✝️ 7ቱ ኪዳናት
=>"ተካየደ" ማለት "ተስማማ: ተማማለ" እንደ ማለት ሲሆን "ኪዳን" በቁሙ "ውል: ስምምነት" እንደ ማለት ነው:: ይኸውም እግዚአብሔር ከሰዎች ጋር: ሰዎችም ከሰዎች ጋር የሚያደርጉት ሊሆን ይችላል:: ልዩነቱ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ቅዱስና የማይለወጥ መሆኑ ነው::
+እግዚአብሔር አምላክ ከሥነ ፍጥረት ጀምሮ በየጊዜው ከብዙ ወዳጆቹ ጋር ኪዳንን አድርጉዋል:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም እነዚህን ኪዳናት ጥቅልል አድርጋ 7 እንደ ሆኑ ታስተምራለች:: ስለዚህም ዛሬ ፈጣሪ ቢረዳን እነዚሁን 7 ኪዳናት በጥቂቱ እንመለከታለን::
"ኪዳነ ተካየድኩ ምስለ ኅሩያንየ"
"ከመረጥኩዋቸው ጋር ቃል ኪዳንን አደረግሁ" (መዝ. 88:3)
=>አዳም ማለት የእግዚአብሔር ድንቅ ፍጥረት:
የፍጡራን አስተዳዳሪ: ነቢይ: ካህንና ንጉሥ ነው::
እግዚአብሔር ከአዳም ጋር አስቀድሞ በእጸ በለስ
አማካኝነት ቃል ኪዳን ነበራቸው:: ነገር ግን አባታችን
በዲያብሎስ ሴራ በመረታቱ ኪዳኑ ፈረሰ:: (ዘፍ. 3:1)
+አዳምና ሔዋን ተጸጽተው ቢያለቅሱ ግን አዲስ የኪዳን
ተስፋ: "ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ኪዳንን
ተቀበሉ:: (ቀሌምንጦስ: ገላ. 4:4)
=>ከአዳም እስከ ኖኅ ድረስ ባሉት 10 ትውልድ ዓለም
በዓመፃ ተሞላች:: ቅዱስ ኖኅ በደግነቱ መርከብ ሠርቶ
ቤተሰቡን ሲያተርፍ ዓለም በማየ ሥራዌ ጠፋች::
ከመርከቡ ከወጣ በሁዋላ ኖኅና እግዚአብሔር በቀስተ
ደመና ምልክትነት ቃል ኪዳን ተጋቡ:: "ኢያማስና
ለምድር ዳግመ በማየ አይኅ" እንዲል:: (ዘፍ. 9:12)
=>መልከ ጼዴቅ የእግዚአብሔር ካህኑ: የክርስቶስም
ምሳሌው የሆነ የሳሌም ንጉሥ ነው:: በ15 ዓመቱ
መንኖ: አጽመ አዳምን ይዞ: በቀራንዮ በሕብስትና በወይን
ያስታኩት ነበር::
+እግዚአብሔር ለመልከ ጼዴቅ: በሐዲስ ኪዳን
ለምትሠራው ክህነትና ምሥጢረ ቁርባን ምሳሌ አድርጐ
በቃል ኪዳን አትሞታል:: በዚህም ተሰውሮ ይኖራል እንጂ
ሞትን እስካሁን አልቀመሰም:: ይህም ካህኑ መልከ
ጼዴቅ ከአብርሃም ጋር በተገናኙበት ጊዜ ተገልጧል:: (ዘፍ. 14:17, ዕብ. 7:1)
=>ቅዱስ አብርሃም የሕዝብና የአሕዛብ አባት: ሥርወ
ሃይማኖት: የጽድቅም አበጋዝ ነው:: ስለ ፍቅረ
እግዚአብሔር ሲል ከርስቱና ከወገኖቹ ተለይቶ በቅድስና
ኑሯልና እግዚአብሔር "በዘርሕ አሕዛብ ይባረካሉ"
አለው:: (ዘፍ. 12:1) የቃል ኪዳን ምልክትም ይሆነው ዘንድ ግዝረትን ሰጠው:: (ዘፍ. 17:1-14)
=>ቅዱስ ሙሴ የነቢያት አለቃ: የእሥራኤል እረኛ:
የእግዚአብሔር ሰው እና ፍጹም ትሑት (የዋህ) ሰው
ነው:: በፈጣሪው ትዕዛዝ እሥራኤልን ከግብጽ ባርነት አውጥቶ ለ40 ዘመናት በበርሃ ሲመራቸው
ከእግዚአብሔር የኪዳንን ጽላትና አሠርቱን ትዕዛዛት
ተቀብሏል:: (ዘጸ. 20:1, 31:18)
=>ቅዱስ ዳዊት ሥርወ ነገሥት: ጻድቅ: የዋህና ቡሩክ
የሆነ አባት ነው:: እግዚአብሔር ከእረኝነት ጠርቶ ንጉሥ
አድርጐ ሹሞት "ከሆድህ ፍሬ በዙፋንህ ላይ
አኖራለሁ" (መዝ. 131:11) ሲል ምሎለታል:: አክሎም
ሰፊ ቃል ኪዳን ሰጥቶ "አልዋሰሽህም" ብሎ ሲምልለት
እንመለከታለን:: (መዝ. 88:35)
=>በብሉይ ኪዳን የነበሩ 6ቱ ኪዳናት በዘመናቸው ክቡርና ሕዝቡን ከመቅሰፍት ይታደጉ የነበሩ ቢሆንም ከሲዖል ማዳን ግን አልቻሉም:: ስለዚህም አንድ ፍጹም ኪዳን ያስፈልግ ነበር:: ይህን ፍጹም ኪዳን ይፈጽም ዘንድም ከቅድስት ሥላሴ አንዱ ወልድ ከሰማያት ወርዶ በድንግል ማርያም ማሕጸን አደረ::
+በፍጹም ተዋሕዶም በሕቱም ድንግልና ተወልዶ: አድጎ:
ተጠምቆ: አስተምሮ: ሙቶ: ተነስቶና ዐርጐ ሥጋ
ማርያምን በዘባነ ኪሩብ አስቀመጠው:: ኪዳነ ምሕረት
(የምሕረት ኪዳን) የምንለው አንዱ ታዲያ ይሔው ነው::
+የጌታችን መጸነሱ: መወለዱ: መሰደዱ: መጠመቁ: ማስተማሩ: ሥጋውንና ደሙን መስጠቱ: መሰቀሉ: መሞቱና መነሳቱ: ማረጉና መንፈስ ቅዱስን መላኩ በአንድ ላይ ኪዳነ ምሕረት ይባላል:: ታዲያ ይህ ሁሉ የተደረገው በሥጋ ማርያም ነውና የኪዳኑ ባለቤት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት::
+የእርሷ ኪዳን የ6ቱን አበው ኪዳናት ፍጹም በማድረጉ "የኪዳናት ማሕተም" ይባላል:: የድንግል ማርያም ኪዳኗ ከሲዖልና ከገሃነም ሊታደገን አቅሙ አለውና:: መድኃኒታችን ክርስቶስ ለድንግል እናቱ ቃል ኪዳኑን ያጸናላት ደግሞ ካረገ ከዓመታት በሁዋላ ጐልጐታ ላይ ነው::
+እመ ብርሃን በዚያ ቁማ ስለ ኃጥአን ስታለቅስ "እናቴ ሆይ! በስምሽ ያመነውን: በቃል ኪዳንሽ የተማጸነውን እምርልሻለሁ" ብሎ ደስ አሰኝቷታልና:: ይሔው በእመ ብርሃን ምልጃና ቃል ኪዳን ምዕመናን ከመቅሰፍትና ከገሃነመ እሳት ማምለጥ ከጀመሩ 2ሺ ዓመታት ሆኑ:: ዛሬም እኛ ኃጥአን ልጆቿ ከእሳት እንደምታድነን አምነን በጥላዋ ሥር እንኖራለን::
*" ኢትዝክሪ ብነ አበሳነ: ኃጢአተነ: ወጌጋየነ፡፡
ማርያም እሙ ለእግዚእነ፡፡
በኪዳንኪ: ወበስደትኪ ድንግል ተማሕጸነ:: "*
"ድንግል ሆይ! ኃጢአታችን: አበሳችንና በደላችንን
አታስቢብን ዘንድ በስደትሽና በኪዳንሽ ተማጽነናል::"

(1) " ኪዳነ አዳም "
=>አዳም ማለት የእግዚአብሔር ድንቅ ፍጥረት:
የፍጡራን አስተዳዳሪ: ነቢይ: ካህንና ንጉሥ ነው::
እግዚአብሔር ከአዳም ጋር አስቀድሞ በእጸ በለስ
አማካኝነት ቃል ኪዳን ነበራቸው:: ነገር ግን አባታችን
በዲያብሎስ ሴራ በመረታቱ ኪዳኑ ፈረሰ:: (ዘፍ. 3:1)
+አዳምና ሔዋን ተጸጽተው ቢያለቅሱ ግን አዲስ የኪዳን
ተስፋ: "ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ኪዳንን
ተቀበሉ:: (ቀሌምንጦስ: ገላ. 4:4)
(2) " ኪዳነ ኖኅ "
=>ከአዳም እስከ ኖኅ ድረስ ባሉት 10 ትውልድ ዓለም
በዓመፃ ተሞላች:: ቅዱስ ኖኅ በደግነቱ መርከብ ሠርቶ
ቤተሰቡን ሲያተርፍ ዓለም በማየ ሥራዌ ጠፋች::
ከመርከቡ ከወጣ በሁዋላ ኖኅና እግዚአብሔር በቀስተ
ደመና ምልክትነት ቃል ኪዳን ተጋቡ:: "ኢያማስና
ለምድር ዳግመ በማየ አይኅ" እንዲል:: (ዘፍ. 9:12)
(3) " ኪዳነ መልከ ጼዴቅ "
=>መልከ ጼዴቅ የእግዚአብሔር ካህኑ: የክርስቶስም
ምሳሌው የሆነ የሳሌም ንጉሥ ነው:: በ15 ዓመቱ
መንኖ: አጽመ አዳምን ይዞ: በቀራንዮ በሕብስትና በወይን
ያስታኩት ነበር::
+እግዚአብሔር ለመልከ ጼዴቅ: በሐዲስ ኪዳን
ለምትሠራው ክህነትና ምሥጢረ ቁርባን ምሳሌ አድርጐ
በቃል ኪዳን አትሞታል:: በዚህም ተሰውሮ ይኖራል እንጂ
ሞትን እስካሁን አልቀመሰም:: ይህም ካህኑ መልከ
ጼዴቅ ከአብርሃም ጋር በተገናኙበት ጊዜ ተገልጧል:: (ዘፍ. 14:17, ዕብ. 7:1)
(4) " ኪዳነ አብርሃም "
=>ቅዱስ አብርሃም የሕዝብና የአሕዛብ አባት: ሥርወ
ሃይማኖት: የጽድቅም አበጋዝ ነው:: ስለ ፍቅረ
እግዚአብሔር ሲል ከርስቱና ከወገኖቹ ተለይቶ በቅድስና
ኑሯልና እግዚአብሔር "በዘርሕ አሕዛብ ይባረካሉ"
አለው:: (ዘፍ. 12:1) የቃል ኪዳን ምልክትም ይሆነው ዘንድ ግዝረትን ሰጠው:: (ዘፍ. 17:1-14)
(5) " ኪዳነ ሙሴ "
=>ቅዱስ ሙሴ የነቢያት አለቃ: የእሥራኤል እረኛ:
የእግዚአብሔር ሰው እና ፍጹም ትሑት (የዋህ) ሰው
ነው:: በፈጣሪው ትዕዛዝ እሥራኤልን ከግብጽ ባርነት አውጥቶ ለ40 ዘመናት በበርሃ ሲመራቸው
ከእግዚአብሔር የኪዳንን ጽላትና አሠርቱን ትዕዛዛት
ተቀብሏል:: (ዘጸ. 20:1, 31:18)
(6) " ኪዳነ ዳዊት "
=>ቅዱስ ዳዊት ሥርወ ነገሥት: ጻድቅ: የዋህና ቡሩክ
የሆነ አባት ነው:: እግዚአብሔር ከእረኝነት ጠርቶ ንጉሥ
አድርጐ ሹሞት "ከሆድህ ፍሬ በዙፋንህ ላይ
አኖራለሁ" (መዝ. 131:11) ሲል ምሎለታል:: አክሎም
ሰፊ ቃል ኪዳን ሰጥቶ "አልዋሰሽህም" ብሎ ሲምልለት
እንመለከታለን:: (መዝ. 88:35)
(7) " ኪዳነ ምሕረት "
=>በብሉይ ኪዳን የነበሩ 6ቱ ኪዳናት በዘመናቸው ክቡርና ሕዝቡን ከመቅሰፍት ይታደጉ የነበሩ ቢሆንም ከሲዖል ማዳን ግን አልቻሉም:: ስለዚህም አንድ ፍጹም ኪዳን ያስፈልግ ነበር:: ይህን ፍጹም ኪዳን ይፈጽም ዘንድም ከቅድስት ሥላሴ አንዱ ወልድ ከሰማያት ወርዶ በድንግል ማርያም ማሕጸን አደረ::
+በፍጹም ተዋሕዶም በሕቱም ድንግልና ተወልዶ: አድጎ:
ተጠምቆ: አስተምሮ: ሙቶ: ተነስቶና ዐርጐ ሥጋ
ማርያምን በዘባነ ኪሩብ አስቀመጠው:: ኪዳነ ምሕረት
(የምሕረት ኪዳን) የምንለው አንዱ ታዲያ ይሔው ነው::
+የጌታችን መጸነሱ: መወለዱ: መሰደዱ: መጠመቁ: ማስተማሩ: ሥጋውንና ደሙን መስጠቱ: መሰቀሉ: መሞቱና መነሳቱ: ማረጉና መንፈስ ቅዱስን መላኩ በአንድ ላይ ኪዳነ ምሕረት ይባላል:: ታዲያ ይህ ሁሉ የተደረገው በሥጋ ማርያም ነውና የኪዳኑ ባለቤት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት::
+የእርሷ ኪዳን የ6ቱን አበው ኪዳናት ፍጹም በማድረጉ "የኪዳናት ማሕተም" ይባላል:: የድንግል ማርያም ኪዳኗ ከሲዖልና ከገሃነም ሊታደገን አቅሙ አለውና:: መድኃኒታችን ክርስቶስ ለድንግል እናቱ ቃል ኪዳኑን ያጸናላት ደግሞ ካረገ ከዓመታት በሁዋላ ጐልጐታ ላይ ነው::
+እመ ብርሃን በዚያ ቁማ ስለ ኃጥአን ስታለቅስ "እናቴ ሆይ! በስምሽ ያመነውን: በቃል ኪዳንሽ የተማጸነውን እምርልሻለሁ" ብሎ ደስ አሰኝቷታልና:: ይሔው በእመ ብርሃን ምልጃና ቃል ኪዳን ምዕመናን ከመቅሰፍትና ከገሃነመ እሳት ማምለጥ ከጀመሩ 2ሺ ዓመታት ሆኑ:: ዛሬም እኛ ኃጥአን ልጆቿ ከእሳት እንደምታድነን አምነን በጥላዋ ሥር እንኖራለን::
*" ኢትዝክሪ ብነ አበሳነ: ኃጢአተነ: ወጌጋየነ፡፡
ማርያም እሙ ለእግዚእነ፡፡
በኪዳንኪ: ወበስደትኪ ድንግል ተማሕጸነ:: "*
"ድንግል ሆይ! ኃጢአታችን: አበሳችንና በደላችንን
አታስቢብን ዘንድ በስደትሽና በኪዳንሽ ተማጽነናል::"
=>ቸሩ ልጇ ከበረከተ ኪዳኗ አይለየን::