በአንድ ወቅት ስሙ የገነነው ታላቁ ፈላስፋ ዲዮጋን አለምን ከሞሏት ሚሊዮኖች ሰዎች ውስጥ ሰው ፈልጎ ቢያጣባት በየገበያውና በየሰርጣ ሰርጡ በቀን በጠራራ ጸሀይ ወጣ።
የቀን ጋኔን፣ የአለምን ማጋነንና ሃሜት ሳይፈራ ፋኖሱን አብርቶ ሰው ፍለጋ ጀመረ። ግን ዲዮጋን የፋኖሱን መብራት በላዩ አብርቶ ራሱን ተመልክቷል? ራሱን ሰው አድርጎ ነው ሰው ፍለጋ የወጣው? በአለም ፈልጌ አንድ ሰወ አጣሁ ያለውስ ራሱም ሰው ሆኖ አልተገኘም ይሆን? በርግጥ በዛን ዘመን በአለም ከነበሩ ሚሊዮኖች አሊያም መቶ ሺዎች አሁን ላይ በራሱ ከቢሊዮኖች ውስጥ ሰውን ማግኘት ከባድ ሆኗል፤ ሰው የሆነን ሰው ከመፈለግ የማያልቀውን ህልቁ መሳፍርት መላው ዩኒቨርስን አርሶና አዳርሶ፤ አረስርሶ መጨረስ ይቀላል።
እያንዳንዳችን ሰው ለመሆን የምንሞክር የሰው ምስል ፎቶ ነን እንጂ 8 ቢሊዮን ህዝብ አለምን አልሞላትም።
በኢየሩሳሌም የነገሰው ንጉሥ "ንጉሥ ዳዊት " ለልጁ ኑዛዜ ሲያስተላልፍለት "ልጄ ሆይ ሰው ሁን!" ነው ያለው።
ወደ ሰውነት ጉዞ መጀመር አለብን ባይ ነኝ። የስታቲስቲክሱን ነገር ለጊዜው ወደጎን ብለነው "በቁጥር አለም ይህን ያህል ሰው ያዘች " ብለን ከመለፈፋችን አስቀድመን ሰው የሆነና ሰው ያልሆነውን እንደ ዲዮጋን ማሿችንን ከራሳችን ጀምረን እያበራን "የሰው ያለህ" ማለት ይገባናል።
የሀይማኖት ተቋማት በእኛ እምነት የሚያምኑ "ሚሊዮኖች " አሉ ብለን ከመደስኮራቸንና ቁመት ከመለካካታችን አስቀድመን " ሰው" የተባለውን ፍጡር ከጥልቁ ጨለማ አስሰን ማግኘትና ሰውነትን ማጎልመስ ይገባናል ከሚሉት ነኝ።
✍️ዮዳA
7:15ሌ
27/8/2015ዓ.ም
https://t.me/danielaweke