‼️‼️ወንድሜ ሆይይይይ‼️ ለነገሩ ሴቶችም አሉበት ለካ⁉️
ሴቶችም የጀመሩ ስላሉ ነው። አላህ አቅል ይስጥሽ። ላንተም‼️ ላንቺም‼️
የዛሬ ዘጠና ደቂቃህ ያባከንካት ነገ አላህ ፊት ስትቆም መልስ አዘጋጅተሃልን⁉️ ወጣትነትህ በምን አሳለፍከው ተብለህ ሳትጠየቅ እግር ንቅንቅ የለም። (ታውቃለሃ??) ታዳ "ዲ'ኤስ'ቲቪ" እያየሁ: ወይስ አይ "ሲኒማ ነበርኩ" ወይስ ምን ላይ⁉️
አትዋሸውም/አታመልጠውም‼️ (ነገሩ ለአባትህ:ለመ/ርህ: ለጓደኛህ አይደለም እኮ ምትዘረዝረው። እወቅ (ያ- የውስጥ/የቅርቡ የሩቁንም አዋቂው ለአላህ ነው ምትነግረው። ታዳ መልስህ ምንድነው⁉️
ሲቀጥል ኳስ ማየት ኻራም ነው። የሴቶችም የወንዶችም: ለወንዶችም ለሴቶችም; ምክንያቱም:-
አውራቸው ይታያል: ጊዜያችን ያባክኑብናል: ምንም ነገር ስለማይጠቅመን, በሸሪያ በማይጠቅም በማይጎዳ ነገር ዘው ብሎ መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው። አይምሮዋችን ስለሚቆጣጠሩብን: ኳስ አፍቃሪዎች የሸሪዓ/የእስልምና ህግጋቶ ለመሃፈዝ በጣም ሲቸገሩ እናያለንና።
እኔ የማውቀው ሰው አለ።‼️
የእግር ኳስ ክለቦች ብዙዎችን የሚያውቅ: ብዙ ይዘረዝራል።
ተጫዋቾች ሁሉም የሚያውቅ: ግን የነብዩ "ሰለላሁአለይሂወሰለም" ስም ከነ-አያታቸው የማያው አውቃለሁ።
እና ከዚህ አሲድ (acid) ከሆነው ኳስ በላይ ወጣቶችን ያባከነ: ያከሰረ አለን⁉️
ምናልባት አንዳንድ እህቶች በፊልም ከዚህ የሚብሱም ቢኖሩም...!
እና አላህን እንፍራ ጊዜያችን በአግባቡ እንጠቀም። እንማር የተማርነውን እናስተምር።
(ከኡስታዜ ሳዳት:- አላህ ወፍቆህ 30 አመት ቢያቆይህ 5 አመት ቁጭ ብለህ ብትማር 25 አመት ሙስሊሞችን ትጠቅማለህ።)
ይቀጥላል:- (የምታወቀውን/የተማርከውን ሳትቀንስ ሳትጨምር አሰራጭ።) ይላል። ሃፊዘሁላህ
ሃቂቃ ይህ ንግግር ላስተነተነው በውስጡ ብዙ ትርጉሞች ይዟል። እና ጊዜ ሂወት ነው። አንዴ ከሄደ የሚይመለስ።
አላህ ለኔም ለናንተም ያግራልን።
✍الياس
ለተጨማሪ ፅሁፎች ይቀላቀሉ።
👇
Share Share & join channel
https://t.me/iliyasNassir@iliyasNassir