TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
English
Site language
Russian
English
Uzbek
Sign In
Catalog
Channels and groups catalog
Search for channels
Add a channel/group
Ratings
Rating of channels
Rating of groups
Posts rating
Ratings of brands and people
Analytics
Search by posts
Telegram monitoring
©Legal details center© :የህግ ማብራሪያ ማዕከል©
5 Jan, 13:24
Open in Telegram
Share
Report
ባልና ሚስት በየስማቸው የተመዘገቡ መኖሪያ ቤቶች የግል ንብረታቸው እንዲሆኑ በጋብቻ ውል ተስማምተዋል። ሁለቱም ቤቶች የሚገኙት አማራ ክልል ነው። ጋብቻ ውስጥ እያሉ አዲስ አበባ ላይ ቤት መግዛት ፈለጉና አንድ ዘዴ ዘየዱ። ይኸውም በባል ስም የተመዘገበውና የባል የግሉ የሆነው መኖሪያ ቤት ተሸጦ አዲስ አበባ ላይ ለኮንዶሚኒየም መግዣ እንዲውል: በተጨማሪም ይኸው የተገዛው ቤት እና በሚስት ስም ተመዝግቦ ያለው የሚስት የግል ንብረት ሁለቱም የጋራ ንብረቶቻቸው እንዲሆኑ ተስማሙ።
በዚህ መሰረት የባል ቤት ተሸጠና አዲስ አበባ ላይ ቤት ተገዛበት። በመቀጠል ባልና ሚስት ስምምነታቸውን በፍርድ ቤት ለማፀደቅ በዝግጅት ላይ እንዳሉ ሚስት ቀድማ "ትዳር በቃኝ" አለችና ፍቺ ጠየቀች። ፍቺ በፍርድ ቤት ተወሰነ።
ቀጥሎ የንብረት ክፍፍል ጥያቄ ቀረበ። ንብረቱ እንዴት ነው መካፈል ያለበት?
ያው አዲስ አበባ ያለው ቤት የግል ንብረት ተሸጦ በግብይት የተገኘ ስለሆነና በባል በኩል የግል ይባልልኝ አቤቱታ ቀርቦ በፍርድ ቤት ስላልፀደቀ የጋራ ንብረት ነው።
በሚስት ስም የተመዘገበው ንብረት ደግሞ አስቀድሞ በጋብቻ ውል የሚስት ስለሆነ የግል ንብረቷ ነው።
እርግጥ ነው በመካከላቸው ስምምነት ነበር። ግን በፍርድ ቤት ቀርቦ አልፀደቀም።
ግልፅ ሆኖ አንደኛው ወገን በህጉ ክፍተት በልፅጓል።
ግን ደሞ በሌላ መልኩ ፍትሐዊ ውሳኔ መስጠት የሚቻልበት መንገድ አለ?
792
0
2
1
×