MINSTERY OF EDUCATION


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Education


For more information!
✅የተረጋገጠ የትምህርት ደረጃ
ለማግኘት እኛን ይከተሉ!!
Minister
Contact us- @All_promoteme

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Education
Statistics
Posts filter


"የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሁሉም ተማሪዎች በተማሩበት ስርዓተ ትምህርት ይዘት ይዘጋጃል፡፡" - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የ2017 ዓ.ም ተፈታኝ ተማሪዎች ከ9ኛ-10ኛ በነባሩ ስርዓተ ትምህርት፣ ከ11ኛ-12ኛ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት እንዲሁም ለስርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ በናሙናነት ተመርጠው የተሳተፉ ትምህርት ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች 10ኛ ከፍልን በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የተማሩ መሆናቸውን አገልግሎቱ ገልጿል፡፡

በአማራ ክልል በፀጥታ ችግር ምክንያት በ2016 ዓ.ም ሳይፈተኑ የቀሩና የ11ኛ ክፍልን በነባሩ ስርዓተ ትምህርት የተማሩ ትምህርት ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች በ2017 ዓ.ም የሚፈተኑም አሉ፡፡

በመሆኑም የ2017 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና "ከላይ የተገለፁትን ነባራዊ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ባስገባና ሁሉንም ተፈታኝ ተማሪዎች በማከለ መንገድ ስታንዳርዱን፣ ደህንነቱንና ሚስጢራዊነቱን ጠብቆ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል" ብሏል አገልግሎቱ።

የፈተና ዝግጅቱ ምን ያካትታል?

➫ ከ9ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ ከነባሩ ስርዓተ ትምህርት፣
➫ ከ10ኛ ክፍል በነባሩ እና በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ተመሳሳይ ይዘቶች፣
➫ ከ11ኛ ከፍል በነባሩ እና በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ተመሳሳይ ይዘቶች፣
➫ ከ12ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት የሚዘጋጅ ይሆናል።

የኢኮኖሚክስ የትምህርት ዓይነት በስርዓተ ትምህርቱ አዲስ የተጀመረ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በ12ኛ ክፍል ይዘት ላይ ብቻ ተመስርቶ ይዘጋጃል ተብሏል።

@minster_of_education


ሚዛን ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ በሦስት ዙር ቴክኖሎጂ ነክ በሆኑ ኮርሶች ያሰለጠናቸውን 127 ተማሪዎች አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በዌብ ዲቨሎፕመንት፣ በሞባይል አፕ ዲቨሎፕመንት፣ በግራፊክስ ዲዛይን፣ በዲጂታል ማርኬቲንግ፣ በቪዲዮ ኤዲቲንግ፣ በቤዚክ ኮምፒውተር ስኪል እና በዳታ ሳይንስ መስኮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ተማሪዎቹም በመደበኛ፣ በማታ እና በእረፍት ቀናት በአካል እና በኦንላይን ትምህርታቸውን መከታተላቸውን የኢንስቲትዩቱ ሥራ አስኪያጅ አህመድ ሙሀመድ ገልፀዋል።

በ2014 ዓ.ም የተቋቋመው ኢንስቲትዩቱ እስካሁን ከ300 በላይ ተማሪዎችን ከ 2-9 ወር በሚሰጡ ኮርሶች በሰባት ዙር ማስመረቁን ሥራ አስኪያጁ ጠቁመዋል።

https://t.me/minster_of_education


"በ2017 ዓ.ም 150 ሺህ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን በበይነ መረብ ለመፈተን ዝግጅት እየተደረገ ነው።" - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የምክክር መድረክ በማካሔድ ላይ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) "በዚህ ዓመት 150 ሺህ የሚደርሱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናቸውን በበይነ መረብ እንዲወስዱ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል" ብለዋል።

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በወረቀት እና በኦንላይን ድብልቅ በሆነ መልኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠ ሲሆን፤ 30 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች ፈተናቸውን በኦንላይን መውሰዳቸው ይታወሳል።

https://t.me/minster_of_education




የተለያዩ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በልዩ ልዩ የትምህርት መስኮች ያስተማሯቸውን ተማሪዎች የካቲት 15 እና 16/2017 ዓ.ም ያስመርቃሉ።

አምቦ ዩኒቨርሲቲ፣ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ፣ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ፣ እና ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በሳምንቱ መጨረሻ ተማሪዎቻቸውን ከሚያስመርቁ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል ይገኙበታል፡፡

ተቋማቱ በቅድመ-ምረቃ እና በድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች ያስተምሯቸውን ተማሪዎች ያስመርቃሉ።

@minster_of_education


#ጥቆማ

የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሪፌራል ሆስፒታል በተለያዩ ክፍት የሥራ መደቦች ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል።

የምዝገባ ጊዜ፦
እስከ ሰኞ የካቲት 17/2017 ዓ.ም

የምዝገባ ቦታ፡-
ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሪፌራል ሆስፒታል የሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት የሥራ ሂደት ቢሮ ቁ. 85

➫ አመልካቾች የምታቀርቡት የሥራ ልምድ ከሥራ መደቡ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው መሆን እንዲሁም ደመወዝና ከመቼ እስከ መቼ እንዳገለገሉ የሚገልጽ መሆን አለበት።

➫ አመልካቾች የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውና የማይመለስ አንድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡

➫ አመልካቾች የምታቀርቡት የሥራ ልምድ ማስረጃ የመንግሥታዊ መስሪያ ቤት ካልሆነ የገቢ ግብር መክፈላችሁን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡

➫ ዜሮ ዓመት ለሚጠይቁ የሥራ መደቦች የምትወዳደሩ አመልካቾች የሥራ-አጥ ካርድ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።

አስፈላጊውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች መወዳደር ትችላላችሁ የተባለ ሲሆን፤ የፈተና ቀን በውስጥ ማስታወቂያ ይገለጻል ተብሏል።

@minster_of_education


አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 85 የሕክምና ዶክተሮች እና 160 የጤና ሳይንስ ተማሪዎችን ቅዳሜ የካቲት 15/2017 ዓ.ም ያስመርቃል፡፡

መቱ እና ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሳምንቱ መጨረሻ ተማሪዎቻቸውን ያስመርቃሉ።

@minster_of_education


የድሮ GROUP
ያላችሁ ሰዎች ካላችሁ እየገዛው ነው

በ 2️⃣0️⃣2️⃣2️⃣ የተከፈተ.......💸💸💸
በ 2️⃣0️⃣2️⃣1️⃣ የተከፈተ......💸💸💸
በ 2️⃣0️⃣2️⃣0️⃣ የተከፈተ......💸💸💸
በ 2️⃣0️⃣1️⃣9️⃣ የተከፈተ......💸💸💸
በ 2️⃣0️⃣1️⃣8️⃣ የተከፈተ......💸💸💸
በ 2️⃣0️⃣1️⃣7️⃣ የተከፈተ......💸💸💸

👆👆👆👆
👤ከላይ በጠቀስኳቸው አመት ውስጥ የተከፈተ ማንኛውም ግሩፕ ካላችሁ ከታች በማስቀምጠው አካውንት በማምጣት መሸጥ ትችላላችሁ።

‼️ማሳሰቢያ
➩ 𝗠𝗲𝗺𝗯𝗲𝗿  0 ቢሆንም ችግር የለውም።
➩ ነገር ግን 𝗰𝗵𝗮𝘁 𝗵𝗶𝘀𝘁𝗼𝗿𝘆 𝗰𝗹𝗲𝗮𝗿 እንዳይደረግ
➩ 𝗰𝗵𝗮𝘁 𝗵𝗶𝘀𝘁𝗼𝗿𝘆 ው 𝗗𝗲𝗹𝗲𝘁𝗲 ከሆነ ግሩፑ አያገለግልም❌                               

የግሩፑ አይነት 𝗽𝘂𝗯𝗹𝗶𝗰 ም ይሁን 𝗽𝗿𝗶𝘃𝗮𝘁𝗲 ም ይሁን ምንም ችግር የለውም ።   ነገር ግን 𝗣𝗥𝗜𝗩𝗔𝗧𝗘 የነበረ ግሩፕ 𝗰𝗵𝗮𝘁 𝗵𝗶𝘀𝘁𝗼𝗿𝘆 ውን 𝗩𝗜𝗦𝗜𝗕𝗟𝗘 ማድረግ አለባችሁ።
🇪🇹 💵የክፍያ አማራጮች       
      ➣በ ማንኛውም ባንክ
      ➣በ ቴሌ ብር      
      ➣በ ሞባይል ባንኪንግ
      ➣በ ሲቢኢ ብር
 

ለመሸጥ በዚ ያናግሩኝ
@All_promoteme
@All_promoteme


Forward from: Elad Training and Job Hawassa
⚠️⚠️ሊዘጋ 3ቀን ብቻ ቀረው
ወደ ሮማኒያ በስራ ቪዛ ለመሄድ ይፈልጋሉ
የተመቻቸ የቪዛ አገልግሎቶችን ለማግኘት ይህ ዕድል ለእርሶ ነው ምዝገባው ለ3 ቀናት ብቻ ስለሚቆይ እንዳያመልጦት!
⚠️⚠️ውስን ቦታ ነው ያለን
ይሄ ልዩ ዕድል እንዳያመልጦት !!
ለመመዝገብ


📍 አድራሻ:
ሀዋሳ ፒያሳ አዋሽ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 22

📞 ስልክ:
+251993848358 / +251901506464
በመደወል ይመዝገቡ እንዳያመልጦት!!
Or Ask Any Questions On:- @elad_supporter

✅ Elad Training & Job
🔗 Telegram link 👉👇👇👇
https://t.me/eladtrainigjobhawassa

Facebook Page 👇👇👇

https://facebook.com/eladjobandtraining


የመውጫ ፈተና ውጤት መለቀቅን ተከትሎ በርካታ የኮምፕርሄንሲቭ ነርሲንግ ተፈታኞች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ልከዋል፡፡

"ፈተናው ከብሉ ፕሪንት ውጪ ነው የመጣው" የሚሉት ተፈታኞቹ፤ እርማቱ በድጋሜ ሊታይ ይገባል ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡

በጉዳዩ ላይ ትምህርት ሚኒስቴርን ያነጋገርን ሲሆን፤ ከኮምፕርሄንሲቭ ነርሲንግ ፈተና ጋር የተያያዘ ምንም አይነት ቅሬታ ለተቋሙ #አለመድረሱን ሚኒስቴሩ ጠቁሟል፡፡

በውጤታቸው ላይ ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በትምህርት ሚኒስቴር ውስጥ ለሚገኘው የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ማቅረብ እንደሚችሉም ተቋሙ ገልጿል፡፡

በሌላ በኩል ውጤታቸውን ለማየት የተቸገሩ የግል (በድጋሜ) ተፈታኞች፣ ውጤታቸው ወደተፈተኑበት ተቋም የተላከ በመሆኑ ወደተቋማቱ በመሔድ ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ አስረድቷል፡፡

https://t.me/minster_of_education


ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 612 ተማሪዎችን ዛሬ አስመርቋል።

ከተመራቂዎቹ መካከል 223 በድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆኑ፤ ቀሪዎቹ 389 ተማሪዎች በመደበኛ፣ በተከታታይ እና በክረምት መርሐግብሮች በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ ናቸው።

127 ተማሪዎች በህክምና ትምህርት የተመረቁ መሆናቸው ተገልጿል።

https://t.me/minster_of_education


ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና በተቋሙ የወደሰዱ ተፈታኞች ውጤታቸው ኦንላይን የሚያዩበት አማራጭ አዘጋጅቷል።

የተቋሙ ተፈታኞች ተከታዩን ማስፈንጠሪያ በመጠቀምና የራሳቸውን User Name በማስገባት ውጤታቸውን መመልከት እንደሚችሉ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

የተቋሙ ተፈታኝ ከሆኑ ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ፦
https://script.google.com/macros/s/AKfycbye3I3K9rESI7a7Xr5NHF6-vX7KNbnJcIkTxyR4L4yn7LEd79-1GkzW0ltCOgrD1LlGnQ/exec

https://t.me/minster_of_education


Forward from: Elad Training and Job Hawassa
ወደ ሮማኒያ በስራ ቪዛ ለመሄድ ይፈልጋሉ
የተመቻቸ የቪዛ አገልግሎቶችን ለማግኘት ይህ ዕድል ለእርሶ ነው ምዝገባው ለ4 ቀናት ብቻ ስለሚቆይ እንዳያመልጦት!
⚠️⚠️ውስን ቦታ ውስን ጊዜ ነው ያለን ፡
ለመመዝገብ


📍 አድራሻ:
ሀዋሳ ፒያሳ አዋሽ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 22

📞 ስልክ:
+251993848358 / +251901506464
በመደወል ይመዝገቡ እንዳያመልጦት!!
Or Ask Any Questions On:- @elad_supporter

✅ Elad Training & Job
🔗 Telegram link 👉👇👇👇
https://t.me/eladtrainigjobhawassa

Facebook Page 👇👇👇

https://facebook.com/eladjobandtraining


ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ሥራ ያስጀመረው የመሀል-ሜዳ ካምፓስ ትምህርት መስጠት ጀምሯል፡፡

በቅርቡ ተማሪዎችን የተቀበለው ካምፓሱ፤ የመጀመሪያ ቀን የመጀመሪያ የትምህርት ክፍለ-ጊዜ ዛሬ አካሒዷል።

@minster_of_education


#Exit_Exam_Result

የ2017 አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት ኦንላይን የመመልከቻ ሊንክ መስራት ጀምሯል።

https//result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት ExitExam የሚለውን በመምረጥና የራስዎን User Name በማስገባት ውጤትዎን መመልከት ይችላሉ።

@minster_of_education


UU Mid 2017 Exit Exam Result.pdf
104.3Kb
#UnityUniversity

፨የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል

ከላይ ስማችሁ የተዘረዘረ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ያለፋችሁ መሆኑን ዩንቨርሲቲው አሳውቋል።


@minster_of_education


#TVTI_Exit_Exam

የመውጫ ፈተና የምትወስዱ የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ሰልጣኞች በኦንላይን የምዝገባ ጊዜ ዛሬ ያበቃል።

ተከታዩን ማስፈንጠሪያ በመጫን የምታገኙትን ቅፅ በመሙላት ምዝገባ ያድርጉ 👇
https://forms.office.com/r/3KgnK1esuc

ኦንላይን መመዝገብ የማትችሉ አመልካቾች በኢንስቲትዩቱ ዋናው ግቢ በመገኘት በየትምህርት ክፍላችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል።

🔔 የምዝገባ ጊዜው ዛሬ የካቲት 10/2017 ዓ.ም ያበቃል።

የመውጫ ፈተናውን #በድጋሜ ለምትወስዱ ተፈታኞች ፈተናው በኢንስቲትዩቱ ዋና ግቢ እና በአዲስ አበባ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።

የመዝገባ ብር 500 በኢንስቲትዩቱ የንግድ ባንክ አካውንት በማስገባት ክፍያ በመፈፀም ደረሰኝ መያዝ ይጠበቅባችኋል።

✍ የምዝገባ ጥሪው በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የጋርመንት ቴክኖሎጂ ሰልጣኞችንም ይመለከታል።

የመውጫ ፈተናው ከመጋቢት 6-11/2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ እንደሚሰጥ ኢንስቲትዩቱ ገልጿል።

@minster_of_education



18 last posts shown.