ተግባራዊ ክርስትና
አባ መቃሪዮስ በአንድ ወቅት ስለራሱ እንዲህ ሲል ተናግሯል “ወጣት በነበርኩበት ጊዜ በግብፅ በአንዲት መንደር በትንሽ ጎጆ እኖር ነበር በአንድ ወቅት የመንደሩ ነዋሪ እኔን ለቤተክርስቲያን ሹመት አጩኝ እኔ ግን ይህን ክብር ሽሽቼ ወደሌላ መንደር ሄድኩኝ፡፡ ከዚያም ትጉህ አገልጋይ የሆነ ረዳት አብሮኝ መኖር ጀመረ እኔ የምሰራቸውን የእጅ ስራወች እርሱ በመሽጥ ያገለግለኝ ነበር፤ በዚህ ወቅት በምኖርበት መንደር ያለች አንዲት ድንግል በድካም ዝላ ከጋብቻ ውጭ ዝሙት ትሰራና ታረግዛለች ቤተሰቦቿ ከማን እንዳረገዘች እንድትናገር ወጥረው ሲይዟት “ከመናኙ” ነው በማለት ተናገረች፤ የመንደሩም ሰው ተሰብስቦ ወደ እኔ መጣ ወደ መንደሩም እየጎተቱ ይዘውኝ ሄዱ በአንገቴም ላይ በጥላሽትና በልዩ ልዩ ነገሮች የጠቆሩ ቶፋወችን እንዳንጠለጥል አድርገው በመንደሩ ሁሉ እንድዞር አደረገው ይመቱኝ ነበር እንዲህም ይሉ ነበር “ይህ መነኩሴ ልጃችንን አስነውሯታል እያሉ “መቱኝም አመታታቸውም ለሞት የሚያደርስ ነበር፡፡
ያገለግለኝ የነበረው ያ ሰው ግን ፊቱ በሃፍረት ተሞልቶ ከጎኔ ይጓዝ ነበር እርሱንም አብረው ይሰድቡት ነበርና እንዲህም ይሉት ነበር “ይህን መናኝ ተመልከት ያደረገውንም እይ ለእርሱም በትጋት ስትታዘዘው ነበር” የልጅቷም ወላጆች እንዲህ አሉ “ልጃችንን ለመንከባከብ እስካልማለ ድረስ እንዳትለቁት” እኔም ለአገልጋዬ የሚሉትን ሁሉ አደርጋለሁ በላቸው ስል ነገርኩት፡፡ በዚህም ጊዜ ለቀቁኝ፡፡ ወደ ጎጆየ ደርሼ “የሰራኋቸውን ቅርጫቶች ሁሉ ውሰድ ሽጣቸውም የሚበላ ይሆናት ዘንድ ለሚስቴም ስጣት” አልኩት፡፡ ለራሴም እንዲህ አልኩኝ “መቃሪዮስ ሆይ አንተ ለራስህ እነሆ ሚስት አግኝተሃል ለወትሮው ከምትሰራው ይልቅ የበለጠ መስራት አለብህ ፤ በዚህም ሚስትህን ትጠብቃለህ፡፡”
ከዚያም በኅላ ቀንና ሌሊት እየሰራሁ አገልጋየ በመሽጥ ለልጅቷ እልክላት ነበር፡፡ ነገር ግን የልጅቷ የመውለጃ ቀኗ ሲደርስ፦ ምጥ ይዟት መውለድ ሳትችል ረጂም ቀናቶች አለፉ፤ ወላጆቿም “ይህ ነገር ምንድን ነው?”ሲሉ ጠየቋት፤ እርሷም “ምን እንደሆነ አውቃለሁ ይህ የሆነው ያንን መናኝ ያለስራው ከስሼው ስለነበር ነው በሃሰትም ወንጅየው ነበር ያስረገዘኝ ያ መናኝ መነኩሴ አይደለም እኔም ዋሽቻለሁ” በማለት ተናገረች፡፡ ይህን የሰማ አገልጋዬም እጅግ ደስተኛ ሆኖ ወደእኔ መጣና “ያቺ ድንግል ሴት የእርስወን ንፅህና ሳትናገር በፊት መውለድ አልችል አለች የርስዋን ንፅህና ከተናገረች በኅላ ግን መውለድ ቻለች የመንደሩ ሰው ሁሉ በሰራው ስህተት ይቅርታ ሊጠይቅ ወደዚህ እየመጡ ነው” በማለት ነገረኝ፡፡ ነገር ግን ይህን በሰማሁ ሰአት የመንደሩ ሰው ሊያደርገው የነበረውን ከንቱ ውዳሴ እንዳልካፈል ከመኖሪያዬ ተነሳሁ አሁን ወደ ምኖርበት ወደ አስቄጥስ ገዳም መጣሁኝ ወደዚህ የመምጣቴም ምክንያት ይህ ነበር፡፡”
ክርስቲያን ማለት እንዲህ ነው አብነቶቻችንም እንዲህ ያሉ ናቸው፡፡
╔✞═┉✽🌹✥🌹✽┉═✞╗
❀#መልካም_የበረከት_ቀን❀
╚✞═┉✽🌹✥🌹✽┉═✞╝አላቲኖስ
የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏
በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" t.me/mezgebehaymanot
ወስብሐትለእግዚአብሔር