውሉድ ፤
ዘያነብራ ለመካን ውስተ ቤቱ ።
ዘቅዳሴ
መዝሙር ፪ ቁጥር ፲፩ - ፫፪
ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ፤
ወተሐሠዩ ሎቱ በረዓድ ፤
አጽንዕዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመዓዕ እግዚአብሔር ::
⚜️ የዕለቱ ወንጌል
ዘነግህ
የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፭ - ፲፰
በትምህርት እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል ትምህርታዊ ጽሑፍ ዝግጅት ንዑስ ክፍል የቆሎ ተማሪ የቴሌግራም መርሀ ግብር ዝግጅት ክፍል የቀረበ።
▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬
የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥 @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን
⚜️⚜️⚜️ መዝሙር ዘዘወረደ ሰንበት ⚜️⚜️⚜️
ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ወተሐሠዩ ሎቱ በረዓድ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ ባዑ ቅድሜሁ በተጋንዮ ወውስተ አዕፃዲሁ በስብሐት እመንዎ (እ) ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ ወንትፋቀር በበይናቲነ (እ) አክብሩ ሰንበተ ተገበሩ ጽድቀ እስመ ሰንበትሰ በእንተ ሰብእ ተፈጥረት (እ) ምሕረተ ወፍትሐ አሐሊ ለከ እዜምር ወዕሌቡ ፍኖተ ንጹሐ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ አባግዓ መርዔቱ።
⚜️ ምስባክ አመ ፲፮ ለወርኃ የካቲት ሰንበተ ክርስቲያን ወበዓለ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት
ዘነግህ
መዝሙር ፻፲፪ ቁጥር ፱-፲
ዘያነብራ ለመካን ውስተ ቤቱ ፤
ወያስተፌሥሓ ለእመ ውሉድ ፤
ዘያነብራ ለመካን ውስተ ቤቱ ።
መካኒቱን በቤት የሚያኖራት፥ ደስ የተሰኘችም የልጆች እናት የሚያደርጋት።
ዘቅዳሴ
መዝሙር ፪ ቁጥር ፲፩ - ፫፪
ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ፤
ወተሐሠዩ ሎቱ በረዓድ ፤
አጽንዕዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመዓዕ እግዚአብሔር ::
ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፥
በረዓድም ደስ ይበላችሁ።
ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቈጣ እናንተም በመንገድ እንዳትጠፉ፥ ቍጣው ፈጥና ትነድዳለችና።
⚜️ የዕለቱ ወንጌል
ዘነግህ
የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፭ - ፲፰
በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ ሚስቱም ከአሮን ልጆች ነበረች ስምዋም ኤልሳቤጥ ነበረ።
ሁለቱም በጌታ ትእዛዝና ሕግጋት ሁሉ ያለ ነቀፋ እየሄዱ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ።
ኤልሳቤጥም መካን ነበረችና ልጅ አልነበራቸውም ሁለቱም በዕድሜያቸው አርጅተው ነበር።
እርሱም በክፍሉ ተራ በእግዚአብሔር ፊት ሲያገለግል እንደ ካህናት ሥርዓት ወደ ጌታ ቤተ መቅደስ ገብቶ ለማጠን ዕጣ ደረሰበት። በዕጣንም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ በውጭ ቆመው ይጸልዩ ነበር። የጌታም መልአክ በዕጣኑ መሠዊያ ቀኝ ቆሞ ታየው።ዘካርያስም ባየው ጊዜ ደነገጠ፥ ፍርሃትም ወደቀበት።መልአኩም እንዲህ አለው። ዘካርያስ ሆይ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ።ደስታና ተድላም ይሆንልሃል በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል።
በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም ገናም በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ይሞላበታል ከእስራኤልም ልጆች ብዙዎችን ወደ ጌታ ወደ አምላካቸው ይመልሳል።እርሱም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል።ዘካርያስም መልአኩን። እኔ ሽማግሌ ነኝ ምስቴም በዕድሜዋ አርጅታለችና ይህን በምን አውቃለሁ? አለው።
ዘቅዳሴ
ዮዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲ - ፳፭
ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። አንተ የእስራኤል መምህር ስትሆን ይህን አታውቅምን
እውነት እውነት እልሃለሁ የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን ምስክራችንንም አትቀበሉትም።ስለ ምድራዊ ነገር በነገርኋችሁ ጊዜ ካላመናችሁ ስለ ሰማያዊ ነገር ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው።
ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና።በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።ብርሃንም ወደ ዓለም ስለ መጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለ ወደዱ ፍርዱ ይህ ነው።ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም እውነትን የሚያደርግ ግን ሥራው በእግዚአብሔር ተደርጎ እንደ ሆነ ይገለጥ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል።ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ይሁዳ አገር መጣ በዚያም ከእነርሱ ጋር ተቀምጦ ያጠምቅ ነበር።ዮሐንስም ደግሞ በሳሌም አቅራቢያ በሄኖን በዚያ ብዙ ውኃ ነበርና ያጠምቅ ነበር እየመጡም ይጠመቁ ነበር ዮሐንስ ገና ወደ ወኅኒ አልተጨመረም ነበርና።ስለዚህም በዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና በአይሁድ መካከል ስለ ማንጻት ክርክር ሆነ።
በትምህርት እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል ትምህርታዊ ጽሑፍ ዝግጅት ንዑስ ክፍል የቆሎ ተማሪ የቴሌግራም መርሀ ግብር ዝግጅት ክፍል የቀረበ።
▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬
የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
📥 @gibigubae_hasab_bot ጻፉልን
🏷 @gibigubae ተከታተሉን
📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን