“ሃሎ መምህር” የተሰኘ ለሃይማኖታዊ ጥያቄዎች በስልክ ምላሽ የሚሰጥ አገልግሎት መጀመሩ ተገለጸ።
የካቲት ፮/፳፻፲፯ ዓ.ም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት “ሃሎ መምህር” የተሰኘ ለሃይማኖታዊ ጥያቄዎች በስልክ ምላሽ የሚሰጥ አገልግሎት መጀመሩን አስታውቋል።
የስብከተ ወንጌልና ዕቅበተ እምነት ምክትል ኃላፊ ዲያቆን ዐብይ ጌታሁን እንደገለጹት አገልግሎቱ በዋናነት የስብከተ ወንጌልን ተልዕኮ ለማዳረስ በተለይ በቤተ ክርስቲያን የሚገኙ ምዕመናንን በእምነታቸው እንዲጸኑ ለማድረግና ከአዳዲሰ አማንያን የሚመጡ ጥያቄዎችን ለመመለስ የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል።
ከተጀመረ 5 ቀን የሆነው ይህ አገልግሎት ከ 30 እስከ 40 ለሚሆኑ ምዕመናን ለጠየቋቸው ጥያቄዎች ምላሽ መሰጠቱን በመግለጽ ሰዓቱን ያልጠበቁ የስልክ ጥሪዎችን ለማስተናገድ ፈተና እንደሆነባቸው አክለው ገልጸዋል።
በዚህም ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 4፡00 - 10፡00 ሰዓት አገልግሎቱ የሚሰጥ ሲሆን ሰኞ፣ ረቡዕና ዓርብ በኦሮምኛና በአማርኛ እንዲሁም ማክሰኞና ዓርብ በአማርኛ ቋንቋ ብቻ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።
በተጨማሪም ም/ኃላፊው የምዕመናን ተሳትፎ ጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገልጸው “በተለያየ ምክንያት መማር ያልቻሉ፣ ጥያቄ የፈጠረባቸውና በአካል መገኘት ለማይችሉ ምዕመናን በያሉበት ስልክ በመደወል ጥያቄዎችን በመጠየቅ ምላሽ ማግኘት ቢችሉ ከሃይማኖት እንዳይወጡና ከቤተ ክርስቲያን እንዳይለዩ ይረዳቸዋል” በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።