የመውጫ ፈተና ውጤት መለቀቅን ተከትሎ በርካታ የኮምፕርሄንሲቭ ነርሲንግ ተፈታኞች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ልከዋል፡፡
"ፈተናው ከብሉ ፕሪንት ውጪ ነው የመጣው" የሚሉት ተፈታኞቹ፤ እርማቱ በድጋሜ ሊታይ ይገባል ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡
በጉዳዩ ላይ ትምህርት ሚኒስቴርን ያነጋገርን ሲሆን፤ ከኮምፕርሄንሲቭ ነርሲንግ ፈተና ጋር የተያያዘ ምንም አይነት ቅሬታ ለተቋሙ #አለመድረሱን ሚኒስቴሩ ጠቁሟል፡፡
በውጤታቸው ላይ ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በትምህርት ሚኒስቴር ውስጥ ለሚገኘው የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ማቅረብ እንደሚችሉም ተቋሙ ገልጿል፡፡
በሌላ በኩል ውጤታቸውን ለማየት የተቸገሩ የግል (በድጋሜ) ተፈታኞች፣ ውጤታቸው ወደተፈተኑበት ተቋም የተላከ በመሆኑ ወደተቋማቱ በመሔድ ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ አስረድቷል፡፡
📄
@Exitnewss