Posts filter


በአሜሪካዋ አላስካ 10 መንገደኞችን የጫነች አውሮፕላን መጥፋቷ ተገለጸ


የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አውሮፕላኗን እየፈለጉ ነው ተብሏል


በአሜሪካ ባሁለት ሳምንት ውስጥ ሁለት የአውሮፕላን አደጋዎች ተከስተዋል



Via @mussesolomon


በ26 ጎማዎች የሚንቀሳቀሰው የዓለማችን ረጅሙ መኪና

ባንድ ጊዜ 75 ሰዎችን የሚያጓጉዘው ይህ መኪና በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ሰፍሯል

መኪናው ከትራንስፖርት ባለፈ የመዋኛ፣ አነስተኛ የጎልፍ ሜዳ እና አነስተኛ ሂልኮፕተር ማረፊያ ቦታ አለው ተብሏል



Via @mussesolomon


በግሪክ ካንሰር ቀዳሚው የሞት መንስኤ መሆኑ ተነገረ

ካንሰር በግሪክ ውስጥ ዋነኛው የሞት መንስኤ ሲሆን በአብዛኛው በከፍተኛ የሲጋራ ማጨስ መጠን፣ በአየር ብክለት እና በደካማ የህዝብ ጤና ስርዓት ምክንያት እንደሆነ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

የሳንባ ካንሰር በጣም የተለመደ ከካንሰር ጋር በተገናኘ ለሞት የሚዳርግ መንስኤ ነው ሲል ዕለታዊ ቶ ቪማ ዘግቧል። በሴቶች ላይ በብዛት የሚታወቁት የጡት እና የሳንባ ካንሰር ሲሆኑ የፕሮስቴት እና የሳንባ ካንሰር በወንዶች ላይ በብዛት እንደሚገኙ ዘገባው አክሎ ገልጿል።

እንደ ጣሊያን እና ስፔን ካሉ የሜዲትራኒያን ሀገራት ግሪክ ከፍተኛ የሆነ የዜጎች ውፍረት ያለባት ሀገር ስትሆን እስከ 70 በመቶው ዝቅተኛ ገቢ ያለው ህዝብ ይጎዳል ይላል ዘገባው። ዕለታዊው የብሔራዊ የካንሰር ስትራቴጂ አስፈላጊነትን አበክሮ ገልጿል።  “ካንሰርን ለመከላከል ቅድሚያ በመስጠት፣ አዳዲስ ሕክምናዎችን በማድረግ ኢንቨስት በማድረግ እና እኩል የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን በማረጋገጥ፣ ግሪክ ከካንሰር ጋር የተያያዘ ሞትን በእጅጉ በመቀነስ የታካሚዎችን ውጤት ማሻሻል ትችላለች ሲል የመፍትሄ ሀሳብ አቅርባል።


Via @mussesolomon


የኦሃዮ ዩኒቨርስቲ እንዳጠናው ወንዶች የራሳቸውን ፎቶ አብዝተው የሚፖስቱ ከሆነ የአእምሮ በሽተኞች ናቸው።


Via @mussesolomon


ለ15 ቀን ለኢትዮጵያ እንዲጸለይ የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አወጀች

በመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ባሉት ቀጣናዎች፣ ክልሎች እና አጥቢያዎች በሙሉ አገራችን ኢትዮጵያን አስመልክቶ ከየካቲት 1 ጀምሮ እስከ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በጌታ ፊት ጸሎት እንዲደረግ በመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር መሪዎች ጉባኤ መወሰኑን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል::




Via @mussesolomon


በብሪታንያ ከአልኮል መጠጥ ጋር በተያያዘ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በሀገሪቱ ታሪክ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ

በ2023 በሀገሪቱ ከአልኮል መጠጥ ጋር በተያያዘ ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።


Via @mussesolomon


በአዲስ አበባና አካባቢዋ ድሮን ያለ ፈቃድ ማብረር አይቻልም

በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ማንኛውንም አይነት ድሮን ያለ ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ፈቃድ ማስነሳትም ሆነ ማብረር እንደማይቻል የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታውቋል፡፡

አገልግሎቱ በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ የሚደረግ የድሮን እና ሌሎች በራሪ አካላት አጠቃቀምን በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል።

አገልግሎቱ በመግለጫው÷ተቋሙ በአዋጅ ቁጥር 1276/2014 በተሰጠው ስልጣን መሠረት የመሪዎችን፣ የቁልፍ መሠረተ-ልማቶችን እና ብሔራዊ ኩነቶችን ደኅንነት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የማስጠበቅ ኃላፊነት አለበት ብሏል።

Via @mussesolomon


ዛሬ ወደ ሀገር ውስጥ መዳረሻዎች የምትጓዙ መንገደኞች በዓለም አቀፍ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በኩል ወደ በረራችሁ ተሳፋሩ " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ዛሬ ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ ሕንፃ ውስጥ ወደ በረራ ይዞ መግባት ከሚከለከሉ ቁሳቁሶች መካከል ከመንገደኞች የሚሰበሰብ የሲጋራ መለኮሻ (#ላይተር) ጊዜያዊ የማስቀመጫ ስፍራ ውስጥ ጭስ በመከሰቱ ለመንገደኞች ደህንነት ሲባል ሕንፃው ለጊዜው አገልግሎት ማቋረጡን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሳውቋል።

በዛሬው ዕለት ወደ ሀገር ውስጥ መዳረሻዎች የሚጓዙ መንገደኞች በዓለም አቀፍ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በኩል ወደ በረራቸው እንዲሳፈሩ አየር መንገዱ አሳስቧል።

ከነገ ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በተለመደው የሀገር ውስጥ ተርሚናል አገልግሎት መስጠት እንደሚቀጥል ገልጿል።

" ለተፈጠረው መጉላላት መንገደኞቻችንን ይቅርታ እንጠይቃለን " ብሏል።


Via @mussesolomon


በሩሲያ በተካሄደ የከንቲባነት ምርጫ የከተማዋ የቀድሞ ከንቲባ በግል ሹፌሩ ሚስት ተበለጠ

ሩሲያ የከተሞቿን ከንቲባ በምርጫ ውጤት መሰረት እንዲመራ የሚፈቅድ ህግ ትከተላለች

የከንቲባ ምርጫው ውጤት ያልታሰበ እጩ ማሸነፉ አግራሞትን ፈጥሯል



Via @mussesolomon


በማቹሴት ዩኒቨርሲቲ በተሰራ ጥናት የሀሰት ዜና ሰሚ ጋር በመድረስ 6 እጥፍ ከእውነተኛው ዜና እንደሚፈጥን አረጋግጧል::


Via @mussesolomon


ኢትዮጵያን ጨምሮ ሶስት የአፍሪካ ሀገራት ከሩሲያ ጋር በራሳቸው ገንዘብ ለመገበያየት መስማማታቸው ተገለጸ

ሀገራቱ በማዕከላዊ ባንኮቻቸው በኩል ገንዘቦችን በመለዋዋጥ በራሳቸው ገንዘብ ለመገበያየት ነው የተስማሙት።

ከክሪምሊን የወጣው መረጃ እንደሚያመላክተው ይህን ተከትሎ ከሩሲያ ጋር በሀገር ውስጥ ገንዘብ ለመገበያየት ስምምነት ላይ የደረሱ ሀገራት ቁጥር 40 ደርሷል፡፡

እንደ አልጄሪያ፣ ግብፅ፣ ሞሮኮ እና ደቡብ አፍሪካ ያሉ የአፍሪካ ሀገራት በመስከረም 2023 በሩሲያ መንግስት የጸደቀው የመጀመሪያው ዝርዝር ውስጥ ነበሩ።

የአርጀንቲና፣ የካምቦዲያ፣ የላኦስ፣ የሜክሲኮ፣ የናይጄሪያ፣ የቱኒዚያ እና የኢትዮጵያ የንግድ ተወካዮች በመገበያያ ገንዘብ ንግድ እንዲሰማሩ አዲስ ፈቃድ አግኝተዋል፡፡

የሩሲያ መንግስት መመሪያው የሩስያ ኢኮኖሚን በመገበያያ ገንዘብ የሚከፍለውን ፍላጎት ለማሟላት እና ወዳጃዊ እና ገለልተኛ መንግስታት ብሔራዊ ገንዘቦችን በቀጥታ በመለዋወጥ የስርዓቱን ውጤታማነት እንደሚያሳድግ አስታውቋል፡፡



Via @mussesolomon


ከአዲስ ፍቅረኛዋ ጋር ለመኖር የባሏን ኩላሊት ያሸጠችው ህንዳዊት

ከኩላሊት ሽያጭ የተገኘውን ከ11 ሺህ በላይ ዶላር በፌስቡክ ከተዋወቀችው አዲሱ ፍቅረኛዋ ጋር እየተዝናናችበት ነው ተብሏል
የባሏን ኩላሊት አግባብታ ያሸጠችው ህንዳዊት ከሽያጩ የተገኘውን ገንዘብ ይዛ ከአዲስ ፍቅረኛዋ ጋር ጎጆ ቀልሳለች።

በምዕራብ ቤንጋላ ሳንካሬል በተባለች ከተማ ነዋሪ የሆነችው እንስት ባሏ የአካል ክፍሉን እንዲሸጥ ያሳመነችው የሴት ልጃችን የትምህርት ወጪ ለመሸፈንና ለትዳር እድሜዋ ሲደርስ ለጥሎሽ የሚሆን ገንዘብ እንዳንቸገር በሚል ነው።

ባል መጀመሪያ ላይ የሚስቱን አንድ ኩላሊትህን ሸጠን ችግራችን እንለፍ በሚለው ሀሳብ በፍፁም እንደማይቀበለው ቢገልፅም የወራት ውትወታዋ አቋሙን እንዲለውጥ አድርጎታል።



Via @mussesolomon


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘብ ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ደረሰ፡፡
• ባንኩ በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተሰበሰበው ተቀማጭ ገንዘብ 58.3 በመቶ መሰብሰብ ችሏል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድሥት ወራት ብር 245 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ገንዘብ በማሰባሰብ ጠቅላላ የተቀማጭ የገንዘብ መጠኑን ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ማድረስ ችሏል፡፡ ይህ አፈፃም ከእቅድ አንፃር 147.6 በመቶ አፈፃፀም የተመዘገበበት ነው፡፡

ዛሬ በተጀመረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2017 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ጉባኤ ላይ እንደተገለፀው ባንኩ በግማሽ ዓመት ያሰባሰበው የተቀማጭ ገንዘብ መጠን በተመሳሳይ ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተሰበሰበው ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘብ ብር 423.1 ቢሊዮን ብር ውስጥ 58.3 በመቶ ድርሻ እንዲኖረው ያስቻለ ነው፡፡

በባንኩ የተመዘገበው ይህ ውጤት ደንበኞች ከባንኩ ጋር ያላቸው ግንኙነት እና የባንኩ የአገልግሎት ጥራት መሻሻል ማሳያ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፣ ባንኩ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማንቀሳቀስ የተጣለበትን ትልቅ ኃላፊነት ለመወጣት እንደሚያግዘውም ተመላክቷል፡፡


Via @mussesolomon


🛑 25% ብቻ በመክፈል ለውጥ ፈጣሪ ኮርሶችን እንደ Graphics design, video Editing, Digital Marketing, Upwork የምትወስዱበት የዘውድ ቴክ 4ተኛ ዙር ምዝገባ በብዙዎቻችሁ ጥያቄ መሰረት ለጥቂት ጊዜ ተራዝሟል።

✅100% የስራ እድል
✅ጥራት ያለው ስልጠና በ professional አስተማሪዎች
✅አንዴ ከፍለው 4 ስልጠናዎችን የሚወስዱበት
✅ certificate ያለው

️ያሉት ቦታዎች ውስን ስለሆኑ አሁኑኑ ከታች ባለው የዘውድ ቴክ ቻናል ሊንክ ተቀላቅለው orientation ይመልከቱ በመቀጠልም እዛ ላይ ባሉት ስልክ ቁጥሮች መልዕክት መላክ ወይንም መደወል ይችላሉ።

📩ቻናል ሊንክ👇

https://t.me/zewdtech/43


የአንድ ስታዲየም ስፋት ያለው የጠፈር አለት ከሰማይ ወደ መሬት እየተምዘገዘገ ነው ተባለ

የጠፈር አለቱ አሜሪካ በጃፓኗ ሂሮሽማ ላይ ከጣለችው ቦምብ 500 እጥፍ ሀይል አለውም ተብሏል

የአንድ ስታዲየም ስፋት ያለው የጠፈር አለት ከሰማይ ወደ መሬት እየተምዘገዘገ ነው ተባለ፡፡

የአሜሪካ ጠፈር ሳይንስ ምርምር ማዕከል ወይም ናሳ እንደገለጸው ከሆነ አሜሪካ በዓለም ጦርነት ወቅት በጃፓኗ ሂሮሽማ ላይ ከጣለችው ቦምብ በመቶዎች እጥፍ ሀይል ያለው የጠፈር አለት ወይም አስተሮይድ ወደ ምድር እየመጣ ነው ብሏል፡፡

የአንድ ስታዲየም ስፋት መጠን አለው የተባለው ይህ የጠፈር አለት በመጠኑ ባለፉት ስምንት ዓመታት ወደ ምድር ከመጡት ውስጥ ትልቁ እንደሆነ ተገልጿል፡፡




Via @mussesolomon


በአዲስ አበባ እና ሸገር ከተማ የቅድመ ጥገና ሥራ ለማከናወን ሲባል በዕቅድ ኃይል የሚቋረጥባቸው ቦታዎች ::



Via @mussesolomon


ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ 300 ሚሊዮን በላይ አፍሪካዊያንን የኤሌትሪክ ተጠቃሚ ያደርጋል ለተባለዉ ፕሮጀከት 54 ቢሊዮን ዶላር ተመድቧል ተባለ

የአፍሪካ የኃይል ጉባዔ ሚሽን 300 በሚል መሪ ሀሳብ በመጪዎቹ አምስት ዓመታት ኢትዮጵያን ጨምሮ 300 ሚሊዮን አፍሪካውያንን የኤሌትሪክ ኃይል ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት መታቀዱ ተነግሯል።

ለዚህም ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ ከተለያዩ አለምአቀፍ ለጋሽ ተቋማት 53 ነጥብ 95 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱን የአፍሪካ ልማት ባንክ አስታውቋል።

ለሁለት ቀናት በታንዛኒያ ዳሬሠላም በተደረገው ጉባዔ ላይ 30 የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ተመጣጣኝ እና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2030 እንዲስፋፋ ያላቸውን ቁርጠኝነት ማሳየታቸው ተገልጿል።




Via @mussesolomon


ትራምፕ በBRICS አባል ሐገራት ሸቀጦች ላይ 100% የግብር ጭማሪ ለማድረግ ዛቱ!

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የBRICS አባል ሐገራት የአሜሪካዉን ዶላር ትተዉ በሌላ ገንዘብ ለመገበያየት ከወሰኑ ለዩናይትድ ስቴትስ ገበያ በሚያቀርቡት ሸቀጦቻቸዉ ላይ የ100% የቀረጥ ጭማሪ ለማድረግ ዛቱ።

ትራምፕ Truth Social በተባለዉ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴያቸዉ ባሠራጩት ማስጠንቀቂያ እንዳሉት የBRICS አባል ሐገራት ከዶላር ለማፈንገጥ ማሰባቸዉ «ማብቃት አለበት።

ትራምፕ የBRICS አባል መንግሥታትን ለዩናይትድ ስቴትስ «የጠላትነት አዝማሚያ» የሚታይባቸዉ በማለት ወርፈዋቸዋልም።

እነዚሕ ሐገራት፣ ትራምፕ «ግዙፍ» ያሉትን የአሜሪካን ዶላር ለመተካት አዲስ ገዘብ ካሳተሙ ወይም በሌላ ገንዘብ ለመጠቀም ከወሰኑ ከአሜሪካ ገበያ መሰናበት አለባቸዉ።

ትራምፕ እንደሚሉት መስተዳድራቸዉ ወደ አሜሪካ በሚገቡ የየሐገራቱ ሸቀጦች ላይ የ100% የቀረጥ ጭማሪ ያደርጋል።

ቡድኑን በመሠረቱት አምስት ሐገራት ስም የመጀመሪያ ፊደላት ተገጣጥሞ BRICS ተብሎ የሚጠራዉ ቡድን ባሁኑ ወቅት 10 አባል መንግስታትን ያስተናብራል።



Via @mussesolomon


የቻይናው አሊባባ ኩባንያ ከዲፕ ሲክ የተሻለ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ይፋ አደረገ

ዲፕሲክ የተሰኘው የቻይናው ኤአይ ከሰሞኑ የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባያዎችን ማስደንገጡ ይታወሳል

መሰረታቸውን ቻይና ያደረጉ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የዓለም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ውድድሩን እያፋጠኑት ይገኛሉ



Via @mussesolomon


አዲሱ የትራንፕ አስተዳደር የግብረ ሰዶማዊያን ምልክት የሆነውን ማንዲራ እንዲሁም "black lives matter" በየትኛውም የአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ በህንፃዎች እና በፌደራል ተቋማት ላይ እንዳይሰቀል ከልክለዋ


በተጨማሪም ይህንን መመሪያ የጣሱ የመንግስት ሰራተኞች ከስራ መባረርን ጨምሮ የዲሲፕሊን እርምጃ ሊወስዱ እንደሚችሉ ትእዛዝ ሰጥተዋል።



Via @mussesolomon

20 last posts shown.