✨" Go find Yourself first
So you can also find Me. "
🤷♀አንድ ሰው ሌላውን "አላውቀውም " ማለት ሲጀምር ፤ ያኔ ከራሱ ጋር እንደማይተዋወቅ ፤ እሱም ለራሱ ባዳ እንደሆነ መገንዘብ ይኖርበታል ። ለምን ቢባል ሁሉም ሰው እንደሰው የሚጋራቸው የወል የጋራ ስሜቶች አሉት ።
👫በሁለት ግለሰቦች መካከል ከሚኖሩት ልዩነቶች ይልቅ ተመሳሳይነታቸው ትልቁን ድርሻ ይይዛል ። " እኔ ከሌላው የተለየሁ ነኝ " ብለን ማሰብ ስንጀምር በእርግጥ አላዋቂነታችን በውስጣችን የነገሰበት ሰአት ላይ ደርሰናል ማለት ነው ።
💎ስው ማለት ፥ በየጊዜው የሚያድግ ፣ የሚለወጥ ፣ የሚደሰት ፣ የሚያዝን ፣ የሚስቅ ፣ የሚያለቅስ ፣ የሚተክዝ ፣ የሚጨክን ፣ የሚራራ ፣ የሚረሳ ፣ የሚያስታውስ ፣ በተስፋ እና በትዝታ መሐል የሚኖር ፤ .... የሚበርደው ፣ የሚሞቀው ፤ የሚይርበው ፣ የሚጠግብ ፣ ከወደቀ በኋላ የሚነሳ ፤...ወዘተ
🔴.. በመሳሰሉት የተለያዩ ስጋዊ-ወይም መንፈሳዊ ስሜት ጋር የሚኖር ነው ። . እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ስሜቶች ፤የትኛውም የአለም ክፍል የሚገኝ "ሰው " ሆኖ የተፈጠረ ሁሉም የሚጋራው ነው ። ታድያ ለምንድነው አንዱ ሌላውን " አላውቀውም " በማለት የሚክደው? - አንዳችን ጋር ያለ ስሜት ሌላውም ጋር ይኖራል ።
🔵... ሰው በመሆናችን በጋራ የምንጋራቸው እንጂ ፤ አንድም ከዚህ ቀደም ያልተከሰተ በሰው ልጅ ታሪክ ያለነበር ምንም አዲስ ነገር የለም ። ... ..የከፋው ሰው ስመለከት እኔ በህይወቴ የተከፋሁበት ዘመን ለምን ትዝ አይለኝም ?
ገንዘብ ወይም ስራ አጥቶ የተቸገረ ሰው ስመለከት ፤ ለምን ይሆን ያ የሱ ስሜት እኔን የማይሰማኝ ? ምናልባት የምበላው ሳይኖረኝ የተቸገርኩበት አጋጣሚ ምነው ትውስታው ደብዛው ይህን ያህል የሚርቀኝ ! ትውስ የማይለኝ ? በሁላችንም ደርሶ የሚያውቅ ፤ አልያም አንድ ቀን ሊደርስ የሚችል እንጁ ከቶ አዲስ የሆነ ነገር የለም ።
-
🔴ህይወት በአጋጣሚዎች የተሞላች ናት ። የምንደሰትበት ቅፅበት ሲያልፍ ትካዜ ቦታውን ይረከባል። አብረን የኖር ንበት ዘመን ሲያበቃ መለያየት በተራው ይመጣል ። የተለያየም አንድ ቀን ዞሮ መገናኘት ይኖርናል። የጉብዝና ወራት ሲያልቅ እርጅና በቦታው ይተካል ። ከፀሃይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም ። ሁሉም የነበረና ወደፊትም የሚቀጥል ይሆናል። ትውልድ በትውልድ ይተካል ። የህይወት ኡደት በተመሳሳይ ድግግሞሽ ይዘልቃል ።
-
🔴እኔን ለማወቅ ከፈለግክ አንተነትህን ማወቅ ይገባል ። አንተ ማለት እኔ ፤ እኔ ማለት አንተ ከአንድ ምንጭ የተቀዳን ፤ በትውልድ በየዘመናችን የምንፈስ ወንዝ ነን ጅረት ፤ ...ከመሬት ከአፈር የተፈጠርን ስጋ ለባሽ ፤ ተመሳሳይ ስሜት ያለን። ፤ በስተመጨረሻ ተመልሰን ወደ መጣንባት መሬት የምንገባ ።
✍Rumi
#ውብ_ምሽት
@lovefkrlove @Lovefkr