Forward from: ✟ ጋሜል- ዘ ኦርቶዶክስ ✟
❣️ ጥቅምት ፳፯ (27) እንኳን ለፈጣሪያችን መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!❣️
💠 ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው የማዳን ሥራ ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ 3:00 ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት:: ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና: ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት: አስረው ሲደበድቡት አድረዋል።
❖ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት።
¤ምራቃቸውን ተፉበት። ዘበቱበት።
¤ራሱንም በዘንግ መቱት።
¤እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ።
¤በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት።
¤ በሠለስት (3:00 ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ 6,666 ገረፉት::
¤ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት።
¤6:00 ላይ በረዣዥም ብረቶች 5 ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት።
➢ 7 ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ።
¤ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ 7 ቃላትን ተናገረ።
➢ ከቀኑ 9:00 አካባቢ በባሕርይ ስልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ:: በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ።
¤11:00 ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት:: በዚአች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ። ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ። ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ።➢ ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት 27 ቀን ቢሆንም በዓሉ ወደ ጥቅምት እንዲመጣ ያደረጉት አበው ሊቃውንት ናቸው:: ምክንያቱም ብዙ ጊዜ መጋቢት 27 የሚውለው ዓቢይ ጾም ውስጥ በመሆኑና የንግሥ በዓላት በዓቢይ ጾም ስለማይፈቀዱ ነው።
➢ ምንም እንኩዋ በቅርብ ጊዜ በዓቢይ ጾም የሚያነግሡ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም አባቶቻችን ግን እንዲህ ያለውን ሥርዓት አላቆዩልንም። ከበሮና የቸብቸቦ ዝማሬም በወቅቱ የተፈቀደ አይደለም።
➢ በዚህም ምክንያት የበዓለ ስቅለት ንግሡ ወደ ጥቅምት 27 ሲመጣ: የመጋቢት 5 ገብረ መንፈስ ቅዱስ ንግሥ ወደ ጥቅምት 5: የመጋቢት 10 መስቀል ወደ መስከረም 17 መጥቶ እንዲከበር ሆኗል።
✝️ አምላከ ቅዱሳን በአማኑኤል ስሙ: በማርያም እሙ: በፈሰሰ ደሙ: በተወጋ ጐኑ: በንጹሐን ቅዱሳኑ ይማረን። ከመስቀሉና ከቅዱሳኑ በረከትም አይለየን።
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@maedot_ze_orthodox
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈