#ራስን_መግዛት -የማለዳ ትምህርታችን ክፍል ፪
#አሳብን_መግዛት
መንፈሳዊው ሰው አንደበቱን መግታት እንደ ቻለ ሁሉ አሳቡንም መግዛት ይችላል፡፡ እርሱ የጀመረውን መንፈሳዊ መንገድ በሆነ አሳብ ምክንያት ስቶ እንዳይወጣ አሳቡን ይገታል፡፡ ወደ አሳቡ የሚመጣውን የኃጢአት አሳብ ሁሉ አይቀበልም፡፡ ፈጠን ብሎ ስለሚያስወጣው በእርሱ ላይ ለዘብተኝነት አያሳይም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በመጀመሪያ ቀላል መስሎ የሚታየውንና ቀስ በቀስ ተቀባይነት ወደሌለው ነገር የሚመራውን አሳብ ገና ከጅምሩ አይቀበለውም፡፡ እንደዚህ ዓይነቱን ውስጡ ተኩላ ሆኖ ከላይ ግን የበግ ለምድ ለብሶ የሚመጣውን አሳብ ስለማይቀበለው ስለ ሰይጣን ቅዱስ ጳውሎስ የተናገረውን «በሰይጣን እንዳንታለል የእርሱን አሳብ አንስተውምና።» (2ኛ ቆሮ. 2፥11) የሚለውን ቃል ለውስጡ አበክሮ ይነግረዋል።
እርሱ በኃጢአት አሳብ ከተሳሳተም ስህተቱን ፈልጎ በማግኘት ጥፋቱን ብዙ ሳይቆይ ያቆመዋል:: ምክንያቱም ከኃጢአት አሳብ ጋር አብሮ መጓዝ ጌታን እንደመካድ ስለሚቆጠር ብቻ ሳይሆን ይህ ክፉ አሳብ አንድ ጊዜ ከሕሊና ጋር ክፉኛ ከተጣበቀ ስለማይለቅ ነው፡፡ ከዚህ በመቀጠል እያደገና እየጎለመሰ ከንቱ ከሄደ በኋላ ልብን ከማጥቃቱም በላይ ወደ ምኞት ይቀየራል፡፡ በእርግጥም እንደዚህ ዓይነቱን አሳብ ገና ከውጥኑ ማጥፋት አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው::
መንፈሳዊው ሰው ጊዜውን ሙሉ ለሙሉ ክፉ አሳቦችን በመቆጣጠርና ኃጢአት በመከላከል አይጨርስም:: ይልቁኑ ሕሊናውንና ልቦናውን በንጹሕና በመንፈሳዊ አሳብ አብዝቶ ይሞላል፡፡ በመሆኑም ዲያብሎስ በክፉ አሳብ ሊዋጋው ሲመጣ ሕሊናውን በመንፈሳዊ ተመስጦ ተሞልቶ ያገኘዋል፡፡ በሕሊናው ውስጥ ያለው መንፈሳዊ ከባቢ አየር ማንኛ ውም ዓይነት የኃጢአት አሳብ ወደ እርሱ እንዳይቀርብ በማድረግ ልክ እንደ ጠንካራ ምሽግ ይመክተዋል።
#ስሜትን_መግዛት
ስሜት የአሳብ ሁሉ መዝጊያ ነው:: ስለሆነም መንፈሳዊ ሰው አሳቡን ለመቆጣጠር ሲፈልግ ስሜቱን ይቀጣጠራል፡፡ ዓይኖቹንና ጆሮዎቹን ይቆጣጠራል:: ስለሆነም ማንኛውም ወደ አሳብ የሚመራ ነገር ካለ ወደ ስሜቱ ስለሚደርስ ፈጥኖ ያስወግደዋል:: እዚህ ላይ አንዱን በሌላው መተካት በሚለው መርሆው መሠረት በአንዱ አሳቡ ቦታ ሌላ አሳብ ይተካል፡፡
ዮሐንስ ሐጺር የተባለው ቅዱስ ሰው ማዳመጥን በመከልከል ዙሪያ አስገራሚ ነገሮች ይሠራ ነበር ... አባ ኦር የተባለው ቅዱስም ለደቀ መዝሙሩ:- «ልጄ ሆይ! ወደዚህች ወደ በአታችን ምንም ዓይነት እንግዳ ቃል እንደማይገባ ተመለከትህን!?» ብሎት ነበር።
👉 t.me/mezgebehaymanot 👈
ይቀጥላል....
(#በብፁዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
#መንፈሳዊ_ሰው_መጽሐፍ ገጽ 122-128
#በአያሌው_ዘኢየሱስ_የተተረጎመ)
አዘጋጅ :-በለጠ ከበደ (የጣፈጡ ልጅ)✍ አላቲኖስ
╔✞═┉✽🌹✥🌹✽┉═✞╗
❀#መልካም_የበረከት_ዕለት ❀
╚✞═┉✽🌹✥🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ
አዘጋጅ :-በለጠ ከበደ (የጣፈጡ ልጅ)✍ አላቲኖስ
የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏
በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" t.me/mezgebehaymanot
በ Facebook በፔጃችን "መዝገበ ሃይማኖት" ወይም ከዚህ እታች ያለውን በመጫን ፔጁን ይቀላቀላሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇... ...... 👉አስተማሪ ጹሁች ለማግኝት ከስር ያለውን በመጫን ላይክ 👍 ይቀላቀላሉ https://www.facebook.com/%E1%88%98%E1%8B%9D%E1%8C%88%E1%89%A0-%E1%88%83%E1%8B%AD%E1%88%9B%E1%8A%96%E1%89%B5-232318137666445/
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
rel='nofollow'>👉t.me/mezgebehaymanot👈 ለሌሎች ያስተላልፉ መልካሙን ያካፍሉ🤳🤳🤳
beletekebede03@gmail.com
ወስብሐት ለእግዚአብሔር