⚠️
አደጋ ላይ ነው ያለነው ‼️
⚠️ ሁላችንም የዓለም ሙስሊሞች በአንድ ነገር ተስማምተናል። ምን መሰላቹ❓
🌀 ሳንዘራ ማጨድ... ወይም ደግሞ ክፋትን ዘርተን መልካምን ማፈስ የተስማማንበት ምኞታችን ሆኗል !!!
🔥 ዛሬ ይነስም ይብዛ በሁሉም የሙስሊም ሀገራቶች ሊባል በሚችል መልኩ የልዕለ አያሉ አምላክ "
ሐቅ" የሰው ልጆች ወደው ፈቅደው... ሸራርፈው እንደራሳቸው ፍጡር ለሆኑ ደካማ አካላቶች እየሰጡበት ነው❗️
🔥
ቀብር እየተመለከ ነው ፤ ከአጭበርባሪ ጠንቋይ የሩቅ ሚስጥር እየተገለጠ ነው ፤ ለአጋንንቶች እየተገበረ ነው ፤ ለሙታኖች ጥሪ እየተደረገ ነው ፤ ለድንጋይ ፣ ለዛፍና አስጠሊታ ለሆኑ ፍጥረታቶች ሁሉ ሳይቀር "ሱጁድ" ተወርዶ "በረካ" እየተፈለገ ነው ፤ መተተኛ ተብታቢዎች ምቀኛና ቅናተኞችን ባሪያ አድርገው እንዳሻቸው እየነዱሃቸው በማስገበር ንፁሃንን ሳይቀር እይወታቸውን እየቀጠፉ ምድርን በፍርሐት ውጠዋታል ... እንተወው እንጂ መች ቆጥረን እንዘልቀውና❓❗
👉 ታላቁ "ኢማም ኢብን ባዝ" ሙስሊሞች ጥሪያቸውን ለማይሰሙ ሙታኖች ራሳቸውን አዋርደው እንዴት ባሪያ እንደሆኑ አሳዛኙን ክስተት እንዲህ ያስታውሱናል ፦
🔥 " ... (
በዘመናችን አብዛኞቹ አጋሪዎች) ማጋራታቸው በድሎትም በጭንቅም ሰዓት ነው። ይህንንም ነገር የተቀላቀላቸውና ሁኔታቸውን ያጠና የሆነ ሰው የሚያውቀው ነው።*⃣ ከዚህም በመነሳት (ይህም ሰው) "በግብፅ" ሀገር አል-ሑሰይንና አል-በደዊ ቀብር ዘንድ የሚሰሩት የሆነውን ነገር ይመለከታል።
🔥
እንደዚሁም "ዐደን" ውስጥ "አል-ዐይዱሩስ" ቀብር ላይ ፤ "የመን" ውስጥ "አል-ሀዲ" ቀብር ላይ ፤ "ሻም" ውስጥ "ኢብን ዐረቢ" ቀብር ላይ ፤ "ዒራቅ" ውስጥ "የሼይኽ ዐብዱል ቃድር ጀይላኒ" ቀብር ላይና ሌሎችም የሚታወቁ በሆኑ (ቀብሮች ላይ) አብዛኞቹ አላዋቂ የሆኑ ሰዎች ድንበር ያለፉባት ሲሆንና ብዙ የሆነን የአሸናፊውንና የላቀውን አላህ "ሐቅ" ቀንሰው የሰጡበት ነው።
👉 ይህን ነገር በነርሱ (በአጋሪዎቹ) ላይ የሚያወግዝም (ሰው) አንሷል❗
🔸 ያ አላህ ነብዩን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለምና) ከሳቸውም በፊትም የላካቸው መልዕክተኞች ሰላምና ሶላት በነርሱ ላይ ይሁንና እነርሱ የመጡበት የሆነውን "
የተውሒድ" እውነታ ግልፅ የሚያደረግላቸውም አንሷል❗
🔘" እኛ ከእርሱ (ከአላህ) ነን ወደ እርሱም ተመላሾች
ነን !! "
✔️ጥራት የተገባው አምላክ ወደ ቅናቻቸው እንዲመልሳቸው እንጠይቀዋለን ! በመካከላቸውም የቅናቻመሪዎችንእንዲያበዛላቸው
እንዲሁም የሙስሊም መሪዎችንና ዑለማዎችም ይህን አፀያፊ " ሽርክ " አንዲዋጉና እንዲያጠፉት ይገጥማቸው ዘንድ (አላህን እንጠይቀዋለን !!! )
እርሱ (አላህ) ሰሚም ቅርብም ነው !!!
✍የሸኹ ንግግር አበቃ !
📚[አል- ዐቂደቱ ሰሒሓ ...(25)]
ኢማሙ ኢብን ባዝ እንዳሉት ባደረገውና ሙስሊሞች ካሉበት ሽርክና ዘመናዊ ድንቁርና የሚያወጣቸው መሪ ባገኙ ምነኛ መታደል ነበር።
🔥
ዛሬ ሸኹ ከሞቱ 20 ምናምን ዓመት በኋላ የሙስሊሞች ጉዳይ አሳሳቢና አስጊ ደረጃ ላይ ደርሶ ከሙስሊሙ ከራሱ አብራክ የወጣው ትውልድ "university" በሚባል የፍልስፍና ተቋም ውስጥ አራት አምስት ዓመታትን አልፈው ጋዎን አርገው ቆብ ከደፉ በኋላ 70 እስከ 80 ዓመት እንዲሁም እስከ ዕለተ ሞታቸው እስልምናን ከአጥፊዎች ታድገው ክፉን ከደግ ለይተው ሙስሊሙን ሲያነቁና ሲያስጠነቅቁ የነበሩትን ዑለማዎችን "ፊቅሁ አል-ዋቂዕ" ( የተጨባጩ ዓለም ሁኔታ ያልገባቸው...) በሚል ጭምብል ትውልዱ ዑለማዎችን በመተው ወደ እነሱ ተውሒድንም ሱናንም " ትቶ " ከነችግራችንም አንድ ብቻ እንሁን " ወደሚለው ፍልስፍና እንዲተም አደረጉት።
👉 ምን የሚሉት አንድነት ነው ?‼️" ተውሒድና ሱና " አርማ !! ሳይደረግ ?!
📎 አሸናፊው አምላክ ከሃዲያንን የገለፀበት አንድነት ካልሆነ በስተቀር ፦
(( " لَا يُقَٰتِلُونَكُمْ جَمِيعًا إِلَّا فِى قُرًى مُّحَصَّنَةٍ أَوْ مِن وَرَآءِ جُدُرٍۭ بَأْسُهُم بَيْنَهُمْ شَدِيدٌ تَحْسَبُهُمْ جَمِيعًا وَقُلُوبُهُمْ شَتَّىٰ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ قَوْمٌ لَّا يَعْقِلُون"َ )) (الحشْر), 14
(( " በተመሸጉ ከተሞች ውስጥ ወይም ከአጥሮች ጀርባ ኾነው እንጅ ፤ የተሰበሰቡ ኾነው አይዋጉዋችሁም፡፡ ኀይላቸው በመካከላቸው ብርቱ ነው፡፡ ልቦቻቸው የተበታተኑ ሲኾኑ የተሰበሰቡ ናቸው ብለህ ትጠረጥራቸዋለህ፡፡ ይህ እነሱ አእምሮ የሌላቸው ሕዝቦች በመኾናቸው ነው፡፡ " ))
በዚህም የተሳሳተ እሳቦት የተነሳ የእስልምና እውነተኛ ገፅታ ጠፍቶ ... ነብዩ ( ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) እንዳሉት ፦ አስተካካዮች እንደ አጥፊ አጥፊዎች ደሞ እንደ አስተካካይ ተደርገው ተወሰዱ።
👉 ይህ ዕድል ያመቻቸው ከሃዲያኖች ጊዜ ባለማባከን ሙስሊሙን እርስ በራሱ ደም እየተቃባ እንዲኖር በማድረግ መደላድላቸውን በማመቻቸት በሙስሊሙ ላይ የበላይነታቸውን አረጋግጠው እንዲቀመጡ ሆኑ !!!
📝ሽኽል ኢስላም ኢብን ተሚያ (አላህ ይዘንለትና) እንዲህ ነበር ያለው ፦
" ጠላት በሙስሊሞች ሀገር ላይ የበላይ ከሚሆንባቸው ምክንያቶች ውስጥ ፦ ፈጣሪ የለም ብሎ ማፈንገጥ ፥ በውጪ እስልምናን ገልፆ በውስጥ ክህደትን መደበቅ እንዲሁም በእስልምና ያልተደነገገን ነገር ዕምነት አርጎ መያዝ ናቸው። " ...
🤲አላህ ሆይ ድረስልን !!!
✍... ኢስማኤል ወርቁ...
🔗
https://t.me/mesjidalsunnah/17494https://t.me/amr_nahy1