አስተርዮ ማርያም
የማይታየው የታየበት፣ የራቀው የቀረበበት፣ የረቀቀው መለኮት በገዘፈ ሥጋ ማርያም የተገለጠበት፣ የወልድ ልጅነት በአብና በመንፈስ ቅዱስ የተመሰከረበት፣ በልደቱ፣ በጥምቀቱ አንድነት በሦስትነት እንዲሁም መለኮት በሥጋ ሥጋም በመለኮት በተዋሕዶ ተገልጦ ምሥጢሩ ገሃድ የሆነበት የመገለጥ የመታየት ጊዜ የሆነው ወቅት በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ዘመነ አስተርዮ እየተባለ ይጠራል፡፡
በዚሁ በዘመነ አስተርዮ መካከል የሚገኝ ስለሆነ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም “በዓለ ዕረፍት አስተርዮ ማርያም” እየተባለ ይጠራል፡፡ ይህ አስተርዮ ማርያም የምንለው ታላቅ በዓል እናታችን እመቤታችን ከዚህ ዓለም ድካም ያረፈችበት መታሰቢያ ሲሆን ቀኑም ጥር ፳፩ ነው፡፡ ሰማይና ምድር የማይወስኑትን የወሰነች፣ ሞትን በሞቱ የመሻር ሥልጣን ያለውን፣ ዓለምን በመዳፉ የጨበጠውን የወለደች ክብርት ቅድስት እመቤታችን ከዚህ ዓለም ድካም የምታርፍበት ቀን በደረሰ ጊዜ ይኸውም ጥር ፳፩ ቀን በዕለተ እሑድ በ፷፬ ዓመቷ፣ በ፵፱ ዓ.ም መንፈስ ቅዱስ የዕረፍቷ ጊዜ መድረሱን ነግሯት በልጇ መቃብር ሆና ጸሎት ታድርስ ነበር፡፡ እንዲህም ብላ ጸለየች፤ ‹‹ልጄ ወዳጄ ሆይ ልመናዬን ተቀብለህ ደቀ መዝሙርህን ዮሐንስን በዚህች ሰዓት አምጣው፤ እንዲሁም በሕይወተ ሥጋ ያሉ ሐዋርያትን ሁሉንም፣ ነፍሳቸውንም የለየሃቸውን አምጣቸው፤ አንተ የሕያዋንና የሙታን አምላክ ነህና›› አለች፡፡ (የጥር ፳፩ ስንክሳር)
በዚህ ጊዜ ዮሐንስን ደመና ተሸክማ ከኤፌሶን አመጣችው፤ ምስጋናም አቀረበላት፤ ሁሉም ሐዋርያት የሞቱትም ከመቃብር ተነሥተው ወደ እመቤታችን ደርሰው ሰገዱላት፡፡ እንዲህም ስትል ጠየቀቻቸው፤ ‹‹ትነግሩኝ ዘንድ እሻለሁ፤ ከዚህ ዓለም እንደምለይ ከወዴት ሰማችሁ?›› አለቻቸው፡፡