‹‹ትቀልዳለህ እንዴ…ከዛኛው ዳግላስ ፍቅር ሊይዘኝ እኮ ትንሽ ነበር የቀረኝ …ተጨማሪ አንድ ቀን አብረን ማሳለፍ ብንችል አልቆልኝ ነበር››
‹‹ይሄኛውንም ዳግላስ እኮ ገና እየተዋወቅሽው ነው…ከዛኛው የተሻለ ተወዳጅና ተመራጭ ሊሆን ይችላል››
‹‹አይ በፍፅም …ይሄኛውም ትገደል ብሎ የሞት ፍርድ የፈረደብኝ ነው…ይሄኛው ዳግላስ በአውሬ ሊያስበላኝ የነበረ ነው….ይሄኛው በመርዝ ተመርዤ እንድሞት አድርጎኝ የነበረ ነው፡፡››
‹‹አዝናለው…..ያኛውን ዳግላስ ባመጣልሽ ደስ ይለኝ ነበር..ግን እንደምታይው አሁን ፊትሽ ያለው ይሄኛው ደግላስ ነው፡፡ግን የጊዜ ጉዳይ ነው ይሄኛውንም ዳግላስ ላደረገብሽ ነገር ይቅር ትይዋለሽ…እንደዛኛውም ልትወጂው ትችያለሽ….››
‹‹እኔ እንጃ… አይመስለኝም›› አለችና ሌላ ነገር ልትመልስላት ስትል ምስራቅ ቅፅበታዊ ጆሮ ሰንጣቂ ጩኸት አሰማች… ሁለቱም ተሯርጠው ወደእሷ ሄዱ….አካባቢዋ ያለው የገንዳ ውሀ በደም ቀልሟል… ኑሀሚ አውሬ የነደፋት ነው የመሰላት፡፡
ጎትተው ከገንዳው አወጧት..ናኦል የሚሆነው ግራ ተጋብቶ ወዲህ ወዲያ በድንጋጤ እየተወራጨ ነው፡፡
‹‹አታስቡ ትንሽ ነገር ነው …ወደታች ወደወለሉ ሰምጬ ስዋኛ የገንዳው ወለል ላይ አረፍኩና የሆነ ስለት ነገር ነው እግሬን የቆረጠኝ…..››ስትል ሁኔታውን አብራራችላቸው፡፡
ውስጥ እግሯን አንስተው ሲያዮት መሀከሉ ላይ ሽርክት ብሎ ተቆርሷል … በውስጡ የተቀረቀረበትም ጠጠር ተፈንቅሎ የወጣ ነው የሚመስለው፡፡ዳግላስ አበደ ፡፡ ሰረተኞቹን ጠርቶ ጮኀባቸው….እንዴት ስለት ነገር ገንዳ ውስጥ እንዳስገቡ ጠየቃቸው…መልስ መስጠጥ የቻለ አልነበረም….የሚደርባቸው ቅጣት እየሳቡ በመንቀጥቀጥ ሰሙት፡፡
ወዲያወ የግቢው ሀኪም መጣና ቁስሉን አፀድቶላት በተገቢው መንገድ አሸገለት…ከዛ ሁሉ ነገር ተረጋጋና ሁሉም ልብሳቸውን ለባብሰው ዝግጅቱን ለማተዳም ጠረጴዛ ከበው ተቀመጡ፡፡በግዙፍ ጠራጴዛ ምግቡ ተደረደረ፡፡ መጠጡ ተኮለኮለ፡፡ ጉብታ የሚያህል ባለደረጃ ኬክ እየተገፈ መጣ…አከባቢው ሁሉ በባለ ቀለም የሻማ ብርሀን ተንቦገቦገ…በህይወታቸው በጣም የሚገርም …የሚያምረውንና ውዱን የልደት በዓለቸውን ማክበር ጀመሩ….በሀከል ኑሀሚ ወደምስራቅ ጆሮ ጠጋ ብላ…‹‹እግርሽን ለምንድነው የቆረጥሽው››ስትል ጠየቃቻ..ሆነ ብላ እንደዛ እንዳደረች ያወቀችው እሷ ብቻ ነች፡፡
ዛሬም እንደድሮው የምትገርሚ ሴት ነሽ..አንቺን ደብቆ የሆነ ነገር ማድረግ መቼስ አይተሰብም…ከኢትዬጵያ ስነሳ እንዳይገኝ ተደርጎ እግሬ መሀል የተቀበረ ችብስ ነበር..አሁን ሶስታችንም አንድ ቦታ በመገኘታችን ለሰዎቻችን መልዕክት ማስተላለፊያ ጊዜው ስለሆነ ነው ያደረኩት..አንቺን እስክናገኝ ነበር የምጠብቀው… አሁን ምልክቱን ሰጥቻቸዋለው….እንግዲ ከቻሉ ያድኑናል››አለቻት፡፡
ኑሀሚ ለይ የተስፋ ብርሀን በውስጧ ሲፈነጥቅ ታወቃት…የካርሎስ ሙከራ ባይሳካ እንኳን ሌላ ትስፋ አላቸው ማለት ነው…በህይወት ተደረራቢ ተስፋ አለ ማለት ደግሞ ለመኖርም ተደረራቢ የኃይል ክምችት አለ ማለት ነው፡፡ዛና ባላ ሁኔታ ልደቷን ማክበር ጀመረች…ዳግላስን እንደጠላቷ እና ለቀናቶች ሊገድላት ሲያሳድዳት እንደነበረ ሰው ሳይሆን ልክ እንደ ረጅም ጊዜ ጓደኛዋ እየተንጠለለችበትና እየተላፋቸው አብራው መደነስ ጀመረች፡፡

ይቀጥላል...
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
https://t.me/manbabemulusewyaderegal
https://t.me/manbabemulusewyaderegal
https://t.me/manbabemulusewyaderegal
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️