አንድ የ30 አመት ጎልማሳ ብዙ ከወላወለ በኋላ እድሜ ልኩን ሲመኘው የነበረን የምህንድስና ትምህርት ለመማር ለምዝገባ ወደ አንድ ኮሌጅ ሄደ፡፡ ቢሮ እንደገባ የተማሪዎች አማካሪ አገኘውና ሲያማክረው “በመማርና ባለመማር መካከል ብዙ ወላውያለው ” አለው፡፡
አማካሪው ምክንያቱን ሲጠይቀው፣ “አሁን 30 አመቴ ነው፡፡ ስመረቅ እኮ 35 ሊሆነኝ ነው” በማለት የመወላወሉን መነሻ ምክንያት ነገረው፡፡
አማካሪው የመለሰለት መልስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ትምህርት ገፋው፡፡ “የዛሬ አምስት አመት እኮ ብትማርም ሆነ ባትማር 35 አመት መሙላትህ አይቀርም፡፡ ሳትማር 35 አመት ከሚሞላህ፣ ተምረህ ቢሞላህ አይሻልም?”
እስቲ አንድ ጊዜ ጸጥ በሉና እድሜያቹ ስንት እንደሆነ አስቡት፡፡ ከዚያም በአሁኑ እድሜያቹ ላይ አምስት አመት ደምሩበት፡፡ ድምሩ ስንት መጣ?
ብትማሩም ባትማሩም እድሜያቹ መጨመሩ አይቀርም ሳትማሩ እድሜያቹ ከሚጨምር ተምራቹ እድሜያቹ ቢጨምር የተሻለ ነው ።
በሉ ተንቀሳቀሱ!!
@heppymuslim29