የሚያስፈልገን..ከ...ምንፈልገው
የማለዳ የነፍስ ስንቃችን
◆ በአንድ ወቅት አንድ መነኩሴ የወይራ ዘይት ዛፍ ተከለና ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል መጸለይ ጀመረ ፤ "ጌታ ሆይ ለዛፌ ይጠቅም ዘንድ ዝናብን አዝንብልኝ" አለ።
👉 t.me/mezgebehaymanot👈
እግዚአብሔርምጸሎቱን ተቀብሎ ዝናቡን አዘነበለት ፤ ዛፉም ውኃን በጣም ጠግቦ አፈሩ ረሰረሰ። ለዛፉ ይጠቅም ዘንድ ግን ከመጠን በላይ የረሰረሰው አፈር መድረቅ ያስፈልገው ነበር። ስለሆነም መነኩሴው ወደ እግዚአብሔር ጸለየ "ጌታ ሆይ ብዙ ፀሐይ በዛፉ ላይ እንድታወጣ እለምንሃለሁ" አለ።
👉 t.me/mezgebehaymanot👈
እግዚአብሔርምበለመነው መሠረት ፀሐይ አወጣለት ፤ ዛፉም አደገለት። መነኩሴው ልመናውን ቀጠለ "ጌታ ሆይ የዛፉ ሥር እና ቅርንጫፍ ይጠነክር ዘንድ ጥቂት ውርጭ ላክልኝ" አለ። እግዚአብሔርም በጠየቀው መሠረት ውርጩን ላከለት ፤ ከዚያም ዛፉ ከውርጩ የተነሣ ጠወለገ ሞተም።
👉 t.me/mezgebehaymanot👈
◆መነኩሴው በኹኔታው በጣም ተናድዶ ወደ አንድ መነኩሴ ሔዶ የገጠመውን ታሪክ እና ቅሬታውን ያለማጉደል አጫወተው ኀዘኑን አካፈለው። ሁለተኛው መነኩሴ ታሪኩን ከሰማ በኋላ "እኔም እንደ አንተ የወይራ ዘይት ዛፍ አለኝ ተመልከት" አለው ፤ የእርሱ ዛፍ በመልካም ኹኔታ አድጋለች። ሁለተኛው መነኩሴም ቀጥሎ "እኔ ግን ከአንተ በተለየ መልኩ እጸልያለሁ ፤ ይህን ዛፍ የፈጠረው እርሱ ነውና ፤ ከእኔ የተሻለ የሚያስፈልገውን እንደሚያውቅ ለእግዚአብሔር ነገርኹት ፤ እግዚአብሔርም እንዲንከባከበው በጸሎት ጠየቅኹት ፤ እርሱም ጸሎቴን ሰምቶ ተንከባከበው" በማለት አስረዳው።
👉 t.me/mezgebehaymanot👈
◆በእኛም ሕይወት እንዲህ ነው ፤ የሚያስፈልገንን በትክክል የምናውቅ መስሎን እንለምናለን ፤ ነገር ግን ለእኛ የሚያስፈልገንን ያለማጓደል የሚያውቀው እግዚአብሔር ብቻ ነው። ስለዚህ በሙሉ ልብ እንመነውና ◆"ጌታሆይ የምፈልገውን ሳይሆን የሚያስፈልገኝን ስጠኝ" እንበለው።
👉 t.me/mezgebehaymanot👈
አዘጋጅ:-በለጠከበደ(የጣፈጡልጅ)✍አላቲኖስ
╔✞═┉✽🌹✥🌹✽┉═✞╗
❀#መልካም_የበረከት_ቀን❀
╚✞═┉✽🌹✥🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ
የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏
በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" t.me/mezgebehaymanot
ወስብሐትለእግዚአብሔር