🧲የብልህ_አባት_እና_ልጅ_ወግ🧲
ልጅ፦ አባዬ ከእንግዲህ በቃኝ መስጂድ ሁለተኛ አልመጣም።
አባት፦ ምን ነው ልጄ? ምን ተፈጠረ ?
ልጅ፦ መስጅድ የሚመጡ ምዕመናን ግማሹ
ስልካቸውን ይነካካሉ ግማሾቹ በሃሜት የሰውን ስም እያነሱ ያወራሉ እዚህ መምጣቱ ጥቅሙ
አልታየኝም።
አባት፦ መልካም ልጄ! ከውሳኔህ በፊት አንድ ነገር ብቻ ላስቸግርህ ?
ልጅ፦ እሺ አባዬ ምንድን ነው ?
•
•
•
አባት፦ በብርጭቆ ውሃ ሞልተው እያቀበሉት ይሄን ውሃ ምንጣፍ ላይ ሳይንጠባጠብ አንድ
ጊዜ መስጂዱን ዞረህ ተመለስ።
ልጅ፦ እሺ በማለት የብርጭቆውን ውሃ በእጁ በጥንቃቄ በመያዝ በእርጋታ መራመድ
ጀመረ።
ዙሩንም አጠናቆ ወደ አባቱ ዘንድ በመመለስ ብርጭውቆን አስረከበ ..
•
አባት፦ ልጄ ሆይ! ስልክ የሚነካኩ ሰዎችን ተመለከትክን ?
ልጅ፦ አልተመለከትኩም አባዬ።
አባት፦ ሰዎች የሌሎችን ስም አንስተው ሲያሙ ሰማክ ?
ልጅ፦ አልሰማሁም።
አባት፦ ለምን ?
ልጅ፦ የያዝኩት የብርጭቆ ውሃ እንዳይንጠባጠብ ብርጭቆውም ወድቆ እንይዳሰበር ሙሉ
ትኩረቴን በጠቅላላ እሱ ላይ አድርጌ ስለነበር ሌሎችን አልታዘብኩም።
አባት፦ አየህ ልጄ መስጂድ ውስጥ ሙሉ ትኩረትህን ወደ ፈጣሪያችን ወደ አሏህ ካደረግክ
ሰዎችን ለመታዘብ ጊዜ አይኖርህም።
★ [ሱበሃን አሏህ] ምንኛ ያማረ ምክር ነው