Forward from: AGAPE GLC
🦅 እንደ ንስር 🦅
፨ አንድ ሲደመር አንድ የትም ሆነን ብንደምረው ውጤቱ ሁለት መሆኑ እውን ነው። አማኝም ውጤቱ ያማረ እንዲሆን የሚያስገባው የእግዚአብሔርን ቃል መሆን አለበት። እግዚአብሔርን በመተማመን መጠበቅ በሚል ርዕስ ከንስር ህይወት ጋር በማነፃፀር የአማኝ ህይወት በከፍታ እንዲኖር የሚያደርገው ይህ እንደ ንስር የተሰኘው አስደናቂ ትምህርት በአጭሩ እነሆ.....
ፍጥረታትን ሁሌጊዜ ስንመለከት እግዚአብሔር ግልፅ ሆኖ ይታያል። የንስርም ህይወት በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ የክርስትያንን ህይወት ወክሎ ቀርቧል።
🦅 ንስር አስገራሚ ፍጡር ሲሆን በዕብራይስጥ 'ነሽር' ማለት ሲሆን ትርጓሜውም አፉ ላይ ባለው መንቁር የሚበጣጥስ፣ የሚዘለዝል ማለት ነው። ንስር በመላው አለም የጥንካሬ፣ የነፃነት፣ የውበት እና የሥልጣን ምሳሌ ተደር ይወሰዳል።
ንስር በአዕዋፋት አለም ላይ ንጉስ ነው። ነገር ግን 40ዓመት ሲሆነው ከባድ የሆነን ውሳኔ ይወስናል። ውሳኔውም ለ150 ቀን የሚፈጅ ነው። ይህ ውሳኔ ለቀጣዩ 30 አመት ለመኖር መሰረት ነው።
ከባዱም ውሳኔ የአፉን ጥፍር (መንቁር)፣ የእግሩን ጥፍር ከአለት ጋር በማጋጨት ያወልቀዋል። በመቀጠልም ከጊዜ በኋላ የሰውነቱን ላባ በሙሉ በመንቀል እና በማስወገድ እራሱን በከባድ ለውጥ ውስጥ ያስገባል።
ይህን ማወቅ ለምን አስፈለገ ❓
በተመሳሳይ መልኩ አማኝ ህይወቱ ላይ ያለውን የማይጠቅመውን እና የተጣበቀውን ነገር በእግዚአብሔር ቃል ማስወገድ ይችላል።
🦅 የንስር አስደናቂ ማንነት ከአማኝ ጋር ሲነጻጸር፦
1. ክንፉን ሳያወዛውዝ መብረር ይችላል
- ንስር የነፋስን ፍሰት በመጠበቅ ያለምንም ችግር ይበራል። አማኝም የመንፈስን ፍሰት ጠብቆ ያለ ትግል መኖር ይችላል።
2. ንስር ከሌሎች አእዋፋት ጋር አይቀላቀልም
- ንስር ከሌሎች ወፎች ጋር አብሮ አይበርም፤ አይኖርም። አማኝም በክርስቶስ ምርጥ፣ ንጉስ፣ ካህን፣ ቅዱስ ህዝብ መሆኑን በመረዳት በከፍታ እንዲኖር ማሳያ ነው።
3. ንስር ከተወለደ በኋላ ከፍተኛ ረሀብ ይዞ ነው የሚወለደው
- ንስር በጣም የሚበላ ሲሆን አማኝም ከተወለደ በኋላ ንፁህ የሆነውን የቃሉን ወተት መመገብ አለበት። ንስር የሞተ ነገር አይበላም። አማኝም ለአይናችን እና ለጆሮአችን የምንመግበውን ነገር መምረጥ አለብን።
4. ንስር ከ3ኪ.ሜ ርቀት ያለውን ነገር ያያል
- አይኑ አጥርቶ የሚያይ ሲሆን ሁለት የአይን ብሌን አለው። አንዱ ፀሀይን ትኩር ብሎ ሲመለከት በተመሳሳይ መልኩ የሚያድነውን ያያል። አማኝም የስጋ አይኑ ግዑዙን ዓለም እንዲያይ፣ መንፈሳዊ አይኑ ደግሞ እግዚአብሔርን እና በቃሉ ውሰጥ ያለውን መገለጥ ትኩር ብሎ እንዲያይ ተሰጥቶታል።
5. የንስር የጋብቻ ህይወት
- ሴቷ ንስር ወንዱን ለጋብቻ ከመቀበሏ በፊት ቅድመ ሁኔታዎች አሏት። አማኝ በተመሳሳይ መልኩ ምን ያህል ጌታን መዉደድ፣ ቃሉን መውደድ፣ ህይወት ላይ ያለ ዓላማ፣ መስጠት፣ ታማኝነት እና በመንፈስ መመራት ለጋብቻ ትልቁ ቅድመ ሁኔታ መሆን አለበት።
6. ንስር ማዕበልን ይወዳል
- የአውሎ ነፋሱ ማዕበል ንስርን ሁሌም ወደተለየ ከፍታ ያወጣዋል። ለአማኝ ችግር መውደቂያው ሳይሆን ማድመቂያውና የዕድገቱ ምክንያት ነው።
ለችግር እንዴት ምላሽ እንስጥ?
፩. በእግዚአብሔር መታመን/መደገፍ
፪. እግዚአብሔርን ማምለክ
፫. ችግሩ የመጣበት ምክንያት ለእኛ ለመልካም ሊደረግ እንደሆነ በመረዳት
፬. ፈተና ወደ ምስክርነት እንደሚለወጥ በመረዳት
🦅 ንስር ቤቱን የሚሰራው በከፍታ ሲሆን ልጆቹንም ከትልቅ ከፍታ በመወርወር መብረርን ያለማምዳሉ። አማኝም እምነታችንን ተለማምደን መንፈሳዊ ህይወታችንን ማሳደግ ይኖርብናል። ሁልግዜ ቃሉ ላይ ተቀምጠን የመንፈሱን ፍሰት በመጠበቅ ከነገሮች ሁሉ በላይ ሆነን በከፍታ ህይወት እንድንኖር የሚያደርግ ድንቅ ትምህርት ስለሆነ እንደ ንስር የሚለውን ሲዲ በመስማት እና ሙሉ ሀሳቡን (ትምህርቱን) በማግኘት ሕይወትዎን በእግዚአብሔር ቃል እውነት ይለውጡ!
ብሩካን ናችሁ !
_____________
“እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።”
— ኢሳይያስ 40፥31
🦅 እንደ ንስር 🎧
◇ የ20 ሰዓት mp3
💎በሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ
Get Your Copy!
☆ ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ አንድ ቃል ሕይወትዎ ለዘላለም ይለወጣል።
👉 @AgapeGLC
@AgapeGLC