መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፣
በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታዮች ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት በሙሉ፤
የዲያብሎስን የፈተና ወጥመዶች በጣጥሶ በድል ኣድራጊነት የተገለጠው ጌታችን ኣምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ሰባት ዓመተ ምሕረት የጾመ ኢየሱስ ሱባዔ ኣደረሰን አደረሳችሁ!
“አኮ በኅብስት ክመ ዘየሓዩ ሰብእ አላ በኵሉ ቃል ዘይወፅእ እምኣፉሁ ለእግዚአብሔር፡- ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ ኣይኖርም” (ማቴ.፬÷፬)፤
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈለገ ዮርዳኖስ ከተጠመቀ በኋላ ሳይውል ሳያድር ወዲያውኑ ወደ በረኻ በመሄድ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጾመ፡፡
በአርባዎቹ ቀናት ሁሉ በቀንም ሆነ በሌሊት ምንም አልበላም ነበር፤ ካርባ ቀንም በኋላ ተራበ፤ በመብል ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር ማጣላት ልማዱ የሆነ ዲያብሎስም መራቡን ኣይቶ ለምን ትራባለህ?
እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ ይሁኑ ብለህ እዘዝና ብላ፤ የእግዚአብሔር ልጅ አይደለህምን? ይህንን ማድረግ ኣያቅትህም ብሎ በመብል ምክንያት የሱ ታዛዥ እንዲሆን ፈተነው::
በዚህ ጊዜ የጌታችን መልስ “ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ ኣይኖርም” የሚል ነበረ፤
ጌታችን በዚህ አባባሉ የዲያብሎስን ክፉ ሐሳብ የሚንድ እንጂ የእሱ ታዛዥ አለመሆኑን ኣሳየ፤ ዲያብሎስ በዚህ ሳያበቃ በትዕቢት በፍቅረ ንዋይና በባዕድ አምልኮ ሊጥለው ደጋግሞ ሙከራ አደረገ፤ ግን አልተሳካለትም፤
በመጨረሻም ጌታ “ሑር እምድኅሬየ ሰይጣን፣ ሰይጣን ከኋላዬ ወግድ” ብሎ እኩይ ተግባሩን ውድቅ ኣድርጎበታል፤