ዘፈን በቤተ ክርሰቲያን አስተምህሮ
ክፍል 2
ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያን ለምን ዘፈንን አወገዘች ?
💐💐💐💐💐💐💐
1. ዘፈን የአጋንንት ሥራ ነው:: አጋንንት ይዘፍናሉና:: ለዚህ ምንም ማስተባበያ አያስፈልገውም:: መጽሐፍ ቅዱስ "በዚያም አጋንንት ይዘፍናሉ" በማለት ስለ አጋንንት ዘፋኝነት ይናገራል::(ኢሳ.13:21) አትዝፈኑ ማለት የአጋንንትን ሥራ አትሥሩ ማለት መሆኑን እንረዳ:: ይህን በተመለከተ መጽሐፈ መቃብያን ደግሞ እንዲህ ይላል:-
"....እየዘፈኑም ከአጋንንት ጋር ይጫወቱ ነበር:: አጋንንትም ጫወታቸውንና ዘፈናቸውንም ሁሉ ያደንቁላቸው ነበር::" (1ኛ.መቃ.36፥27-28)
በዚህ ስፍራ አገላለጥ ደግሞ ለየት የሚለው አጋንንት ዘፋኞች ብቻ ሳይሆኑ ከዘፈን አድናቂዎች ጐራ መሰለፋቸው ነው::
💐💐💐💐💐💐💐
2. ፍትሐ ነገሥት መንፈሳዊ ሥራን አስመልክቶ ሲናገር እንዲህ ይላል:- "ስለ ተግባረ ዕድ ግን በዓለም ከሚሠሩ
ሥራዎች መንፈሳዊ ሕግን ከሚቃወም ሥራ በቀር ሁሉንም ሊሠሩ ይገባል:: ... እንደ ዘፋኝነት፥ እንደ መጥፎ ጫወታ፥
በእግር እንደ ማሸብሸብ(ዳንስና ጭፈራ) ካልሆነ በቀር ነው::"
👉 (ፍት.ነገ.መን.አን. 23:820)
ይህ የአበው ቃል ዘፋኝነት በመንፈሳዊ እይታ እንደ ሥራ መቆጠር እንደሌለበት ያስረዳል::
💐💐💐💐💐💐💐
3. ዘፋኝነት "የሥጋ ሥራ" በመሆኑ ኃጢአት ነው:: (ገላ.5:21):: "በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ፤" ተብሏልና:: (ገላ.5:16)
💐💐💐💐💐💐💐
4. ዘፈን በመንፈሳውያን መጻሕፍት ተወግዟል:: ሐዋርያት በዲድስቅልያ 📚 "ኢትኩኑ ዘፈንያነ" ፥ "ዘፋኞች አትሁኑ" ብለዋል:: (ዲድስቅልያ፤ አንቀጽ 7) ቅዱስ ጳውሎስ "በቀን እንደምንሆን በአግባብ እንመላለስ:: በዘፈንና በስካር አይሁን" ብሏል:: (ሮሜ.13፥13) ቅዱስ ጴጥሮስ ደግሞ "በስካርና በዘፈን
የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል::" ይለናል:: (1ኛ.ጴጥ.4:3)
👉 መጽሐፈ ሐዊ ደግሞ 📚 "ከሰይጣን የተገኘ ነውና ዘፈንንና ዳንስን ከኛ ማራቅ ይገባናል::" ይለናል
(መጽ.ሐዊ አን. 50)
👉 ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ደግሞ ከማዘዝ አልፎ ዘፈንን እንተው ዘንድ "ዘፈንን ትተዉ ዘንድ እማልዳችሗለሁ፤" በማለት ይማጸናል:: (ተግ.ዘዮሐ.አፈ.28) ዘፈንን አንተውም ላሉ ደግሞ መጽሐፈ ሐዊ "በዘፈን ጸንተው የሚኖሩ ይፈረድባቸዋል" በማለት ሲያስጠነቅቅ እናገኛለን (መጽ.ሐዊ.አን. 12)
Comment @Kokuhahaymanotbot
💚 @kokuha_haymanot 💚
💛 @kokuha_haymanot 💛
❤️ @kokuha_haymanot ❤️