"ልጄ የተወለደችው በ5 ወሯ ነው ክብደቷም 750 ግራም ነበር። እንደዚህ ሆና ማየት ለእኔ ከባድ ነበር በጣም አለቀስኩ ፈጣሪ ለምን እንዲህ አደረገ ብዬ አማረርኩት፡፡
ግን ድንገት የሆነ ተዓምር ሊያድናት እንደሚችል አሰብኩ ያ ሃሳብ ደሞ እስከዛሬ ድረስ በህይወት የመኖሯ ሚስጥር ነው።
በአምላኬ ላይ ያለኝ እምነት ጠንካራ መሆን እንዳለበት አመንኩ መጸለይ ጀመርኩ ስለ ምን መጸለይ እንዳለብኝ አላውቅም ነበር ግን ህመሜን እንዲሰማኝ አድርጌ ጸለይኩ እናም የእኔ ኃጥያት ወደ ልጄ እንዳይተላለፍ ፈጣሪን ለመንኩት።
ልጄ ብዙ ችግር ሳይገጥማት ከሆስፒታል እንድትወጣ ጸለይኩ አመንኩም። እምነቴ አድኗት አሁን ላይ ልጄ እድሜዋ 14 ዓመት ሲሆን ሰቃይ ተማሪ ነች። በሁሉም የትምህርት አይነት ውጤቷ A ነው፤ 3 ዓለም አቀፍ ቋንቋዎችን ትናገራለች፡፡
ለካ ይህ ሁሉ ነገር የተፈጠረው እኔ ወደ ፈጣሪ ይበልጥ እንድቀርበው አስቦ ነው።
እናንተም ችግር ሲገጥማችሁ ከችግሩ ትልቅነት ይልቅ የፈጣሪን ትልቅነት ለራሳችሁ እየነገራችሁ ወደ አምላካችሁ ቅረቡ እንጂ አታማሩ።"
አባት 🙌❤