የፖሊስ የደንብ ልብስ በመልበስ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ወርቅ የሰረቁ ተጠርጣሪዎች ከነኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር ዋሉ።
በርኖስ ሚዲያ /ህዳር /10/2013 ዓ.ም
የግል ተበዳይ አቶ አቤል አሰፋ ህዳር 4 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ገደማ ፖሊሶች ነን ያሉ ግለሰቦች በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ራስ መኮንን ድልድይ አካባቢ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው መጥተው በር እንዲከፍቱላቸው ሲጠይቋቸው ማንነታችሁን ሳላረጋግጥ እና ለቤተሰቦቼ ሳላሳውቅ አልከፍትም ማለታቸውንና ከዚያም ፖሊስ ነን ያሉት ግለሰቦች ተጨማሪ ሃይል ያስፈልገናል እያሉ እየተነጋገሩ ወደመጡበት እንደተመለሱ ተናግረዋል፡፡
ይሁን እንጂ የግል ተበዳይ አቶ አቤል ቀን ወደ ስራ ከሄዱ በኋላ ተጠርጣሪዎቹ ከቀኑ 9 ሰዓት ሲሆን የፖሊስ የደንብ ልብስ ለብሰው እና ሽጉጥ ታጥቀው ተመልሰው በመምጣት « አቶ አቤል ወንጀል ሰርተው ስለታሰሩ እኛ ቤታቸውን ልንበረብር ነው የመጣነው » ብለው ለጎረቤት ከተናገሩ በኋላ የተቆለፈውን በር ሰብረው በመግባት በካዝና ውስጥ ለንግድ አገልግሎት የተቀመጡ አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሺህ ብር ግምት ያላቸውን የወርቅ ጌጣጌጦች ሰርቀው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 4-20411 አ.አ በሆነ ፒካፕ ተሽከርካሪ ጭነው መውሰዳቸውን የግል ተበዳይ ገልፀዋል፡፡
በአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የጃንሜዳ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ለውጥአየሁ ከበደ እንዳስረዱት የወንጀሉ መፈፀም ሪፖርት የደረሰው ጣቢያው የምርመራ እና የክትትል ቡድን በማቋቋም እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የክትትል ክፍል ጋር በመቀናጀት ውጤታማ ስራ ተሰርቷል፡፡
የፈፃሚዎቹን ማንነት ለማወቅ ቀን እና ለሊት በተደረገው እልህ አስጨራሽ ክትትል ካዝናውን ጭኖ የተሰወረውን ተሽከርካሪ፣በወንጀሉ ተሳትፈዋል የተባሉ 5 ተጠርጣሪዎችን፣ ለወንጀል ተግባር ሲጠቀሙባቸው የነበሩ የፖሊስ የደንብ አልባሳት፣ሽጉጥ፣ ካቴና እና ስለቶችን በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለ፣ የፖሊስ የደንብ አልባሳቱንም ከየት አምጥተው እንደለበሱ የማጣራት ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ዋና ኢንስፔክተር ለውጥአየሁ ከበደ ተናግረዋል፡፡
የተሰረቁት ወርቆች በ600 ሺ ብር ለሌላ ግለሰብ ተሽጠው እንደነበር ያስታወሱት ምክትል ኢንስፔክተር ሄኖክ የተሸጡት ወርቆች መርካቶ አካባቢ እንደተገኙ እና ገዢውም በቁጥጥር ስር እንደዋለ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
ፖሊስ ቀንና ለሊት ደክሞ በመስራትና ተጠርጣሪዎቹን አውቆ በመያዝ ያከናወነው ተግባር እንዳስደሰታቸው የግል ተበዳይ አቶ አቤል አሰፋ ተናግረዋል፡፡
ምርመራውን ለማስፋት በተደራጀ መንገድ እየተሰራ ነው ያሉት ዋና ኢንስፔክተር ለውጥአየሁ ከበደ ፖሊስ ሳይሆኑ የፖሊስ የደንብ ልብስ ለብሰው ወንጀል የሚፈፅሙ እና የከተማችንን ፀጥታ ለማደፍረስ የሚንቀሣቀሱ ግለሰቦች በመኖራቸው ህብረተሰቡ መታወቂያ በመጠየቅም ሆነ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ስልክ በመደወል ህጋዊነታቸውን ሊያረጋግጥ እና አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙም ለሚመለከተው አካል ሊያሳውቅ ይገባል ብለዋል፡፡
የፀጥታ አካላትን የደንብ ልብስ በመልበስ ለስራ ጉዳይ በሚል ምክንያት ወደተለያዩ መኖሪያ ቤቶች እና ተቋማት የሚሄዱ ግለሰቦችን ማንነት መለየት እና ማረጋገጥ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ማሳሰቡ ይታወሳል ብሏል ኮሚሽኑ።