ቅዱስ ጴጥሮስና ሐዋርያት ሁሉም ‹‹ወደ አንቺ እንድንመጣ መንፈስ ቅዱስ አዘዘን፤ በደመና ላይም በተጫን ጊዜ ወደ አንቺ እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥነን ደረስን›› አላት፡፡ በዚያን ጊዜ የክብር ባለቤት ልጇ ወዳጇ ኢየሱስ ክርስቶስ እልፍ አእላፍ መላእክቱን አስከትሎ ወደ እርሷ መጣ፡፡ (ጥር ፳፩ ስንክሳር)
እንዲህም አላት ‹‹እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጥቻለሁ›› አላት፡፡ እርሷ ግን ‹‹ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑህን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀኔ ተሸክሜህ፤ በድንግልና ወልጀህ እሞታለሁን?›› አለችው፡፡ በዚህ ጊዜ በሲኦል የነበሩ ነፍሳትን ሁሉ አሳያትና ‹‹እናቴ ሆይ ሞትሽ ለእነዚህ ሁሉ ነፍሳት መዳን ምክንያት (ቤዛ) ይሆናቸዋል›› አላት፡፡ ‹‹እነዚህን ሁሉ ከማርክልኝስ ይሁን›› አለች፡፡ በዚህ ጊዜ ቅድስት ሥጋዋን ከክብርት ነፍሷ ለይቶ በቃለ አቅርንት በይባቤ መላእክት በክብር ነፍሷን ዐሳረጋት፡፡ (መዝገበ ታሪክ ቁጥር አንድ ገጽ ፻፶፭፣ ጥር ፳፩ ስንክሳር)
የእመቤታችን አማላጅነትና ተረዳኢነት አይለየን፤ አሜን!